Get Mystery Box with random crypto!

AMN-Addis Media Network

የቴሌግራም ቻናል አርማ addismedianetwork — AMN-Addis Media Network A
የቴሌግራም ቻናል አርማ addismedianetwork — AMN-Addis Media Network
የሰርጥ አድራሻ: @addismedianetwork
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.65K
የሰርጥ መግለጫ

This is an official Telegram channal for Addis Media Network (AMN) We trive to be the prime informer of issues. Hence, our motto says so, 'first to inform'
ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ !!
contact us via:- E-mail:- addisaammaa@gmail.com
twitter.com/AmnAddis

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-05 08:23:54
እንኳን ለዐርበኞች ቀን(የድል በዓል) አደረሳችሁ

ኢትዮጵያ የነጻነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ያላት ሀገር ነች። ነጻነታቸውን በምንም ነገር ለመቀየር ፈቃደኛ ያልሆኑት እናቶቻችን እና አባቶቻችን ለነጻነት ሲሉ ዋጋ ከፍለዋል።

እናቶቻችን እና አባቶቻችን ሕይወት ከፍለው ያቆዩልን ነጻነት ብቻቸውን አይቆምም። በሌሎች ነጻነቶች መደገፍ አለበት። ሀብት፣ ኅብረትና አገልጋይነት ሊደግፉት ይገባል።

በኢኮኖሚው ዘርፍ በርትተን ሀገራዊ ሀብት ካልፈጠርንና ከርዳታ ካልተላቀቅን ነጻነት ብቻውን ሩቅ አይወስደንም። ኩሩ ድኻ ያደርገናል እንጂ። ኅብረት ፈጥረን መለያየትንና መከፋፈልን ካላሸነፍን ነጻነት ብቻዉን ኃይል አይሆነንም። በኅብረት ያገኘነው ነጻነት በመለያየት በፈቃዳችን እናጣዋለንና።

ሀገርንና ሕዝብን በቅንነትና በትጋትና በንጽሕና ለማገልገል ካልወሰንን ነጻነት ብቻውን ዕድገት አያመጣም። ሙስና፣ ኋላ ቀር አሠራርና ስንፍና ወደኋላ ይጎትቱናልና።

የድል ቀናችንን ስናከብር ከዐርበኞቻችን ድል በኋላ ያስመዘገብናቸውን ድሎች በመቁጠር መሆን አለበት። ድል የማይወልድ ድል ድል አይባልም።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሚያዚያ 27፣ 2015 ዓ.ም
10.5K views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 19:55:30
ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ እና በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ፦
16.9K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 19:55:10
ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ እና በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የሚፈለጉ፦
14.6K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:26:44
13.7K views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:26:26 ሚያዝያ 22 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
10.8K views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:26:26 ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ

በአማራ ክልል ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመያዝ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በህቡዕ ተደራጅተውና ተቀናጅተው በሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።

በመሆኑም የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል እየወሰደ ባለው እርምጃ በዚህ ህቡዕ አደረጃጀት ውስጥ ሲንቀሳቀሱና የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ የተገኙ 47 ተጠርጣሪዎችን ከበርካታ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሣሪያዎች፣ ቦንቦችና ተቀጣጣይ ፈንጂዎች እንዲሁም ከሳተላይት መገናኛ መሣሪያዎች እና የተለያዩ መረጃዎችን ከያዙ ላፕቶፖች ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ አመልክቷል።

ተጠርጣሪዎቹ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችን የግድያ ዒላማ በማድረግ፤ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በመናድ የክልሉን መንግሥታዊ መዋቅር በመቆጣጠር የፌደራል መንግሥትን ለመጣል በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ተደራጅተው እና ተቀናጅተው በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ እንደተደረሰባቸው አስታውቋል።

ግብረ-ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ፤ መንግስት የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት እና ለሐሳብ ትግል ሰፊ ዕድል በመስጠቱ እንዲሁም ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ባደረገው ጥረት ብዙዎች ይሄንን ዕድል መጠቀማቸውን አስታውሷል።

