Get Mystery Box with random crypto!

አድስ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ adszena — አድስ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ adszena — አድስ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @adszena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.34K
የሰርጥ መግለጫ

ወቅታዊ፣ ጠቃሚ እና እንገብጋቢ መረጃወችን ከስር ከስር ለመከታተል የዚህ ቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ ሆኑ!
ይጫኑ @adszena
Welcome to addis zena latest Ethiopian news channel you will get trust, usfull and latest news in and around the globe! STAY TUNED WITH ADDIS ZENA👍
@adszena

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 23:06:53 የሀሙስ ዉሎ መርጃዎች

1፤ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኤርትራ ኃይሎች በሰሜናዊ ትግራይ በአራት አቅጣጫ የተቀናጀ ወታደራዊ ጥቃት ከፍተውብኛል ሲል ሕወሃት መክሰሱን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል። ሆኖም ሮይተርስ የሕወሃትን ክስ በገለልተኛነት ማረጋገጥ እንዳልቻለ ገልጧል። አንድ ሺሬ ከተማ ያሉ የረድዔት ድርጅት ባልደረባ ግን ሺራሮ ከተማ አካባቢ ትናንት ድንበር ዘለል የመድፍ ድብደባ መኖሩን ከአካባቢው ከሄዱ እማኞች መስማታቸውን እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል። ሮይተርስ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግሥታት ቃል አቀባዮች በሕወሃት ክስ ዙሪያ ላነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንዳልሰጡት ገልጧል።

2፤ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ የመንግሥት የሰላም በሮች ክፍት መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ መንግሥት የዜጎቹን ደኅንነት የመጠበቅ ግዴታውን መወጣት ይቀጥላል ሲሉ ዛሬ ለውጭ ዲፕሎማቶች በሰጡት ማብራሪያ ተናግረዋል። ሕወሃት ተኩስ አቁሙን በመጣስ "በግጭት ቀስቃሽ ፕሮፓጋንዳ፣ ሕዝብን ለጦርነት በማንቀሳቀስ እና ሕጻናትን ለውጊያ በመመልመል" ተሰማርቶ ቆይቷል ያሉት ደመቀ፣ አሁንም "መንግሥትን በሐሰት በመወንጀልና በማጥላላት እና የሐሰት የውጊያ ድል በመንዛት ስልቶች" ላይ ተጠምዷል በማለት ከሰዋል። ደመቀ በዚሁ ማብራሪያቸው፣ "አንዳንድ ወገኖች መንግሥትን እና ሕወሃትን በእኩል ዓይን ከማየት እና ግጭቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ" አሳስበዋል።

3፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ሕወሃት የከፈተውን ወታደራዊ ጥቃት የሚከላከለው የትግራይ "ሕዝብን ከርሃብ የማዳን ግዴታ ስላለበት ነው" ሲል የመንግሥት ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። መንግሥት ሰብዓዊ ዕርዳታ ለትግራይ ሕዝብ እንዲደርስ እና ሕዝቡ ከችጋር እንዲወጣ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት መግለጫው አውስቷል። ሕወሃት የመንግሥትን ተደጋጋሚ የሰላም ጥረቶች በገፋበት ሁኔታ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ቡድኑ ላይ ጫና በማሳደር ፋንታ፣ "ሁለቱ ወገኖች በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ተቀባይነት የላቸውም ብሏል መግለጫው። "መከላከያ ኃይላችን በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተበትን ወረራ" መመከት እንደሚቀጥል መግለጫው አረጋግጧል።

4፤ የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕወሃት ባስቸኳይ ጦርነቱን እንዲያቆሙ በትዊተር ገጻቸው ጠይቀዋል። የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚንስትር ቪኪ ፎርድ በበኩላቸው፣ ሕወሃት በኃይል ከያዛቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች እንዲሁም የኤርትራ ሠራዊት የትግራይ ከሆኑ ይዞታዎች ለቀው ይውጡ በማለት ዛሬ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል። አዲስ ያገረሸው ግጭት በሚያስከትለው ሰብዓዊ ቀውስ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች እንደሚጎዱና የሰብዓዊ ዕርዳት አቅርቦት ችግሩንም እንደሚያወሳስበው ሚንስትሯ ጠቁመዋል። ሚንስትሯ ሕወሃት በእጁ ያለውን ነዳጅ ለሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራ እንዲያውለውና መንግሥትም ለትግራይ የተቋረጡ መሠረተ ልማቶችን እንዲያስጀምር ጭምር ጠይቀዋል።

