2023-02-02 17:51:20
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቅርቡ ለ4ኛ ዙር ሰልጣኞች ለሚሰጠው ስልጠና በሶስተኛው ዙር ስልጠና የነበሩ ገለዳዮችን ትምህርት ይሆኑ ዘንድ ሰልጣኞች ይወቁልኝ ብሎ ተከታዮቹን ሃሳቦች አቅርቧል፦
በሶስተኛው ዙር ስልጠና ምን ምን ጥንካሬ እና ድክመቶች ነበሩ? ከ4ኛው ዙር ሰልጣኞች ምን ይጠበቃል??
ጥንካሬዎች?
1. በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኖች እራሳቸው በእውቀትና እና በኢኮኖሚ ተቀይረው ሀገራቸውን ለመቀየር የፀና አቋም ያሳዩበት ነበር፡፡
2. ብዙዎች በሚያስገርም ሁኔታ ንቁ ተሳታፊ ነበሩ፣ በጥያቄም በመልስም!
3. ብዙዎች ሰአት አክባሪ ነበሩ፣ መግቢያ ሰአትን አክብረው በስልጠና ማዕከላት ተገኝተዋል ከዛም ስልጠናው ሲጠናቀቅ ብቻ ወጥተዋል!
4. ብዙዎች በስልጠናው የኢትዮጵያ ልማት ባንክን የሊዝ ፋይናንሲንግ የብድር ስርአት ለመጠቀም ቅድመ ሁኔታ ስለሆነ ስልጠናውን ለመካፈል ሲሉ ብቻ የመጡ የነበረ ቢሆንም ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለማንኛውም በንግዱና በህይወቱ መቀየር ለሚፈልግ ሰው ስልጠናው ወሳኝ ክህሎትንና እውቀትን ማስጨበጫ መሳሪያ እንደሆነ እየመሰከሩ ስልጠናዎች ተጠናቀዋል።
5. በከፍተኛ ደረጃ እርስ በርስ መግባባትና መከባበር በሰልጣኖች መሀከል ዳብሮ ነበር፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በጋራ ለመስራት እድሉን ያገኙበትና እውቂያ የፈጠሩበት ሁኔታም ነበር፡፡
6. በአንዳንድ ስልጠና ማዕከሎች ሙቀት የነበረ ቢሆንም ተቋቁመው ስልጠናቸውን በፍላጎት ተከታትለዋል፡፡
7. በተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች፣ በአሰልጣኞች እና በባንኩ አስተባባሪዎች፣ እንዲሁም እጅግ ቁልፍ የሆኑ ጥያቄዎች በባንኩ ፕሬዚደንት አመርቂ መልስ የተሰጠበት ሁኔታ ነበር።
8. አራስ እናቶች እና ነፍሰ-ጡሮች በስልጠናው የተካፈሉበትና የበቁበት ሁኔታ ነበር፡፡
ድክመቶች?
1. አንዳንድ ሰልጣኞች በጣም እያረፈዱ መምጣት
2. አንዳንድ ሰልጣኞች ከስልጠና ማዕከሎች ጠፍቶ መሄድ
3. አንዳንድ ሰልጣኞች በስልካቸው ላይ ያለአግባብ እና ያለምክንያት በተደጋጋሚ እና ለረዥም ደቂቃዎች ማሳለፍ
4. አንዳንድ ሰልጣኞች ከስልጠናው አላማና ጭብጥ ውጪ ውይይቶችን በተሳታፊዎች መሀከል እንዲፈጠር ምክንያት መሆን
5. ከስልጠና መቅረት
6. አቴንዳንስ ላይ የሰውን ስም እያጠፉ/እየቀየሩ የራስን ስም ማድረግና መፈረም
7. ለሰው አስመስሎ ለመፈረም ሙከራ ማድረግ
8. በስልጠና ወቅት የውይይት ሰአት ሳይደለ ድምፅን አጉልቶ ከጎን ካለ ሰው ጋር ማውራት
9. በአንዳንድ ሰልጣኞች አማካኝነት ለስልጠና ከተመዘገቡና ከተጠበቁ ሰዎች ውጪ ሌሎች እንዲመጡ ማድረግና በተለይም በምግብና ሰዓት አካባቢ ያለአግባብ ግርግር መፍጠር
ማጠቃለያ፡
በነበሩ ጥንካሬዎች አማካኝነት የሚፈለገው እውቀትና ክህሎት ተጨብጧል፣ ግሩም የሆነ የእረስ በእርስና የንግድ ትስስር ለመመስረት ተሳታፊዎች በራሳቸው ተነሳሽት በራሳቸው መንገድ መሠረት ጥለዋል፣ በባንኩና በተሳታፊዎች መሀከል ለዘለቄታው ጠቃሚ መስተጋብር ተገንብቷል ፣ ሰልጣኞች ለሊዝ ፋይናንሲንግ ብድር ብቁ የሚያደርጋቸውን ሰርተፊኬት ተረክበው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል።
በድክመቶች ምክንያት በዋናነት የክስተቱ ምንጭ የነበሩ ሰዎች ከዚህ ውድ ዕውቀት መቋደስ አልቻሉም። ከስልጠና የጠፉና የቀሩ ደግሞ ለሰርተፊኬት ብቁ ባለመሆናቸው ምክንያት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግልታችን መጠቀም የሚገባቸውን ዕድል አምክነዋል።
4.3K views14:51