Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ ከጸጥታ አካላት ጋር በቁርኝት መሥራት ይኖርባቸ | AMN-Addis Media Network

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ ከጸጥታ አካላት ጋር በቁርኝት መሥራት ይኖርባቸዋል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን)መጋቢት 19/2015

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ ከጸጥታ አካላት ጋር በቁርኝት መሥራት ይኖርባቸዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዜጎች ወደ አዲስ አበባ በሰላም መግባት እየተቸገሩ ነው በሚል ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ሰዎች በነጻነት የመዘዋወር መብት እንዳላቸው በመጥቀስ ይህ መብት እንዲከበር መስራት አለብን ብለዋል፡፡

አዲስ አበባን የብጥብጥ ማዕከል ማድረግ እና ስልጣን ለመያዝ የሚያስቡ የሀገር ውስጥ ሃይሎች መኖራቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህን ለመከላከል በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ሃይሎች የሕዝብ በዓላት ሲኖሩ አበል ከፍለው ሰዎች ወደ አዲስ አበባ ያስገባሉም ነው ያሉት፡፡

ይሄን ለመከላከል በቅንጅት ይሰራል በማለት ይህ ሲደረግ ንጹሃን እንዳይጉላሉ ከባለፈው ስህተት በመማር ማስተካከያ ይደረጋል ሲሉም አብራርተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ ከጸጥታ አካላት ጋር በቁርኝት መሥራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።