Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የሰርጥ አድራሻ: @addiszeybe
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.27K
የሰርጥ መግለጫ

ለፈጣን መረጃዎች አዲስ ዘይቤ
Twitter : https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Website : https://addiszeybe.com/
YouTube : https://youtube.com/c/AddisZeybe
Instagram : https://bit.ly/3D1tEwC
ስልክ 251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 90

2022-09-29 18:22:27
በአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ መድረሱ ተሰማ

መስከረም 19/2015 ዓ/ም

(አዲስ ዘይቤ፣ አዳማ) በአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ ከአዳማ መግቢያ 11 ኪሜ ርቀት ላይ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ መድረሱን የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ የትራፊክ ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወርቅነህ ተርፌሳ ለአዲስ ዘይቤ ገልጸዋል።

የአደጋው ሁኔታ ባልተለመደ ሁኔታ ከባድ እንደሆነ ከተለያዩ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ቢጠቁምም በተጨባጭ የአደጋውን ክብደትና ሁኔታ ማረጋገጥ አልቻልንም።

የአደጋውን ዝርዝር ሁኔታ እያጣሩ እንደሆነ የገለጹት የዞኑ ፖሊስ የትራፊክ ዲቪዥን ኃላፊ፣ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አዳማ ኮንፕሬንሲቭ ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ተናግረዋል።

ስለጉዳዩ ለማጣራት ወደ ኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ባለስልጣን ህዝብ ግንኙነት ደጋግመን ብንደውልም ስልክ ባለመነሳቱ ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም።
@AddisZeybe
520 viewsedited  15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 18:09:38 ነዳጅ በሊትር 10 ብር ጨመረ - Zeybe+
ሙሉ ቪድዮውን ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ


483 viewsedited  15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 15:41:54
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ለኮማንደር ዋጋው ታረቀኝ ቤተሰቦች ድጋፍ አደረገ

መስከረም 19/2015 ዓ.ም

አዲስ ዘይቤ (አዲስ አበባ) ከንቲባ ድረስ (ዶ/ር) ሳህሉ የተመራው የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሜቴ ስራ ላይ እንዳለ ህይወቱ ላለፈው የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አባል በነበረው ኮማንደር ዋጋው ታረቀኝ ቤተሰቦች ቤት በመገኘት ድጋፍ አደረጉ።

በተደረገውም ድጋፍ የሁለት መቶ ሺህ ብር ስጦታ፣ በአባይ ማዶ አፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ የገበያ ቦታ፣ ከመንግሥት ኪራይ ቤቶች በኪራይ የተቀበሉትን የኪራይ ቤት ውል በኮማንደር ዋጋ ታረቀኝ ባለቤት ስም እንዲሆንና በቀጣይ የመኖሪያ ቤት ማደራጀት ሲጀመር አስፈላጊ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው የከተማው ከንቲባ ገልፀዋል።
___
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።
Twitter : https://bit.ly/3uQBnvj
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Telegram : https://bit.ly/3JX93LY
Website : https://bit.ly/3JOUavm
YouTube : https://bit.ly/37rIyBa
603 viewsedited  12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 12:18:23 አቶ ተመስገን ሞላ እና ባለቤታቸው ወ/ሮ ትግስት ይርጋ በግንባታ ስራ የሚተዳደሩ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ናቸው። አቶ ተመስገን በግንበኝነት ወ/ሮ ትግስት ደግሞ በለሳኝነት ለረዥም ዓመት ሰርተዋል። ሁለት ልጆቻቸውን በግል ትምህርት ቤት የሚያስተምሩት ባልና ሚስት፤ የሲሚንቶ ዋጋ ንረት እና ከገበያ መጥፋት ቤተሰባቸው ለችግር አጋልጧል።

የሕንጻ ገንቢዎች ደግሞ ሲሚንቶ ለማግኘት በቀበሌ ተመዝግበው፣ አስፈላጊውን ቅድመ ሆኔታ አሟልተው፣ ለአቅራቢው ድርጅት ደብዳቤ ተፅፎላቸው ክፍያ ከፈጸሙ ከወር በላይ ቢሆናቸውም ሲሚንቶ ማግኘት ግን አልቻሉም። ባህር ዳር የሚገኘው የአዲስ ዘይቤ ሪፖርተር በከተማው ያለውን የሲሚንቶ ችግር እንዲህ ዘግቦታል።
https://bit.ly/3Cjbjwz
#Ethiopia #Bahirdar
@AddisZeybe
270 views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 10:42:20
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በጎንደር አገልግሎት መስጠት ጀመረ

መስከረም 19፤ 2015 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ ፣ጎንደር) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በጎንደር ከተማ በ አራት ቦታዎች ስራ መጀመሩን አስታወቀ። የቴሌኮም ድርጅቱ በ አራዳ ፣ፒያሳ፣ኮሌጅ እና አዘዞ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ትላንት መስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም ስራ ጀምሯል።

የሲም ካርድ እና ሞባይል ካርድ መሸጥ እንዲሁም የሞባይል ቀፎ የማከፋፈል ስራውን የጀመረው ሳፋሪኮም ሶስት አይነት የሞባይል ቀፎዎች ለገበያ ያቀረበ መሆኑን የ ጎንደር ቅርንጫፍ ሰራተኞች ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል።

የሞባይል ቀፎዎቹ “አዋዜ”፣ “ቅመም” እና “ናና” የሚል ስም ያላቸው ሲሆን “አዋዜ” የሚባለው ስልክ አነስተኛ ስልክ ሲሆን ቅመም የሚባለው የስልክ ቀፎ ደግሞ የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጥ አነስተኛ ስልክ ነው ያሉት ሰራተኞቹ "ናና" ተብሎ የሚጠራው ደግሞ ስማርት ስልክ ነው።

ሞባይሎቹ ሁለት ሲም ካርድ እንዲያስጠቅሙ ሁነው የተሰሩ ሲሆኑ ቢያንስ አንዱ የሳፋሪኮም ሲም ካርድ ካልሆነ አገልግሎት አይሰጡም ተብሏል።
389 views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 09:30:27
ፕሮፌሰር መስፍንን ስናስታውስ. . . አንጋፋው ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኛና ምሁር ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ልክ የዛሬ ሁለት አመት ነበር ከዚህ አለም በሞት የተለዩት።
441 viewsedited  06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 09:14:29 This day, Sep 29 marks the 2nd year anniversary of the death of Professor Mesfin Woldemariam, a popular Ethiopian politician and academic. Professor Mesfin engagement in Ethiopian politics is rarely interregimic as only a few have featured strong and controversial careers spanning from the Emperor’s time to the current administration of Dr. Abiy Ahmed. Read More....
https://bit.ly/3BSCvRA
#Ethiopia #AddisAbaba
@AddisZeybe
477 views06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 19:53:12 የዶላር እና ብር አቅም አለመመጣጠን የፈጠረው ጫና - Zeybe+
ሙሉ ቪድዮውን ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ


237 views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 19:43:09 Ethio Telcom stated that 192.1 million ETB (about 3.6 million USD) is deposited in its Telebirr Sanduq micro saving service and has given out a total loan of 157.9 million ETB (about 3 million USD) in its Telebirr Mela micro-credit service. Telebirr issued the mentioned amounts of loans and collected deposits just in less than two months. Read More
https://bit.ly/3xZWi0l
#Ethiopia #AddisAbaba #Telecom
@AddisZeybe
264 views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 17:38:34 የድሬዳዋውን ቅዱስ አላዛር ታሪካዊው ማተሚያ ቤት - Zeybe+
ሙሉ ቪድዮውን ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ


406 viewsedited  14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