ይሁንና የአማራን ህዝብ የማይወክሉ እነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎች የመንግሥትን ሰላማዊ አማራጭ በመግፋት በውጭ ከሚገኙ ግብረ-አባሮቻቸው ጋር በህቡዕ በመገናኘት የፖለቲካ፣ የወታደራዊ፣ የኢንተለጀንስ፣ የሚዲያ እና የፋይናንስ ክንፍ ማቋቋምቸው እንደተደረሰበት መግለጫው አመልክቷል።

የጋራ ግብረ-ኃይሉ መግለጫ እንዳመለከተው፤ የጽንፈኛ ኃይሎችን የፖለቲካ፣ የወታደራዊ፣ የኢንተለጀንስ፣ የፋይናንስ እና የሚዲያ ክንፍ የሚመራው ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ የተባለ ግለሰብ ሲሆን፤ ይህ ክንፍ በተለያዩ የውጭ ሀገራት ከሚገኙ 16 ጽንፈኛ የዲያስፖራ አባላት ጋር ትስስር በመፍጠር በሚያገኛቸው የሎጀስቲክስ እና የፋይናንስ ድጋፎች በአማራ ክልል ከባህርዳር ከተማ ጀምሮ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ታጣቂዎችን የመመልመል፣ የማሰልጠን፣ የማስታጠቅና የማሠማራት ተግባር በማከናወን በክልልና በፌደራል ደረጃ ሽብር እና ግድያ እንዲፈጽሙ ተልዕኮ ሲሰጥ እንደነበር በተደረገ ክትትል እና ምርመራ ተደርሶበታል ብሏል መግለጫው።

ለዚህም በለጠ ሸጋው እና ምሕረት ወዳጆ ወይም በቅጽል ስሙ ምሬ ወዳጆ በተባሉት የጽንፈኛ ኃይሉ ታጣቂ መሪዎች እና ግብረ-አባሮቻቸው ሰሞኑን በትውልድ በቀኤአቸው ግፍና ጭካኔ በተሞለበት አኳሃን የተገደሉት የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ እና የጥቃት ሰለባ የሆኑ የሥራ ባልደረቦቻቸው ማሳያ ናቸው ብሏል የጋራ ግብረ-ኃይሉ መግለጫ።

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ አክሎም፤ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሚገኙ እነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎች በፈጠሩት ህቡዕ አደረጃጀት እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈጸም በአማራና በሌሎች አካባቢዎች በሚገኙ 130 ወረዳዎች የመለመላቸውንና በህቡዕ ያዘጋጇቸውን 450 ግለሰቦች የአማራ ክልል ህዝብ የመረጣቸውንና በተለያዩ የአመራር እርከኖች ላይ ያስቀመጣቸውን በኃይል በማስወገድ በራሳቸው መዋቅር የመተካት ሥራ ሲሰሩ እንደነበር በክትትል እና በምርመራ የተደረሰባቸው መሆኑን አስታውቋል።

በተጨማሪም ጽንፈኛ ኃይሎች የክልሉን የፀጥታ ኃይልንም በራሳቸው ታጣቂዎች ለመቀየር ተዘጋጅተው እንደነበር የተገኛው መረጃ ማመላከቱን ገልጿል።

ዶ/ር መሥፍን ኃ/ማርያም፣ ዶ/ር ግሩም ላቀውና ሌሎችም በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚኖሩ የጽንፈኛ ኃይሉ ተባባሪዎች ከውጭ ሆነው የፖለቲካ ክንፉን እንደሚያስተባብሩ፤ አንተነህ ብርሃን፣ ወርቁ ጓዴና ሌሎችም ከሀገር ውስጥና ከውጭ የሚላከውን ገንዘብ እንዲቀበሉና ለሽብር ተልዕኮ ማስፈፀሚያ እንዲያውሉ የባንክ አካውንት እንደተከፈተላቸው በክትትልና በተደረገው ምርመራ መረጋገጡን የገለፀው የጋራ ግብረ-ኃይሉ መግለጫ፤ ቴዎድሮስ አስፋውን ጨምሮ ሌሎችም በዚሁ የሽብር እንቅስቃሴ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን መግለጫው አስታውቋል።

