Get Mystery Box with random crypto!

AMN-Addis Media Network

የቴሌግራም ቻናል አርማ addismedianetwork — AMN-Addis Media Network A
የቴሌግራም ቻናል አርማ addismedianetwork — AMN-Addis Media Network
የሰርጥ አድራሻ: @addismedianetwork
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.65K
የሰርጥ መግለጫ

This is an official Telegram channal for Addis Media Network (AMN) We trive to be the prime informer of issues. Hence, our motto says so, 'first to inform'
ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ !!
contact us via:- E-mail:- addisaammaa@gmail.com
twitter.com/AmnAddis

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-19 09:56:29
6.1K views06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 18:29:34
የሱዳን ሕዝብ አሁን ካጋጠመው ሁኔታ ለመውጣት የሚያስችለው ጥበብና ችሎታ ያለው ሕዝብ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

የሱዳን ሕዝብ አሁን ካጋጠመው ሁኔታ ለመውጣት የሚያስችለው ጥበብና ችሎታ ያለው ሕዝብ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ የጎረቤት አገር ሱዳን ህዝቦች ከጥንትም ጀምረው ነፃነታቸውን የሚወዱ እና ብሄራዊ ክብራቸውን አስጠብቀው የቆዩ ህዝቦች መሆናቸው አውስተዋል፡፡

የሱዳን ህዝብ ከሚወሳባቸው አያሌ መልካም ባህሪያት መካከል ለጋስነት እና እንግዳ ተቀባይነታቸው ከምንም በላይ ጎልቶ ይጠቀሳልም ብለዋል።

እነዚህ እሴቶች ደግሞ ከማህበራዊ ትስስሩ በላይ የኢትዮጵያን እና የሱዳንን ህዝብ የሚያመሳስሉ እና ይበልጥ የሚያቆራኙ ብለውም ከሌላው እንዲለዩ ከሚያረጓቸው እውነታዎች ሆነው እናገኛቸዋለን ነው ያሉት።

በመሆኑም የሱዳን ህዝብ በባህሪው ኩሩ በመሆኑ በምንም ሁኔታ ክብሩን እና ነፃነቱን አሳልፎ የሚሰጥ አያደርገውም ብለዋል።

ስለሆነም የሱዳን ህዝብ የራሱን ችግር በራሱ የመፍታት ታላቅ ዓቅም እና ጥበብ ያለው ታላቅ ህዝብ በመሆኑ ማንኛውም የሁከት ዓላማን ያነገበ የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያስተናግድ አይሆንም ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
11.6K views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 18:29:11
አቶ ደመቀ መኮንን ከሱዳን አቻቸው ጋር በስልክ ተወያዩ

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር አሊ ኢል ሳዲግ አሊ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡

አቶ ደመቀ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ ከሱዳኑ አቻቸው ጋር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያ ለሱዳን ህዝብ ያላትን አጋርነት እንዲሁም በተከሰተው ግጭት በሞቱ ዜጎች የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡

የሱዳን ህዝብ በተለይም በተቀደሰው ረመዳን ወር የተከሰተውን ግጭት በማብረድ ወደ ቀድሞው ሰላም እንደሚመለስ ያላቸውን እምነት መግለፃቸውን ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
9.0K views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 16:18:13 የሀገራችን የፖለቲካ ተዋናያን ከህገ ወጥ እና መርህ አልባ እንቅስቃሴ ሊቆጠቡ ይገባል! -ብልጽግና ፓርቲ

የሀገራችን የፖለቲካ ተዋናያን ከህገ ወጥ እና መርህ አልባ እንቅስቃሴ ሊቆጠቡ እንደሚገባ ብልጽግና ፓርቲ አሳሰበ።

ፓርቲው ያወጣው ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የብልጽግና ፓርቲ የሁሉም አቋሞቹ እና ተግባሩ መነሻ እና መድረሻ የኢትዮጵያ ህልውና፣ ታላቅነት፣ ብልጽግና እና የህዝቦቿ ሰላም ብቻ ነው፡፡ በዚህ የማይናወጥ ሀገራዊ እና ህዝባዊ መሰረት ላይ ቆመን ለመላ የሀገራችን ህዝቦች የጋራ ደጀን ፣መከታ፣ ክንድ እና የማይታጠፍ አለኝታ የሆነ ሀገራዊ ሰራዊት ለመገንባት ህገ መንግስቱን መሰረት ያደረገ ጥረቶች ማድረግ ከጀመርን ውለን አድረናል፡፡ በስድስተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ቅስቀሳ ወቅትም የክልሎችን ልዩ ሃይል በህገ መንግስቱ መሰረት መልሰን እንደምናደራጅ አቋማችን ለህዝብ ግልጽ ማድረጋችን ይታወሳል፡፡

