Get Mystery Box with random crypto!

Maraki Books

የቴሌግራም ቻናል አርማ yourpeak — Maraki Books M
የቴሌግራም ቻናል አርማ yourpeak — Maraki Books
የሰርጥ አድራሻ: @yourpeak
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 171
የሰርጥ መግለጫ

ማራኪ ቡክስ በኦንኢማንድ ፕሪንቲንግ፥ በኦዲዮ እና ኢቡክ የተሳለጠ አቅቦት የአንባቢያንን እና የትምርት ተቋማትን ፍላጎት በማርካት እንዲሁም የኢትዮጵያውያን ደራሲያንን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በመጽሐፍ ንግዱ ዘርፍ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የሚሠራ ህጋዊ ድርጅት ነው።

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-02-11 10:32:26 Todaro, Economic Development 13ed, full Color and Paper Back ገብቷል
211 viewsNebiyu T. Lemma, 07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-08 13:05:02 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገጥማቸው መጽሐፍ የማግኘት ችግር በማራኪ ቡክስ (ባለጅ) እየተፈታ መሆኑንና በሥራችን ደስተኛ መሆናቸውን ታውቃላችሁ? በአዲስ አበባ፥ በአፋር፥ በጎጃም በጎንደር፥ በደብረብርሃን፥ በደሴ፥ በአዳማ እና በሌሎችም ከተሞች የምትገኙ የግል ኮሌጆች ላለፉት አራት አመታት ደንበኞቻችን ስለነበራችሁ እናመሰግናለን።
219 viewsNebiyu T. Lemma, 10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-08 12:56:05 ወዳጆቻችን ማራኪ ቡክስ አንባቢውን፥ የትምህርት ተቋማትንና ደራሲያንን ተጠቃሚ ለማድረግ በጥንካሬ እየሰራች የመሆኑን መረጃው ላልሰሙ ወዳጆቻችን ብታደርሱልን በመጽሐፍ ስጦታ ልናንበሸብሻችሁ ወስነናል። ይሄ ማጭበርበር አይደለም እውነት ነው።
203 viewsNebiyu T. Lemma, 09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-08 12:49:48 Medical Books color and hard Cover availabl
188 viewsNebiyu T. Lemma, 09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-02 17:10:58 የተያያዘው እጃችን ለማጨብጨብም እንኳን ቢሆን እንዳይፈታ
በዚህ ጦርነት ሀገሬ ኢትዮጵያ እንደምታሸንፍ ምንም ጥርጥር የለኝም። በሞቀው ሀገራዊ ስሜት፣ የተቀጣጠለው ትግል ግን በሌሎች ግንባሮች መቀጠል እንዳለበት ይሰማኛል። በአረንጓዴ ልማት፥ በምግብ ራስን በመቻል፥ በሥራ ፈጠራ፥ በቴክኖሎጂ፥ እና በሌሎችም። በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው ተመልሰው፤ በእውቀትና በስነምግባር ለሚሠሩ ሁሉ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ ሌብነት፥ አድሎና ሙስና ድራሻቸው ጠፍቶ በሙሉ ልብ ወደሥራ የምንመልስበት ቀን ናፍቆኛል።