መግለጫው አያይዞም የእነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎችን የሚዲያና ፕሮፓጋንዳ ክንፍ የሚመራው መስከርም አበራ በተባለች ግለሰብ መሆኑን ጠቅሶ፤ በዚህ ህቡዕ አደረጃጀት ውስጥ ከሀገር ውስጥ ዳዊት በጋሻው የተባለ ግለሰብ እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ ሀገራት ደግሞ ከኢትዮ 360 እና መረጃ ቲቪ ሀብታሙ አያሌው፣ ምንአላቸው ስማቸው፣ ብሩክ ይባስ እና እየሩሳሌም ተ/ፃዲቅ በተጨማሪም ዘመድኩን በቀለ እና ልደቱ አያሌው ከአንከር ሚዲያ መሳይ መኮንን እንዲሁም ሌሎች ግለሰቦች የዚህ እኩይ ዓላማ አስፈፃሚ አባላት መሆናቸውን በምርመራ መረጋገጡን ገልጿል።

እነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎች የሀሰት ወሬዎችን በመፍጠር እና ከፍተኛ የሽብር ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ህዝቡን በብሄር እና በሀይማኖት በመከፋፈልና በማጋጨት የክልል እና የፌደራል መንግሥትን በኃይል ለመጣል እንዲሁም ሀገሪቱ ከጀመረችው የለውጥና የልማት መንገድ ወጥታ ወደ ለየለት ሁከትና ትርምስ እንድትገባ በህቡዕ ተደራጅተው እየሠሩ መሆናቸውን የገለፀው የጋራ ግብረ ኃይሉ፤ በሀገር ውስጥና በውጭ ሆነው በሀሰት ሀገር ለማፍረስ የሚሰሩ እነዚህን ጨምሮ ሌሎችም በህቡዕ አደረጃጀቱ ውስጥ ያሉ ግለሰቦችም ጭምር በሽብርተኝነት ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን መግለጫው አመልክቷል።

እነዚህ የሽብር ኃይሎች ከሚኖሩባቸው ሀገራት በአለም አቀፍ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) እንዲሁም እነሱ ከሚኖሩባቸው ሀገራት መንግሥት የፀጥታ እና የደኅንነት ተቋማት ጋር በተመሠረቱ የትብብር ማዕቀፎች አማካኝነት ወደ ሀገር ቤት ተላልፈው እንዲሰጡ በህግም እንዲጠየቁ እየሰራ መሆኑን እና ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ አክሎም፤ እነዚህ ውጭ ሀገር የሚኖሩ ተፈላጊዎች ከውጭ ሀገር በሚያገኙት እና በሀገር ውስጥ ያላቸውን ሀብት ተጠቅመው ለዚህ እኩይ ተግባር እያዋሉ መሆኑን በምርመራ የተደረሰበት ስለሆነ በሀገር ውስጥ ያላቸውን ሀብት የመለየት እና በህግ የመቆጣጠር ስራ እየተሰራ መሆኑንም ጭምር አስታውቋል።

ሕገ-መንግሥቱንና ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ እየተንቀሳቀሱ የነበሩ እነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎች የኢትዮጵያን አንድነት ከማይፈልጉ የውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር ተቀናጅተው መንግሥትን በኃይል ለማስወገድ ሲሰሩ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው የሚገኝ መሆኑን ያመለከተው የጋራ ግብረኃይሉ መግለጫ፤ ኅብረተሰቡ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚወሰደውን እርምጃ ከትጥቅ ማስፈታት ጋር በማያያዝ ውዥንብር ለመፍጠርና የተሳሳተ መረጃ ለማሰራጨት ከሚጥሩ አካላት ራሱን እንዲጠብቅ በጋራ እንዲታገል ጥሪ አቅርቧል።

በመጨረሻም የተጀመረው ህጋዊ ኦፕሬሽን ከግቡ እንዲደርስ ህብረተሰቡ እያደረገ ላለው ከፍተኛ ተሳትፎ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ምስጋና እያቀረበ፤ በህግ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ጥብቅ ክትትል እየተደረገባቸው ያሉ ተፈላጊዎችን ካሉበት ጠቁሞ እንዲያሲዝ በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን እያቀረበ በቀጣይ የምንደርስበትን ውጤት ለህዝብ እየገለፀ እንደሚሄድ ያስታውቃል።

የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል
11.4K views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 21:25:33 አሁን የደረሰን ዜና!

