Get Mystery Box with random crypto!

የሰሜኑ ጦርነት እና በኦሮሚያ ያለው ግጭት መላ ሀገሪቱን እና ህዝቦቿን የሚጎዳ ነው ሲል ኦፌኮ አሳ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የሰሜኑ ጦርነት እና በኦሮሚያ ያለው ግጭት መላ ሀገሪቱን እና ህዝቦቿን የሚጎዳ ነው ሲል ኦፌኮ አሳሰበ

ነሃሴ 25፤ 2014 ዓ.ም

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት መላ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን የሚጎዳ ነው ሲል የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አሳስቧል።

ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ "በሁለቱም አካባቢዎች ያለው ግጭት ህዝብን ዳግም ለከፋ ሞት እና መፈናቀል የሚዳርግ እንዲሁም ሰፊ የመሰረተ ልማት ውድመት የገጠማቸው አካባቢዎችን ይበልጥ እንዳይረጋጉ የሚያደርግ ነው" ብሏል።

ችግሮቹ በዘላቂነት ሊፈቱ የሚችሉት “እውነተኛ እና ሁሉን አሳታፊ በሆነ ድርድር ብቻ ነው” ያለው ኦፌኮ ሁሉም ተፋላሚ ኃይሎች ለሰላማዊ መፍትሔ ፍላጎት እንዲኖራቸው ጥሪ አቅርቧል።

በኦሮሚያ ክልል ያለው “ጦርነት” ሊፈታ ቀርቶ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅናም ሊሰጠው አለመቻሉ አሳሳቢ ነው ሲል ፓርቲው በመግለጫው አስገንዝቧል።

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ገዢው ፓርቲ፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሚድያ ባለሙያዎች እና አክቲቪስቶች ግጭቱን ከሚያባብሱ ንግግሮች እንዲታቀቡም ተማፅኗል።
_____
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።
Twitter : https://bit.ly/3uQBnvj
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Telegram : https://bit.ly/3JX93LY
Website : https://bit.ly/3JOUavm
YouTube : https://bit.ly/37rIyBa