Get Mystery Box with random crypto!

AMN-Addis Media Network

የቴሌግራም ቻናል አርማ addismedianetwork — AMN-Addis Media Network A
የቴሌግራም ቻናል አርማ addismedianetwork — AMN-Addis Media Network
የሰርጥ አድራሻ: @addismedianetwork
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.65K
የሰርጥ መግለጫ

This is an official Telegram channal for Addis Media Network (AMN) We trive to be the prime informer of issues. Hence, our motto says so, 'first to inform'
ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ !!
contact us via:- E-mail:- addisaammaa@gmail.com
twitter.com/AmnAddis

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-06-03 17:32:39 https://fb.watch/kX29ber2T-/?mibextid=RUbZ1f
9.6K views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 17:32:15 https://fb.watch/kX27MI432h/?mibextid=RUbZ1f
9.4K views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 11:07:38
#Update

ዛሬ ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ በኤፍ.ኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ

ማንችስተር ሲቲ ከ ማንችስተር ዩናይትድ

የሚያደርጉትን የዋንጫ ፍልሚያ በቀጥታ ስርጭት በስፖርት 96.3 ወደ እናንተ እናደርሳለን።

በተጨማሪም በተከታዮቹ የፌስቡክ፣ ቴሌግራም እና ዩቱብ ቻናሎቻችን በቀጥታ ስርጭት የጫወታ ትንተናዎችን እናቀርባለን!!
Join us here

YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr

Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9

Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8

የውጤት ግምቶቻችሁን በመልዕክት መቀበያችን 8288 እና በፌስቡክ ገፃችን አድርሱን።
ትክክለኛ ግምት ለሚያደርሱን አድማጮች ሽልማት አዘጋጅተናል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
11.1K viewsedited  08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 18:37:43 "መለኞቹ" የሚል ስያሜ የተሰጠው እና በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እውነተኛ የጀብድ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራ ፊልም ተመረቀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ግንቦት 23/2015 ዓ.ም

ፊልሙን የመረቁት የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ የፌደራል ፖሊስን ጨምሮ ጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት ያደረጉት ሪፎርም ሀገር ችግር ውስጥ በገባችበት ወቅት ውጤታማነቱ በተግባር የተረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል ።

ይህ ታሪክ በፊልም መልክ በአግባቡ ተሰንዶ ለህዝብ መቅረቡ እና ለቀጣይ ትውልድ መተላለፉ የሚያስመሰግን መሆኑንም ነው አቶ አገኘሁ የተናገሩት።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ሰራዊት በዘመናዊ መልክ በአዋጅ ተቋቁሞ ወደ ስራ ከገባ 80 አመታትን ቢያስቆጥርም በአሁኑ ወቅት የደረሰበትን የቴክኖሎጂ እና የወንጀል መከላከል ደረጃ ለህዝብ ለማስተዋወቅ ታቅዶ ፊልሙ መሰራቱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በማስጠበቅ እና ወንጀልን በመከላከል ረገድ በየዘመናቱ የነበሩ የፖሊስ አባላት መስዋዕትነትን በመክፈል ጭምር በርካታ ተግባራትን ማከናወናቸውን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ እነ ኔልሰን ማንዴላን በማሰልጠን ለአፍሪካ ነጻነት አስተዋጽኦ ያበረከተ ፣ ለአፍሪካ ህብረት ምስረታ የተሳተፈ ፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስር ለአለም ሰላም መከበር አስተዋጽኦ እያበሰከተ ያለ እና ለጎረቤት ሀገራት ፖሊስ ጭምር የአቅም ግንባታ ስልጠናን እየሰጠ ያለ አካል ቢሆንም ይህ ሁሉ ታሪኩ ግን እስካሁን በተደራጀ መልክ ሲተዋወቅ አለመቆየቱን ነው የተናገሩት።