5፤ ብሄራዊ ባንክ በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ የተበላሹ ብድሮችን ከባንኮች የፋይናንስ ወይም ኦዲት ሪፖርት ላይ አላነሳም ማለቱን ሪፖርተር አስነብቧል። ልማት ባንክና አንዳንድ ንግድ ባንኮች በተለይ ለትግራይ ተበዳሪዎች ያበደሯቸውን የተበላሹ ብድሮች ብሄራዊ ባንክ ለጊዜው ከሒሳብ ሪፖርታቸው እንዲያነሳላቸው ጠይቀው ነበር። ብሄራዊ ባንክ ግን፣ ጥያቄው "በሒሳብ አያያዝ ሕግ ያልተደገፈ ነው" ሲል ለባንኮቹ ምላሽ መስጠቱን ዘገባው አመልክቷል። ልማት ባንክ ብቻ በትግራይ ክልል 10 ቢሊዮን ብር ብድር ተበላሽቶብኛል ያለ ሲሆን፣ የባንኩ የተበላሸ ብድር ምጣኔም 24.3 በመቶ ደርሷል።

6፤ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዛሬ በሐረሬ ክልል መጠነ ሰፊ የሞባይል ስልክ አገልግሎት ሙከራ መጀመሩን አስታውቋል። ላንድ ወር በሚቆየው ሙከራ፣ በክልሉ የሚገኙ ደንበኞች በገዟቸው የሳፋሪኮም ሞባይል ስልክ ቁጥሮች የድምጽና የጽሁፍ መልዕክት ወደ ሳፋሪኮምና ኢትዮ ቴሌኮም ስልክ ቁጥሮች መላላክ እንደሚችሉ ኩባንያው ገልጧል። ኩባንያው ደንበኞች የኢንተርኔት አገልግሎት እና ዓላማቀፍ ጥሪዎችን ጭምር መሞከር ይችላሉ ብሏል። የኩባንያው የሐረሬ ክልል የአገልግሎት ሙከራ ከድሬዳዋ ቀጥሎ ሁለተኛው ነው።
350 viewsMAK story, 20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 23:06:49 "ጦርነት ቆሞ የሰላም ሂደቱ ይቀጥል"

በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ዳግም ያገረሸው ግጭት ተባብሶና ሰፍቶ እየቀጠለ ባለበት በዚህ ወቅት መሳሪያ ወርዶ ወደ ንግግር እንዲገባ እና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሚቀርቡ የሰላም ጥሪዎች ቀጥለዋል።

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ" ጦርነት ቆሞ የሰላም ሂደቱ ይቀጥል" ሲል የሰላም ጥሪ አቅርቧል።

ጉኤው ምን አለ?

- ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ሊቆምና የሰላም ሂደቱ ሊቀጥል ይገባል።

- የሰላም ቅድመ ሁኔታው ሰላም ብቻ በመሆኑ ጦርነቱን በማቆም ሰላማዊ ንግግሮች መቀጠል አለባቸው።

- ከዚህ ቀደም የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያደርጉ ቆይተዋል፤አሁንም የሰላም ጥሪ እናቀርባለን።

- የፌደራሉ መንግሥት ለሰላማዊ ንግግሮች ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ እንደገለጸው ሌሎችም ወገኖች ለዚህ ተግባር ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል።

- የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማትና ንጹኃን ዜጎች ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል።

- ህፃናትን ለወታደራዊ ዘመቻ ማሰለፍ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል የሚያስጠይቅና በሁሉም መመዘኛ ተገቢ ባለመሆኑ ሊቆም ይገባል።

