2023-10-04 11:00:41
በትምህርት ዘርፍ ያለውን የጥራት ችግር ዘላቂ በሆነ ሀገራዊ መፍትሄ ለመፍታት የትምህርት ተቋማት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መስከረም 23/2016 ዓ.ም
በትምህርት ዘርፍ ያለውን የጥራት ችግር ዘላቂ በሆነ ሀገራዊ መፍትሄ ለመፍታት የትምህርት ተቋማት ኃላፊነታቸውን በትጋት እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ይፋዊ የትምህርት ዘርፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋምነት ምስረታውን እያከበረ ይገኛል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ብርሀነመስቀል ጠና ለ6 ዩኒቨርስቲው አስርት ዓመታት በትምህርት ዘርፍ ትውልድና ሀገርን ሲያገለግል ስለመቆየቱ አንስተዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የትምህርት ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሆኖ የተቋቋመው የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ዘርፍ ያለውን ሀገራዊ ድርሻና ሚና ለማላቅ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩሉን ለመወጣት እየተሰራ ነውም ብለዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ተወካይ ሚኒስትር ዲዔታ ዶ/ር ሰለሞን አብርሀ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የትምህርት ተደራሽነት ለማሳደግ የተገኙ ውጤቶችን ያክል የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ሰፊ ጥረት ይፈልጋልም ብለዋል።
በዚህ ረገድ እንደ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ያሉ የትምህርት ዘርፉን አጋዥ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ራሳቸውን የማብቃትና ለተሻለ ሀገራዊ ኃላፊነት ዝግጁ የመሆን ተልዕኳቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በአዋጅ ወደ ትምህርት የከፍተኛ ትምህርት ተቋምነት ከተዛወረበት መስከረም 2014 ወዲህ ተቋማዊ ለውጥና ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።
የዩኒቨርሲቲውን ምስረታና ቀጣይ ተልዕኮ በሚመለከት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች፣ ከምሁራን እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር እየመከረ ይገኛል።
በአቡ ቻሌ
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr
Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9
Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8
Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ
13.1K views08:00