ፊልሙ ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ ፌደራል ፖሊስ የደረሰበትን የብቃት ደረጃ እና የሀገርን ሰላምና ጸጥታ አደጋ ላይ የሚጥሉ የወንጀል ድርጊቶችን እንዴት እየተከላከለ እንደሚገኝ የሚያሳይ የኢትዮጵያ ፖሊስን እውነተኛ የጀብድ ታሪክ ላይ የተመሠረተ የመጀመሪያው ፊልም መሆኑንም ነው ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል የተናገሩት።

በሰብስቤ ባዩ
12.8K views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 12:38:22
ማንችስተር ሲቲ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

ፕሪሜይር ሊጉን ለበርካታ ሳምንታት በአንድኝነት ሲመራ ቆይቶ በተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት በማስተናገድ መሪነቱን ለማንቸስተር ሲቲ ያስረከበው አርሰናል ትናንት ምሽት ከበርኒጋምፎረስት ጋር በነበረው ጨዋታ 1፡0 መሸነፉን ተከትሎ ነው ሲቲ በሊጉ ቀሪ ሶስት ጨዋታዎች እያሉት የዋንጫ ባለቤት መሆን የቻለው፡፡

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት ማንችስተር ሲቲዎች የ2022/23 የውድድር ዓመት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆን በመቻላቸውም የሊጉን ዋንጫ ለሶስት ተከታታይ ዓመት የሊጉ ሻምፒዮናነትን ሲያሸንፍ በክለቡ ታሪክ ዘጠነኛው ሆኗል።

በተያያዘ ዜና፣ ፔፕ ጋርድዮላ አዲስ ታሪክ ፅፈዋል።

ስፔናዊው የማንችስተር ሲቲ ዋና አሰልጣኝ ከሲቲ ጋር ለሶስተኛ ተከታታይ ዓመት የሊጉን ዋንጫ ማሳካታቸውን ተከትሎ ቀዳሚው አሰልጣኝ በመሆን ታሪክ ፅፈዋል።

አሰልጣኙ ከሶስት የተለያዩ ክለቦች ጋር ለተከታታይ ሶስት ዓመታት የሊግ ዋንጫዎችን በማሳካት አዲስ ታሪክ ማስመዝገባቸው ተዘግቧል።

በዚህም መሰረት :-

ባርሴሎና :- 2009 - 2010 - 2011 የውድድር ዓመት

ባየር ሙኒክ :- 2014 - 2015 - 2016 የውድድር ዓመት

ማንችስተር ሲቲ :- 2021 - 2022 - 2023 የውድድር ዓመት ላይ የሊግ ዋንጫውን ከተለያዩ ክለቦች ጋር አሳክተዋል።
21.2K views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 08:29:12

5.9K views05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 11:05:58
#update!

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ከ ሪያል ማድሪድ የሚያደርጉትን ተጠባቂ ፍልሚያ በ FM 96.3 ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡

ይህንን አጓጊ ጨዋታ ከምሽቱ 3፡30 ጀምሮ እንድትከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን!!

የጨዋታ ግምቶቻችሁን በ 8288 የመልዕክት መቀበያ አድራሻችን አድርሱን በትክክል የገመቱ አድማጮች የሞባይል ካርድ ሽልማት አዘጋጅተናል፡፡

አዲስ ሚዲየ ኔትዎርክ
7.6K views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 15:27:09
#update!

ዛሬ "በአዲስ ሜዳ" የቀጥታ የእግር ኳስ ስርጭት በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ኢንተር ሚላን ከ ኤሲ ሚላን የሚያደርጉትን ተጠባቂ ግጥሚያ በ FM 96.3 ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡

የተከበራቹ አድማጮቻችን ይህን የደርቢ ጨዋታ ከምሽቱ 3፡30 ጀምሮ እንድትከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛቹሃለን፡፡ የጨዋታ ግምቶቻችሁን በ 8288 የመልዕክት መቀበያ አድራሻችን አድርሱን በትክክል የገመቱ አድማጮች የሞባይል ካርድ ሽልማት አዘጋጅተናል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ!
8.5K views12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 08:40:31