-  በወቅታዊ ጉዳይ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል።

- ትግራይ ክልል የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች መሪዎች የትግራይ ክልል ወደ ሰላማዊ ድርድሩ እንዲመለስ በመምከር አባታዊና መንፈሳዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ እናቀርባለን።

- የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡና የውጭ ሀገራት መንግሥታት፣አፍሪካ ሕብረት፣ ተመድና ሌሎች አካላት ሁሉ የሰላም ጥረቱ አጋዥ እንዲሆኑ ጥሪ እናቀርባለን።

-  የጳጉሜን 5ቱን ቀናት ምእመናን በፆምና ፀሎት እንዲያሳልፉ ጥሪ እናቀርባለን።

(የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ)
340 viewsMAK story, 20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 08:35:32 1፤ በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች ማክሰኞ'ለት በትንሹ 55 ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል ሲሉ የዓይን ምስክሮች መናገራቸውን ጠቅሶ ዶይቸቨለ ዘግቧል። ታጣቂዎች ጥቃቱን ፈጸሙ የተባለው በዞኑ ኡሙሩ ወረዳ፣ አገምሳ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ነው። ታጣቂዎች በነዋሪዎች ላይ ግድያውን የፈጸሙት፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይሎች ከከተማዋ ዕሁድ'ለት መነሳታቸውን ተከትሎ ነው ሲሉ እማኞች ተናግረዋል። ነዋሪዎች ተፈጸመ ስላሉት ግድያ የአስተዳደር እና ጸጥታ ኃላፊዎች ያሉት ነገር የለም።

2፤ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በሰሜን ኢትዮጵያ በመንግሥት እና በሕወሃት መካከል ያገረሸው ጦርነት ለመምህራን ጥያቄ ምላሽ ለማስገኘት እንቅፋት እንደፈጠረበት ትናንት በሰጠው መግለጫ መናገሩን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። መምህራንና ተማሪዎች በጦርነቱ መፈናቀላቸውንና ትምህርት ቤቶች መውደማቸውን የጠቀሰው ማኅበሩ፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የሰላም ንግግር እንዲጀምር ጠይቋል። ለትግራይ ዕርዳታ ፈላጊዎች የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቱ እንዲቀጥልም ማኅበሩ ጥሪ አድርጓል።

3፤ የኢትዮጵያ መርከብ እና ሎጅስቲክስ ድርጅት በሰኔ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 3.6 ሚሊዮን ካርጎ በማጓጓዝ 3 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ሥራ አስኪያጅ ማሞ ምኅረቱ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል። የድርጅቱ ትርፍ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ121 በመቶ ብልጫ እንዳለው ማሞ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ያገኘው ትርፍ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ90 በመቶ እድገት እንዳለው ማሞ ጠቁመዋል።

4፤ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ራማፎዛ በአገራቸው በውጭ ዜጎች ላይ የተቃጣውን ተቃውሞ መንግሥታቸው እንደማይታገስ ለፓርላማው መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘግቧል። በፕሪቶሪያ "ዳዱላ" የተባለ በውጭ ፍልሰተኞች ላይ ያነጣጠረ አዲስ ንቅናቄ፣ ፍልሰተኞች እና የውጭ ዜጎች ሕክምና እንዳያገኙ ማገድ መጀመሩን መንግሥት ገልጧል። ንቅናቄው ዜጎች በሆስፒታሎች ለሚጠብቁት ረጅም ወረፋና ጥራት የለው ላሉት የሕክምና አገልግሎት ፍልሰተኞችን ተጠያቂ ያደርጋል። በአገሪቱ አራት ሚሊዮን የውጭ ዜጎች ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል።
137 viewsMAK story, 05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:24:24 አጫጭር መረጃዎች

