Get Mystery Box with random crypto!

AMN-Addis Media Network

የቴሌግራም ቻናል አርማ addismedianetwork — AMN-Addis Media Network A
የቴሌግራም ቻናል አርማ addismedianetwork — AMN-Addis Media Network
የሰርጥ አድራሻ: @addismedianetwork
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.65K
የሰርጥ መግለጫ

This is an official Telegram channal for Addis Media Network (AMN) We trive to be the prime informer of issues. Hence, our motto says so, 'first to inform'
ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ !!
contact us via:- E-mail:- addisaammaa@gmail.com
twitter.com/AmnAddis

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-03-25 22:29:13

5.7K views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 14:20:00 ማስታወቂያ!!
የ4ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤቶች ጨረታ አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡ ተጫራቾችን ስም ዝርዝር በቀጣዩ የቴሌግራም ቻናል ማግኘት ይችላሉ። ቻናሉን በመቀላቀል መረጃውን ያግኙ!!
7.4K viewsedited  11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 12:24:35
አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት አስታወቀ፡፡

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የኢፌዴሪ የፌዴሬሸን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 (9) እና በአዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀፅ 14/2/ለ/ መሠረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት፣ እንዲሁም በኢፌዴሪ መንግስት እና በህወሓት መካከል ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና ግጭትን ለማስቆም በፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪካ በተደረገው የሰላም ስምምት አንቀጽ (10)መሰረት አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋም አስፈልጓል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት መጋቢት 9 ቀን 2015 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ “የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር ደንብን ማጽደቁ ተመላክቷል፡፡

በዚሁ ደንብ አንቀጽ 3(2) መሰረት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቶ ጌታቸው ረዳን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተ ዳደር አድርገው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት አስታውቋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ በከልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎችን ውክልና የሚያረጋገጥ እና አካታች የሆነ አስተዳደር በማዋቀር የክልሉን አስፈጻሚ አካል የመምራት እና የማስተባበር ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
5.0K views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 12:34:05
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ - ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሰረዝ ውሳኔ አሳለፈ

ምክር ቤቱ ዛሬ ባደረገው 1ኛ ልዩ ስብሳባው ህወሐትን ከሽብርተኝነት ስያሜ ለማንሳት የቀረበውውን የውሳኔ ሃሳብ የውሳኔ ቁጥር 12/2015 በ61 ተቃውሞ በ5 ድምፅ ታዕቅቦ በአብላጫ ድምፅ ማፅደቁን ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
4.8K views09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 10:10:31
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከላይ በተጠቀሱ ክፍት የስራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል።

አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃቸውን ዋናውንና የማይመለስ ቅጂ (ፎቶ ኮፒ) በመያዝ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
5.5K views07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 17:38:22
በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የተፃፈውን "የመደመር ትውልድ" መፅሀፍ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ እና ገቢ የማሰባሰቢያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መጋቢት 12/2015 ዓ.ም
በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የተፃፈውን "የመደመር ትውልድ" መፅሀፍ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ እና ገቢ የማሰባሰቢያ መርሀ ግብር በሸራተን ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በመርሀግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ፣የሀይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎችና ሀደሲንቄዎች፣ባለሀብቶች፣ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የመደመር ትውልድ መጽሀፍ በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች መዘጋጀቱ ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ክልሎች ከመፅሐፉ ሸያጭ የሚያገኙትን ገቢ ሙሉ በሙሉ የተለያዩ የትውልድ ግንባታ እና የታሪክ ማቆየት ስራዎች ላይ እንዲያውሉ መፍቀዳቸው ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎም የኦሮሚያ ክልል በመጽሀፉ ሽያጩ የሶፍዑመር ዋሻን ለጎብኚ ምቹ ለማድረግ፣ 348 ገጽ የያዘውን Dhaloota IDA'AMUU መጽሃፍ የማስመረቅና የሽያጭ መርሀግብር እያካሄደ ነው።

በዘለቃሽ ግርማ
870 views14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 21:32:04
5.3K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 21:29:47
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የመደመር ትውልድ መፅሐፍ የምረቃ ሥነ ስርዓት በፎቶ፦
5.4K views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 21:12:56
ባንኩ ያዘጋጀው ስልጠና የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጀምር አስታወቀ።

አዲስ ሚዲያ ኔትውርክ(ኤ ኤም ኤን)የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ያዘጋጀው ስልጠና የካቲት 14 ቀን 2015 እንደሚጀምር አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ከየካቲት 14 እስከ 18 ቀን 2015 ዓ .ም ድረስ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተር ፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጿል።

ስልጠናው በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 57 ከቸሞችና በ95 የስልጠና ማዕከላት ይሰጣልም ተብሏል።

በዚህ በ4ኛው ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና ከ1መቶ 12ሺህ በላይ ሰልጣኞች እንጀሚሳተፉም ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
2.5K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 11:20:54
ማስታወቂያ
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩ ክፍት የስራ መደቦች ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልገል።
4.0K views08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