በአማራ ክልል ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ሚያዚያ ቀን 20/2015 ዓ.ም

በአማራ ክልል ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ ፡፡

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠው መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

~~\\~~

በአማራ ክልል ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ለአማራ ህዝብ እንታገላለን በሚል በውስጥም በውጭም በመቀናጀት የራሳቸውን ህቡዕ አደረጃጀት የፈጠሩ አካላት ከመሰል ቡድኖች ጋር በመቀናጀት የህዝቡን የቁርጥ ቀን ልጆች መልሰው እየበሉ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ፅንፈኛ ኃይሎች በትናንትናው ዕለትም የአማራ ክልል ብልፅግና ጽ/ቤት ሓላፊ እና የክልሉ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነውን ግርማ የሺጥላን በመግደል አስነዋሪ ድርጊታቸውን አሰመስክረዋል፡፡

ይሄንን እኩይ የጥፋት ሴራ እየፈፀሙ ያሉ ፅንፈኛ ኃይሎች የአማራ ህዝብ የልማትና የሰላም ተጠቃሚ እንዳይሆንና የተረጋጋ ህይወት እንዳይኖረው እንዲሁም በመንግስት የሚወሰኑ ውሳኔዎች እንዳይተገበሩ እንቅፋት ሲፈጥሩ መቆየታቸውን የጋራ ግብረ ኃይሉ መግለጫ አመልክቷል፡፡

በየአካባቢው የተደረጉ የሽምግልና ሂደቶችን በመግፋት እንዲሁም የተቀበሉ በመምሰል በህቡዕ ተደራጅተውና ተቀናጅተው ሕገወጥ ተግባራቸውን መቀጠላቸውን አስታውቋል፡፡

በአማራ ክልል ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በማፍረስም ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠርም ሲጥሩ መቆየታቸውን ጠቅሷል፡፡ የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይልም ይህን ተከትሎ አስፈላጊና ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ጠቁሟል፡፡

ይሄ ጽንፈኛ ሀይል በአማራ ክልል ሳይገደብ እንደ ሀገርም መንግስትን በኃይል ከስልጣን ለማስወገድ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም ያለው የጋራ ግብረ ኃይሉ መግለጫ፤ ከዚህ የጥፋት መንገዳቸው እንዲመለሱ በተደጋጋሚ የተሰጣቸውን እድል ከመጠቀም ይልቅ አሁንም በሕግወጥ ተግባራቸው መቀጠላቸውን አመልክቷል፡፡

በዚህ ህግወጥ ተግባራቸውም በቁጥጥር ስር ዉለው ጉዳያቸው በህግ
እየታየ የሚገኙ በርካታ የቡድኑ አባላት መኖራቸውንም ግበረ ሃይሉ አስታውቋል፡፡

መንግስት በሃገሪቱ ብሎም በክልሉ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሓላፊነት ያለበት በመሆኑ በሌሎቸም የሕገውጥ ቡድኑና ቡድኑን በገንዘብና በሀሳብ በህቡእ በሚደግፉ አካላትና ግለሰቦች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ የፅንፈኛ ቡድኖቹ ደጋፊዎች በዚህ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ ላይ የተፈፀመውን ግድያ ከመኮነን ይልቅ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ገዳይ ቡድኖቹን ሲደግፉ ተስተውለዋል ብሏል መግለጫው፡፡

ሃሳብን በሃሳብ ከማሸነፍ ይልቅ ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት ባፈነገጠ መልኩ በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ የፈጸሙትን ፅንፈኛ ቡድኖች ህዝቡ በአንድነት በማውገዝ ኢትዮጵያዊ ጨዋነቱን ሊያስመሰክር ይገባልም ብሏል፡፡

በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የፅንፈኛ ኃይሎቹን ትክክለኛ መልክና ገፅታ ለህዝቡ በይፋ ያጋለጠ ነው ያለው የደኅንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ፤ መንግስት ለህዝቡ ሰላምና ደኅንነት መረጋገጥ ግዴታውን ለመወጣት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ የጀመረ በመሆኑ፤ ህዝቡም ይሄንን ተገንዝቦ የፌደራል እና የክልል የፀጥታ አካላት ተጠያቂነትን ለማስፈን የጀመሩትን እንቅስቃሴ ጥቆማና መረጃ በመስጠት እንዲደግፍ የጋራ ግብረ ሀይሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