በመንግሥት እና በሕወሃት መካከል ባገረሸው አዲስ ውጊያ ከአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከ30 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የተመድ ዋና ጸሃፊ ቃል አቀባይ ስቲፈን ዱጃሪች ትናንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። በአፋር ክልል እና ትግራይ ክልል አዋሳኞች አካባቢዎች በያሎ እና ገሊና ወረዳዎች እየተካሄደ ባለው ውጊያ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ስለመፈናቀላቸው ተመድ ሪፖርት እንደደረሰው ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። በአፋር እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ ጭፍራ ወረዳ ጭምር ነዋሪዎች ስለመፈናቀላቸው ሪፖርት ደርሶኛል ብሏል።

3፤ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በካርቱም የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮን ጠርቶ ማነጋገሩን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የሱዳን መንግሥት አምባሳደር ይበልጣልን ጠርቶ ያነጋገረው፣ አምባሳደሩ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሱዳን በኩል ጦር መሳሪያ ጭኖ ወደ ትግራይ የገባ አንድ አውሮፕላን መትቶ ጥሏል በማለት ሰኞ'ለት በካርቱም ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጋር በተያያዘ  ነው። ውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ የአምባሳደሩ መግለጫ ከአስተናጋጇ አገር ጋር ቀድሞ በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገር የሚጠይቀውን የዲፕሎማቲክ ደንብ የጣሰ ነው ብሏል።

4፤ ትናንት እኩለ ሌሊት በመቀሌ ተፈጸመ የተባለው የአየር ድብደባ የተፈጸመው በአይደር ሆስፒታል አካባቢ ነው ሲል ሮይተርስ የሆስፒታሉን ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል። ትናንት ተፈጸመ በተባለው የአየር ድብደባ ምን ጉዳት እንደደረሰ ግን የሮይተርስ ዘገባም ሆነ ሕወሃት አልጠቀሱም። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትም ለሕወሃት ውንጀላ ላይ ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም። የአየር ድብደባ ተፈጽሟል ሲሉ ሌሊት ላይ በትዊተር ገጻቸው የገለጡት የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ነበሩ።

5፤ ኦፌኮ በሰሜን ኢትዮጵያና ኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሱት ግጭቶች ሊፈቱ የሚችሉት ዘላቂ መፍትሄ በሚያመጣ እውነተኛና ሁሉን ዓቀፍ ድርድር ብቻ ነው ብሎ እንደሚያምን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በመንግሥት እና ሕወሃት መካከል ጦርነቱ በድጋሚ ማገርሸቱ በጦርነቱ አካባቢ ያሉ ሕዝቦችን ለዳግም ሞት እና መፈናቀል የሚዳርግ እንደሆነ ኦፌኮ ገልጧል። ኦፌኮ ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ግጭቱን አብርደው ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጥሪ አድርጓል። ኦፌኮ በኦሮሚያ ክልል በግጭትና ድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች የሰብዓዊ ሁኔታው አሳሳቢ መሆኑንም ጠቅሷል።

6፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 52 ብር ከ4617 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ5109 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 58 ብር ከ7334 ሳንቲም፣ መሸጫው 59 ብር ከ9081 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ52 ብር ከ6401 ሳንቲም ሲገዛ እና በ53 ብር ከ6929 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል።
427 viewsMAK story, 18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:26:01 የተመድ ዋና ፀሀፊ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ትላንት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተው የነበረ ሲሆን በመግለጫው ላይ የሰሜን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይን አንስተው ነበር።

ስቴፋን ዱጃሪች ምን አሉ ?

- በሰሜን ኢትዮጵያ አሁንም ግጭት መቀጠሉን እና አሁን ላይ ያለድ ሁኔታ ውጥረት የተሞላበት እንደሆነ ገልፀዋል።

- የአፋር ክልል ከትግራይ ጋር በሚዋሰንባቸው ቦታዎች ማለትም በያሎ እና ጉሊና ወረዳዎች እየተካሄደ ባለ ውጊያ ሳቢያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

- በአፋር እና አማራ አዋሳኝ ቦታ ጭፈራ ወረዳ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የሚገልፅ ሪፖርት መኖሩን አመልክተዋል።

- በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከሚገኘው የጃራ የተፈናቃዮች መጠለያ ተጠልለው የነበሩ 30 ሺህ ሰዎችም ለሁለተኛ ጊዜ ተፈናቅለዋል።  

- ዳግም ባገረሸው ግጭት ሰዎች እየተፈናቀሉ መሆኑ የሰብዓዊ መብት ፍላጎትን ይጨምራል ብለዋል።
566 viewsMAK story, 14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 09:36:59 አብይ ዜናዎች

1፤ ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ በመቀሌ ከተማ የአየር ድብደባ ተፈጽሟል ሲሉ የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል። በጥቃቱ ሦስት ቦምቦች እንደተጣሉ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል። ጌታቸው በከተማዋ ላይ ተፈጽሟል ባሉት የአየር ጥቃት በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ግን ያሉት ነገር የለም። በመንግሥት ኃይሎች እና በሕወሃት መካከል ግጭት በድጋሚ ካገረሸ ወዲህ፣ በመቀሌ የአየር ድብደባ እንደተፈጸመ ሕወሃት ሲገልጽ የአሁኑ ሁለተኛው ነው።

2፤ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተቀሰቀሰውን ጦርነት በመስጋት ወደ መርሳ፣ ኮምቦልቻ እና ደሴ ከተሞች ጉዞ ጀምረው የነበሩ አንዳንድ የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው መመለስ መጀመራቸውን ለዶይቸቨለ ተናግረዋል። የሰሜን ወሎ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ወልድያ እስከ ትናንት ምሽት መብራት፣ ስልክ እና የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዳልተቋረጠ እና በከተማዋ ቅርስ ርቀት ተኩስ እንደማይሰማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

3፤ የተመድ ሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ በመንግሥት እና በሕወሃት መካከል አዲስ ባገረሸው ጦርነት ሳቢያ ካለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለትግራይ ክልል ተረጅዎች ማቅረብ ማቋረጡን አስታውቋል። ቢሮው ያቋረጠው በየብስ ብቻ ሳይሆን በአየር ጭምር ሲያጓጉዝ የቆየውን ዕርዳታ እንደሆነ ገልጧል። ቢሮው በአማራ እና አፋር ክልሎች ነዋሪዎች ጦርነቱን በመስጋት ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ስለመሆኑ ያልተረጋገጡ ሪፖርቶች ደርሰውኛል ብሏል።

4፤ ሳፋሪኮም ኩባንያ በድሬዳዋ ለጀመረው የሞባይል አገልግሎት ለድምጽ በደቂቃ 50 ሳንቲም እንደሚያስከፍል ለአል ዓይን ኔትዎርክ በሰጠው ቃል ተናግሯል። የኢንተርኔት አገልግሎት ደሞ 120 ሜጋ ባይት በ10 ብር፣ 900 ሜጋ ባይት በ50 ብር እና ሁለት ጌጋ ባይት በ100 ብር ለደንበኞቹ እየሸጠ እንደሚገኝ ኩባንያው ገልጧል። ኩባንያው እስከ ቀጣዩ ዓመት ሚያዝያ ወር ድረስ የቴሌኮም አገልግሎቱን በ25 ከተሞች እጀምራለሁ ብሏል።

5፤ በደቡብ ሱዳን ሰላም ስምምነት መሠረት የአማጺዎች ተዋጊዎች ከመንግሥት ጦር ሠራዊት ጋር መቀላቀል መጀመራቸውን ዘግበዋል። ሰሞኑን ከ50 ሺህ በላይ የአማጺ ተዋጊዎች ከመንግሥት ጦር ሠራዊት ጋር ተቀላቅለዋል። አማጺያን በሰላም ትጥቅ ፈተው ከመንግሥት ሠራዊት ጋር በመዋሃድ አንድ ብሄራዊ ጦር ሠራዊት እንዲቋቋም ማድረግ ከአራት ዓመት በፊት የተፈረመው የሰላም ስምምነቱ ዋነኛ ግብ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስትር አብርሃም በላይ በስነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

