ቦቢ የተባለው ውሻ ለ30 ዓመታት መኖሩን ጊነስ ወርልድ ሪከርድ አረጋግጫለው አለ፡፡ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ.ኤም.ኤን) ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም የዓለማችን ትልቁ የ30 ዓመት ዕድሜ ያስቆጠረው ውሻ በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ ላይ ሊሰፍር መቻሉ ተዘግቧል፡፡ ቦቢ እ.ኤ.አ በ1992 የተወለደ ሲሆን ዕድሜውም 30 አመት ከ266 ቀን መሆኑን ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ ገልጿል። ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ በመግለጫው ፖርቹጋላዊው ውሻ ቦቢ ሪከርዱን የወሰደው ባለፈው ዓመት የአለማችን ትልቁ ውሻ ተብሎ ከተሰየመው ስፓይክ ከተባለ የ23 አመት ውሻ መሆኑ ተገልጿል። ቦቢ ዕድሜውን በሙሉ ኮንኬይሮስ በተባለች የፖርቹጋል ገጠራማ መንደር ውስጥ ከአሳዳጊዎቹ ጋር እንደሚኖር ታውቋል። ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን! YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9 Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8 Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጥር 26/2015 ዓ.ም 5.3K views11:19