8.5K views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 22:04:46 ከፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ተባብሮ በመሥራት የሽብር ተግባር ፈፅሟል በሚል ሲፈለግ የነበረው ጎበዜ ሲሳይ የተባለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በአማራ ክልል ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማፍረስ ከፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ተባብሮ በመሥራት የሽብር ተግባር ፈፅሟል በሚል ሲፈለግ የነበረው ጎበዜ ሲሳይ የተባለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ግለሰቡ አምልጦ ጅቡቲ ከገባ በኋላ ወደሌላ አገር ሊሻገር ሲል ከዓለም አቀፉ ፖሊስ እና ከጅቡቲ መንግሥት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውል እና ተላልፎ ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ ተደርጎ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ መግባቱን የፌዴራል ፖሊስ ገልጿል።

በአማራ ክልል ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ሥልጣንን በኃይል ለመያዝ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት በህቡዕ ተደራጅተው እና ተቀናጅተው በሚንቀሳቀሱ ፅንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም ሕጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ሚያዚያ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።

በዚህ መሠረትም፦

1. ሀብታሙ አያሌው፣
2. ምንአላቸው ስማቸው
3. ብሩክ ይባስ እና
4. እየሩሳሌም ተ/ፃዲቅ
5. ዘመድኩን በቀለ
6. ልደቱ አያሌው
7. መሳይ መኮንን
8. ጎበዜ ሲሳይ
9. ምህረት ወዳጆ (ምሬ ወዳጆ)
10. በለጠ ጋሻው እና
11. ሙሉጌታ አንበርብር የተባሉት ተጠርጣሪዎች በፈፀሙት የሽብር ተግባር እንደሚፈለጉ እና ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት ኢንተርፖል ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል ለሕግ እንደሚቀርቡ የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ማሳወቁ ይታወሳል።

ከነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከልም ጎበዜ ሲሳይ ዘገየ የተባለው ግለሰብ፣ በአማራ ክልል ቆቦ አካባቢ የፅንፈኛ ታጣቂ ኃይሎችን በማደራጀት፣ በቅርቡም በጽንፈኞች ግድያ የተፈጸመበትን የአቶ ግርማ የሺጥላን ግድያ በማስተባበር ሚና እንደነበረው፣ በመከላከያ እና በሕዝቡ ላይ ፅንፈኞች ጥቃት እንዲያደርሱ በማደራጀት እና ቃል አቀባይ ሆኖ በማስተባበር የሽብር ተግባር ውስጥ በመሳተፍ ተጠርጣሪ በመሆን ሲፈለግ ቆይቷል።

ግለሰቡ አማራ ክልልን በማሸበር እና ሥልጣንን በኃይል በመቀማት በቀጣይም የፌዴራል መንግሥትን ለማፍረስ ሲንቀሳቀስ ከነበረ ፅንፈኛ አካል ጋር በመተባበር ሲሠራ እንደነበር በመጠርጠሩ፣ ግለሰቡን ጨምሮ ሌሎች በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ የጋራ ግብረ ኃይሉ ከኢንተርፖል ጋር ባለ ስምምነት መሠረት ሲሠራ መቆየቱን ገልፆ ነበር።

በዚሁ መሠረትም አስፈላጊውን ፎርማሊቲ እና አግባብ ያላቸው መረጃዎችን በማደራጀት ጎበዜ ሲሳይ የተባለው ግለሰብ አምልጦ ጅቡቲ ከገባ በኋላ ወደሌላ አገር ሊሻገር ሲል ከዓለም አቀፉ ፖሊስ እና ከጅቡቲ መንግሥት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውል እና ተላልፎ ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ ተደርጎ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብቷል።

የፀጥታ እና የጋራ ግብረ ኃይል አሁንም ኢትዮጵያ ባላት ስምምነት መሠረት ሌሎች ያልተያዙ የሽብር ቡድኑ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሠራ መሆኑን ለኢዜአ ገልጿል።
9.5K views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