ስለሆነም አሁን ላይ ለብዥታ እና ተገቢውን መስመር ለሳተ የትርጉም አንድምታ የተጋለጠው ልዩ ሃይሎቻችንን መልሶ የማደራጀት እንቅስቃሴም አንዳንዶች በሚያሳዝን ሁኔታ አጣመው እንደሚለፍፉት እንግዳ ደራሽ የሆነ የቶሎ ቶሎ ቤት አይነት ውሳኔ ሳይሆን በብዙ ጥናት፣ በጥልቅ ውይይት፣ በሰከነ ንግግር እና በጋራ መግባባት የተደረሰበት ውሳኔ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከህዝባችንም የክልል ልዩ ሃይሎች ህገ መንግስቱን መሰረት ባደረገ እና የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት በተሻለ መልኩ በሚያስጠብቅ አኳሃን መልሶ የማደራጀት ስራ መሰራት እንዳለበት በተለያየ መልኩ ለመንግስትና ለፓርቲያችን ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ውሳኔው የህዝቡን ፍላጎት ከግምት ዉስጥ ያስገባና ህገመንግስታዊ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በህገ መንግስታችን ላይ በማያሻማ መልኩ እንደተመለከተው ሀገርን እና ህዝብን ከየትኛውም ጥቃት እና ጠላት የሚከላከል ሀገራዊ ሀይል የመገንባት ሃላፊነት እና ስልጣን የፌዴራል መንግስቱ ብቻ እንደሆነ በግልጽ ተመልክቷል፡፡ የክልል መንግስታትም የክልላቸዉን ሰላምና ጸጥታ የሚያስጠብቅ ክልላዊ ፖሊስ አደራጅተዉ እንደሚመሩ በህገ መንግስቱ ተደንግጓል፡፡

በዚህም መሰረት የክልል ልዩ ሀይሎችን እንደገና የማደራጀት አስፈላጊነት ልክ ያልነበረን ጉዳይ ልክ የማድረግ ውሳኔ እና ጥረት እንጂ ሌላ ምንም አመክንዮ እንደሌለው በውል ሊታወቅ ይገባል፡፡ አንዳንድ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች እና መሪዎቻቸው እንዲሁም ማህበራዊ አንቂዎች ነን የሚሉ ግለሰቦች ጉዳዩን አንድን ክልል ብቻ ትጥቅ የማስፈታት ጉዳይ አድርገዉ የሚያቀርቡበትና ጉዳዩን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው ‹‹ማክሰም፣ ማጠፍ፣ ማፍረስ፣ መበተን…›› ወዘተ የሚሉት አገላለጾች ምንጫቸው- ከየት እና ምርጫቸው- እንዴት ሆኑ የሚለውን መተንተን ለዚህ አውድ ፋይዳው ብዙ ባይሆንም ግባቸው ግን ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ እና ህዝብን ለማሳሳት በመሞከር ጊዜያዊ ቅቡልነት ለማግኘት የመጣር ፍላጎት እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ ስለሆነም ከዚህ ሀገርን ዋጋ ከሚያስከፍል ህገ ወጥ እና መርህ አልባ እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ ፓርቲያችን ያሳስባል፡፡