6፤ የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ያሸነፉበት የአገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተጭበርብሯል በማለት ተሸናፊው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትሩ ራይላ ኦዲንጋ ያቀረቡትን አቤቱታ ትናንት መስማት ጀምሯል። ሰባት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች የተሰየሙበት ችሎት፣ የኦዲንጋ ጠበቆችን ከምርጫ ኮሚሽኑ እና ከዊሊያም ሩቶ ጠበቆች ያከራክራል። ችሎቱ በኦዲንጋ አቤቱታ ላይ በመጭው ሰኞ ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
337 viewsMAK story, 06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:55:44
ቅዱስ ፓትርያርኩ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን የሕክምና ክትትል በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ጤናቸውንም በተመለከተ የተወሰነ መሻሻል ማሳየቱ ታውቋል።

በመሆኑም ቀደም ሲል በተያዘው  የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
513 viewsMAK story, 18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:08:09
የሰላም ጥሪ ከትግራይ ሀይማኖት አባቶች

ለወራት ተቀዛቅዞ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆም ከትግራይ ክልል የሃይማኖት አባቶች የሰላም ጥሪ አቀረቡ። በድርድር ይቋጫል ተብሎ የታመነለት የመንግሥትና የህወሓት ዉዝግብ ዳግመኛ ጦርነት ማስነሳቱ ብዙዎችን ለመፈናቀል ብሎም ለሃገሪቱን ለዉድመት እየዳረገ ነዉ። ሁለቱ ወገኖች ወደ ጠረቤዛ እንዲመጡ ዓለም እየወተወተ ነዉ።

ምንጭ ጀርመን :- ድምፅ /DW AMHARIC
864 viewsMAK story, edited  19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:21:46 አጫጭር ዜናዎች

1፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መንግሥት እና ሕወሃት ግጭት አቁመው የሰላም ንግግር እንዲጀምሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አድርጓል። ኮሚሽኑ አፍሪካ ኅብረት፣ ተመድ፣ ሲቪክና የሐይማኖት ተቋማትና መገናኛ ብዙኀን ግጭቱ ባስቸኳይ እንዲቆም፣ ንግግር እንዲጀመርና በጦርነቱ ገፈት ቀማሽ ክልሎች የሰላማዊ ሰዎች ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርጉ ጠይቋል። ኮሚሽኑ ሁሉም ወገኖች የግጭቱ ተጎጅ የሆኑ ሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት፣ ደኅንነት፣ አካላዊ እና ሞራላዊ ሁኔታ እና የሰውነት ክብር እንዲያከብሩ ተማጽኗል።

2፤ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የተመድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ኮሚሽን መንግሥት እና ሕወሃት አዲስ ያገረሸውን ግጭት ባስቸኳይ አቁመው ንግግር እንዲጀምሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ኮሚሽኑ ረድዔት ድርጅቶች ለትግራይ የሚያቀርቡት ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲቀጥል መንግሥትና ሕወሃት ጥረት እንዲያደርጉ ተማጽኗል። በቅርቡ በመቀሌ በሙዓለ ሕጻናት ማዕከል ላይ ተፈጽሟል በተባለ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ስለመጎዳታቸው የወጡ ሪፖርቶችና ሰሞኑን በአማራ ክልል ቆቦ ከተማ በተካሄደ ማጥቃት ላማዊ ሰዎች ዒላማ ሆነዋል መባሉ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጧል።

3፤ ትናንት ለይፋዊ ሥራ ጉብኝት አልጀሪያ የገቡት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት አብዱልመጂድ ታቡኔ ጋር መወያየታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአልጀሪያው ፕሬዝዳንት ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር ዙሪያ መነጋገራቸውን ገልጸዋል። ዐቢይ ኢትዮጵያ እና አልጀሪያ ትብብራቸውን ሊያጠናክሩ የሚችሉባቸው በርካታ ዘርፎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

4፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩ መገናኛ ብዙኀንና የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ በማለት ማስጠንቀቁን ኢዜአ ዘግቧል። መገናኛ ብዙኀን በጦርነት ጊዜ ለአገሪቱ ብሄራዊ ጥቅሞ፣ ለሰላምና ደኅንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ ያሳሰቡት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እድሪስ፣ "ለጠላት ፕሮፓጋንዳ ግብዓት የሚውሉ መረጃዎችን" ከማሰራጨት መቆጠብ እንደሚያስፈልግም መክረዋል።

5፤ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ የሙከራ አገልግሎቱን መጀመሩን በድረገጹ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል። የሙከራ አገልግሎቱ ደንበኞች በሚገዟቸው የኩባንያው የስልክ ሲም ካርዶች የድምጽ፣ የጽሁፍና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን መስጠት ነው። ኩባንያው አንድን የሳፋሪኮም የሞባይል ስልክ ሲም ካርድ የሚሸጠው በ30 ብር ነው።

6፤ በአፍሪካ የአሜሪካ ወታደራዊ ዕዝ አፍሪኮም ዋና አዛዥ ጀኔራል ማይክል ላንግሌይ ዛሬ ሞቃዲሾ መግባታቸውን በሞቃዲሾ የአሜሪካ ኢምባሲ በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ጀኔራል ላንግሌይ ነውጠኛውን አልሸባብ በጋራ መዋጋት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ከሱማሊያው መከላከያ ሚንስትር አብዱልቃድር ሞሐመድ ኑር ጋር መነጋገራቸውን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ጀኔራል ላንግሌይ የአፍሪኮም አዲሱ ዋና አዛዥ ሆነው የተሾሙት በወሩ መጀመሪያ ነበር።

7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 52 ብር ከ4344 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ4831 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 59 ብር ከ2586 ሳንቲም፣ መሸጫው 60 ብር ከ4438 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ52 ብር ከ5078 ሳንቲም ሲገዛ እና በ53 ብር ከ5580 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል
897 viewsMAK story, 16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:28:34 በወልድያ ከተማ ሠላማዊ እንቅስቃሴዋ እንደቀጠለ መሆኑን የወልድያ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

የተለያዩ ሚዲያዎች እና የፖለቲካ ተንታኝ ነን የሚሉ የውጭ አካላት በማህበራዊ ሚዲያው ወልድያን በተመለከተ ሀሰተኛ ዜና እያሰራጩ ይገኛሉ።

" ከወልድያ አመራሩ ወጥቷል፣ ወልድያንም ህወሓት ይዟል " የሚሉ መረጃዎችን ቢያሰራጩም ሁሉም ሀሰት መሆኑና ህዝቡን ለማሸበር የሚሰራ ስራ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ግጭት በተለያዩ ከተሞች ተመሳሳይ አይነት በሀሰት ህዝብን የማሸበር ስራ ሲሰራ፣ ህዝብን ለማስደንገጥ ብዙ ጥረቶች ሲደረጉና በዚህ ሳቢያ ብዙ መመሰቃቀል ሲፈጠር እንደነበር አይዘነጋም።

እስካሁን ድረስ በወልድያና በቀጠናው ባለው ሁኔታ ከወልድያ ከተማም ይሁን ከጅቡቲ ወደብ የሚነሱ አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎችን ከተለመደው የዕለት ተዕለት ጉዟቸው ያስተጓጎላቸው ሁኔታ እንዳልተከሰተ ከወልድያ ከተማ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል ደግሞ ፤ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከሚማሩ ተማሪዎች ከወቅቱ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ስጋት አድሮባቸው ግቢያቸውን ለቀው የወጡ፤ የትራንስፖርት አጥተውም በእግር የተጓዙ እንዳሉ ለማወቅ ችለናል።

አንዳንድ መልዕክት የላኩ የግቢው ተማሪዎች ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ " ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱ እንዲደረግ ፤ አሁን በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ እነሱም ቤተሰብም ጭምር ጭንቀት ላይ በመሆኑና በዚህ ሁኔታ ትምህርትን በንቃት መከታተል ስለሚያስቸግር ተቋማቸው መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል።

በተማሪዎቹ ስጋት ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ምላሽ ለማግኘት እንጥራለን።
851 viewsMAK story, 15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