መግለጫው አክሎም፤ የፅንፈኛ ሀይሎቹን አስነዋሪ ተግባር በመሸፋፈን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች መሰረተ ቢስ ወሬዎችን ከሚያሰራጩ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ህብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅ አሳስቦ፤ ግብረ ሀይሉ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በቀጣይ ለህዝቡ የማሳወቅ ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጧል፡
7.8K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 16:21:57
ማስታወሻ!

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ኤፍ ኤም 96.3 ሬዲዮ ከሚያዚያ 19/2ዐ15 ዓ.ም እኩለ ለሊት ጀምሮ በሚያደርገው የማሠራጫ ጣቢያ ማሻሻያ ምክንያት መደበኛው የኤፍኤም ሬዲዮ ስርጭት ይቋረጣል።

ለዚህም ውድ አድማጮቻችንን በቅድሚያ ይቅርታ እየጠየቅን፤ በበለጠ የተደራሽነት ስፋትና የስርጭት ጥራት ወደ አድማጮች ዳግም እስክንመለስ ስርጭቶቻችንን በሌሎች አማራጮች ማለትም በተከታዮቹ የዲጂታል ፕላትፎርሞቻችን ማዳመጥ የምትችሉ መሆኑንለመግለፅ እንወዳለን!!
በ ድረ ገፃችን www.amn.gov.et
በfacebook: www.facebook.com/amn96.3 እንዲሁም
:www.facebook.com/amnafaanoromoo
በሳተላይ አማራጭ NSS11105 Horizontal symbol rate 45000 ላይ መደበኛ እና የዜና ሰዓት መሰናዶዎችን መከታተል የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
4.7K views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 09:46:59
በሱዳን የሚገኙ ዜጎቿን በማስወጣት ህደት ኢትዮጵያ ላሳየችው አጋርነት አሜሪካን አመሰገነች

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ሚያዚያ 16/2015 ዓ.ም

የአሜሪካ የወቅቱ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እና የቀድሞ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ቲቦር ፒ.ናጊ በይፋዊ የትዊተር አድራሻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያ የአሜሪካ ዜጎችን ከሱዳን ካርቱም በማስወጣት በመከራ ወቅት እውነተኛ ወዳጅ መሆንዋን ስላሳየች አመስግነዋል።

የአሜሪካ መንግስት በሱዳን የሚገኙ ዲፕሎማቶችን በማስወጣት ሒደት የኢትዮጵያን መንግስት እና የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ላደረጉት ድጋፍም ምስጋና አቅርቧል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ የአሜሪካ ጦር በሱዳን የሚገኙ የዋሽንግተን ዲፕሎማቶች እና ቤተሰቦቻቸውን ለማስወጣት ባካሄደው ኦፕሬሽን ኢትዮጵያ ላደረገችው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ቲቦር ናዥ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካ በሱዳን የሚገኙ ድፕሎማቶችን በማስወጣት ሒደት ላደረገችው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

ኢትዮጵያ፥ አሜሪካ ችግር ሲያጋጥማት በተደጋጋሚ ጊዜ ድጋፍ በማድረግ የምትታወቅ እውነተኛ ወዳጅ ሀገር መሆኗን አውስተዋል፡፡

በአሜሪካ ውስጥ በተፈፀመው የመስከረም 11 የሽብር ጥቃት ወቅት ኢትዮጵያ ለዩናይትድ ስቴትስ ድጋፏን እና አጋርነቷን አሳይታ እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡
4.7K views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 11:33:38
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ነቀምት ከተማ ገቡ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )ሚያዝያ 11/2015 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ነቀምት ከተማ ገብተዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት ነቀምት ከተማ ሲገቡ አባ ገዳዎች ፥ሐደ ሲንቄዎች፣የሃይማኖት አባቶች፥አመራሮችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ደማቅ አቀባበል ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያሳያል::
5.9K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