Get Mystery Box with random crypto!

ባንኩ ያዘጋጀው ስልጠና የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጀምር አስታወቀ። አዲስ ሚዲያ ኔ | AMN-Addis Media Network

ባንኩ ያዘጋጀው ስልጠና የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጀምር አስታወቀ።

አዲስ ሚዲያ ኔትውርክ(ኤ ኤም ኤን)የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ያዘጋጀው ስልጠና የካቲት 14 ቀን 2015 እንደሚጀምር አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ከየካቲት 14 እስከ 18 ቀን 2015 ዓ .ም ድረስ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተር ፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጿል።

ስልጠናው በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 57 ከቸሞችና በ95 የስልጠና ማዕከላት ይሰጣልም ተብሏል።

በዚህ በ4ኛው ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና ከ1መቶ 12ሺህ በላይ ሰልጣኞች እንጀሚሳተፉም ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።