ፓርቲያችን በጽኑ መግለጽ የሚፈልገዉ ዋና ጉዳይ ልዩ ሀይልን ትጥቅ የማስፈታት ሳይሆን የተሻለ የማስታጠቅ፤ የመበተን ሳይሆን በጠንካራ መሰረት ላይ የማደራጀት ስራ ላይ የመሆናችንን የማያሻማ እውነት ነው፡፡ የሁሉም ክልል ልዩ ሀይሎች በብዙ ሀገራዊ ፈተናዎቻችን እና ድሎቻችን ውስጥ መቼም ሊደበዝዝ የማይችል ደማቅ አሻራ እንዳላቸው ፓርቲያችን በጽኑ ያምናል፡፡ በምንም ስለማይተመነውና በነፍሳቸው ተወራርደው ስለሰጡት አገልግሎትም በተለየ አክብሮት እና ፍቅር ያመሰግናሉ፡፡

የልዩ ሀይሎቻችን በመከላከያ፣ ፌዴራል ፖሊስ እና የክልል ፖሊስ መዋቅሮች ውስጥ ተደራጅተዉ ሀገርን እና ህዝብን ማገልገል ለመላው የሀገራችን ህዝቦች የሚኖረው አስተዋጽኦ እጅጉን ሰፊ እና መሰረታዊ ለውጥ የሚያስገኝ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ልዩ ሀይሎቻችንን እስከዛሬ ስትሰጡት ከነበረው አገልግሎት በተሻለ አደረጃጀት፣ ትጥቅ እና ወታደራዊ ብቃት እንድታገለግሉ አስተማማኝ እድል የሚያጎናጽፋቸዉ በመሆኑ ህግ እና ስርዓትን በጠበቀ አኳሃን ለውሳኔው ተግባራዊነት የበኩላቸሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ይህ ውሳኔ በአማራ ክልል ላይ ብቻ የተወሰነ ውሳኔ አድርገው ለማቅረብ የሚጋጋጡ ዘገር ነቅናቂ ግጭት- ናፋቂ ሀይሎች የሚነዙት መርዛማ መረጃ ፍጹም ሀሰት እንደሆነ ፓርቲያችን በአጽንኦት ማሳወቅ ይፈልጋል፤ ውሳኔው ሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተነጋግረው የተወሰነ ውሳኔ ብቻ ሳይሆን በተመሳሳይ የጊዜ መስመር በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የሚተገበር መሆኑን አበክሮ ያስታውቃል፡፡ የክልል ልዩ ሀይሎች ህገመንግስታዊ በሆኑት የጸጥታ መዋቅሮች ገብተው እንዲያገለግሉ መደረግ እንዳለበት ከብልጽግና እኩል (አንዳንዴም በላይ) ሀሳብ ሲያነሱ እና ሲሞግቱ የነበሩ ፓርቲዎችና አመራሮችም ጭምር ዛሬ ላይ ከስጋው ጾማለሁ ከመረቁ ስጡኝ አይነት መግለጫ ለማውጣት መጋጋጣቸው ፓርቲያችንን እጅጉን አሳዝኖታል፡፡

ሆኖም ግን ብልጽግና ፓርቲ በተግዳሮቶች ውስጥም ቢሆን ከህዝባችን እና ከሁሉም የልዩ ሀይል አመራሮቻችና አባላት ጋር በስክነት በመወያየት እና የተፈጠረውን የተግባቦት ክፍተት በመሙላት ለሀገር እና ለህዝብ ዘላቂ ሰላም በሚበጀው ጎዳና መጓዙን ይቀጥላል፡፡

በዚህ አጋጣሚም ሻማ እንዲሸጥላቸው ጨለማ የሚናፍቁ እና የሚጠብቁ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና መሪዎቻቸው ነገሮችን ከማባባስ እና ሞትን ለመጥመቅ- ግጭት ከመጠንሰስ እንዲቆጠቡ በአጽንኦት ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ‹‹እዉነት እና ንጋት እያደረ ይጠራል›› እንደሚባለው ውሳኔው ነገ ከነገ ወድያ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ ሆኖ በታሰበው መሰረት ተፈጻሚ ሲሆን ለሚታይ ግልጽ ውሳኔ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ በመክፈል ሰላማችን እንዳይደፈርስ መላው የአማራ ህዝብ እና የልዩ ሃይል አባሎቻችን ነገሮችን በሰከነ መልኩ እንዲያዩ እና ለዚህ ሀገርን እና ህዝብን ለሚጠቅም ቀና ውሳኔ ቀና ምላሽ እንዲሰጡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ህብረ ብሄራዊ ክንዳችን- ለሁለንተናዊ ሰላማችን!
ሚያዝያ 2 ቀን 2015 ዓ.ም
የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት
4.4K views13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 11:43:51
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ ከጸጥታ አካላት ጋር በቁርኝት መሥራት ይኖርባቸዋል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን)መጋቢት 19/2015

