Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ዛሬ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ላይ ያበቃ | AMN-Addis Media Network

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ዛሬ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ላይ ያበቃል: - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) ጥር 26/2015 ዓ.ም

የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ዛሬ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት የሚያበቃ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ቀድመው ቅሬታ ያቀረቡ ተፈታኞች የቅሬታቸውን መልስ www.neaea.gov.et:8081 ድረ ገጽ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን (Registration Number/ID) ብቻ በማስገባት ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

የቀረቡ ቅሬታዎች ተጣርተው ሲጠናቀቁ የቅሬታዎቹን ምላሽ በቀጣይ ቀናት የሚያሳውቅ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጾ፤ የቅሬታ ምላሽ ያልደረሳችሁ ተፈታኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ አሳስቧል።

በተመሳሳይ ያልተሟላ ወይም የተሳሳተ ወይም የሌላ ሰው መለያ ቁጥር በመጠቀም ቅሬታ ያቀረቡ ተፈታኞች የስም ዝርዝራቸውን ዛሬ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገጽ ላይ በመመልከት ቅሬታቸውን በትክክለኛ መለያ ቁጥራቸው በድጋሚ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑንም መገለጹን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