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ ከጸጥታ አካላት ጋር በቁርኝት መሥራት ይኖርባቸዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዜጎች ወደ አዲስ አበባ በሰላም መግባት እየተቸገሩ ነው በሚል ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ሰዎች በነጻነት የመዘዋወር መብት እንዳላቸው በመጥቀስ ይህ መብት እንዲከበር መስራት አለብን ብለዋል፡፡

አዲስ አበባን የብጥብጥ ማዕከል ማድረግ እና ስልጣን ለመያዝ የሚያስቡ የሀገር ውስጥ ሃይሎች መኖራቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህን ለመከላከል በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ሃይሎች የሕዝብ በዓላት ሲኖሩ አበል ከፍለው ሰዎች ወደ አዲስ አበባ ያስገባሉም ነው ያሉት፡፡

ይሄን ለመከላከል በቅንጅት ይሰራል በማለት ይህ ሲደረግ ንጹሃን እንዳይጉላሉ ከባለፈው ስህተት በመማር ማስተካከያ ይደረጋል ሲሉም አብራርተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ ከጸጥታ አካላት ጋር በቁርኝት መሥራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።
3.8K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 11:43:13
የሚዲያ ነፃነት ትክክለኛ መረጃን ለህብረተሰቡ ማድረስ እንጂ የራስን ፍላጎት በሀይል መጫን አይደለም-ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎር(ኤ ኤም ኤን) መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከተነሱት ጥያቄዎች መካከልም አንዳንድ ሚዲያዎች ሀሰተኛና ያልተገባ መረጃዎችን በመልቀቅ ህዝብ ወደ ግጭት እንዲገባ የየሚገፋፉ አሉና ከመንገስት ምን ይጠበቃል የሚል ይገኝበታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለተነሳቸው ጥያቄ በሀገራችንም ሆነ በዓለም ላይ በርካታ ሚዲያዎች አሉ፡፡ በእነዚህ ሚዲያዎች በርካታ መረጃዎች ይለቀቃሉ፡፡ አድማጮችም ከሚለቀቁ መረጃዎች መካከል ታማኝና ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮችን መርጦ መከታተል እንደሚገባ ነው የገለጹት፡፡

የሚዲያ ነፃነት ሲሰጥ ሚዲያዎች ራሳቸውን በራሳቸው አርመው ትክክለኛ መረጃን ለህብረተሰቡ እንዲያደርሱ እንጂ ህዝብን የሚረብሽና ወደ አላስፈላጊ ብጥብጥ የሚወስድ መሆን የለበትም ብለዋ ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

አንዳንድ ሚዲያዎች ግጭት ይፈጥራሉ፤ ግጭት ያባዛሉ ፤ይህ አልሆን ሲላቸውም ደግሞ ታሪክን እየመዘዙ ህዝብን ወደ ጥፋት ይወስዳሉ፤ እንደነዚህ አይነት ሚዲያዎች ራሳቸውን መፈተሸ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን እንደነዚህ አይነት ሚዲያዎችን እየተከታተለ ህጋዊ የማስተካከል ስራ መስራት እንደሚገባም ጠቀላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
3.7K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 11:41:09
"ኢትዮጰዕያ እንዳትፈርስ መንግስታችን የከፈለውን መስዋትነት አለም የሚያውቀው ነው። ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብም የሚያውቀው ነው። አለም ሲጮህብን ኢትዮጵያዊያን ክብር አለን ብለን ፀንተን የቆምን ነን!!"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
3.4K views08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 09:59:00 https://www.youtube.com/live/5HGXp_1RlNc?feature=share
4.0K views06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 13:12:27
የመደመር ትውልድ መርሆዎች!
4.2K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 13:11:08
4.2K views10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