_ስማ ጎበዝ እረፍት እያልክ ጤናህን፥ ኪስህንና ሞራልህን በሚጎዱ ተግባራት ውድ ጊዜና ጉልበትህን ማባከን ለአምስት ዓመት ተከልክሏል። በየምክንያቱ እየደገሱ አሸሼ ገዳሜም ፍፁም አይፈቀድም። ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በየቀኑ 16 ሰዓት ለመሥራት ተዘጋጅ። ሥራ በዛብኝ እያልክ ስታሾሙር የነበርክ ሁሉ ሥራ መብዛት ማለት ምን እንደሆነ በተግባር ታሳየናልህ። እረፍት ማለት መጎለት ወይም መጋደም የሚመስልህ ሳይሰልችህና ሳይድክምህ፥ መነሻና መድረሻህን በሚገባ አውቀህ እየጣፈጠህ እንዴት ውጤታማ ሥራ መሥራት እንዳለብህ ካሁኑ ተማር።
ጫትና መጠጥ ሸጠህ የምታድር ሁሉ ወጣት የሚያደነዝዝ ሳይሆን ወጣት ሥራ የሚያሲዝ ሌላ ሥራ ለመፍጠር ተዘጋጅ፤ መንግሥት ሰዎችንና ሠራተኞችን የሚያስከብርና የሚያበረታታ፥ የሌቦችን እጅ የሚሰበስብ ጠንካራ ጠንካራ ህግችን ያወጣል ተብሎ ስለሚጠበቅ በተናጠልም ባይሆን ሀብትንና ዕውቀትን በማሰባሰብ በጋራ የሚሠሩ የልማት ሥራዎች ላይ ለመሳተፍ እና ለመበልፀግ አቅድ። የመክበሪያው መንገድ አቋራጭ ነው ብለህ የምታስብ የማጭበርበሪያ ስልቶችን ከምታጠና ከውጪ የምናስገባቸውን የሚተካ ወይም ወደሌሎች አፍሪካ አገራት የምንልከውን ነገር ለመፍጠር ጣር።
እንደኖህ መርከብ ወዳጆቻችንን አስገብተን በራችንን እንዘጋለን። በቀደሙ ጥበቦቻችን ላይ እናተኩራለን። የአያት ቅድማያቶቻችንን አሻራዎች እንጠብቃለን እንፈትሻለን። ስንማር - ሌሎች ሲፈልጉ ሰጥተው ሲፈልጉ ለሚወስዱት እውቅና ብለን አንደክምም። ችግራችንን ለመለየትና ለመፍታት የሚረዱንን ጥበቦች ለይተን እናጠናለን። በዚህም አዲስ መስመር አዲስ ብርሃን ለዓለም እንፈነጥቃለን _ ደግሞ እንችላለን!! ለወሬ ላሉባታ የሚሆን ጊዜ አይተርፈንም። አዳዲስ የኃይል ምንጮችን እናስተዋውቃለን፥ የግንባታ ጥበብን የሚያቀላጥፉና የሚያሳምሩ ዓለም ያልደረሰባቸው ዘዴዎች ይኖሩናል። ሳይንቲስቶች ብዙ ደክመው መድሀኒት ያላገኙላቸው በሽታዎች በቀላሉ ይፈወሳሉ፤ ኢትዮጵያ ረጃጅም ዕድሜ ያላቸው የጠንካራ ሰዎች ሀገር ትባላለች፤ ዩትዩብን፥ ትዊተርን የሚያስንቁ የማህበራዊ ግንኙነት ዘዴዎች ይፈጠራሉ። ማረሻችን በድምፅ የሚታዘዝ ይሆናል። ወንዞቻችን ይገደባሉ። የዝናብ ውሃችንን በየጓራችን እየከተርን እያንዳንዳችን የዋና ገንዳ ይኖረናል፤ አሳ እናረባለን፥ የጓሮ አትክልት እናለማለን። አካባቢያችንን አረንጓዴ እናደርጋለን። ወደምንጫችን እንመለሳለን።
ጦርነቱ በቅርቡ ይጠናቀቃል። በድሉ ተዘናግተን በፍፁም ወደጭፈራ አንሄድም፤ አድዋ ላይ ካሸነፍን በኋላ እየፎከርን እና እየሸለልን፣ ጠጅና ጮማ እየቆረጥን፥ እኛ አንበሶቹ እያልን ሥራ ባንፈታ ኖሮ ካርባ ዓመት በኋላ ጀትና ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቆ ለበቀል የመጣውን የፋሽስት ጦር የምንመክትበት የተሻለ ነገር በኖረን ነበር። አሁን መዘናጋት ብሎ ነገር የለም። የተቋጠረው ግንባራችን ሳይፈታ፥ የመረረው ሀሞታችን ሳይጣፍጥ፥ የደደረው ክንዳችን ሳይላላ በቀጥታ ድህነትን ለመፋለም እንዘምታለን።
ጊዜ እየቆጠሩ በቀጥታም በተዘዋዋሪም እያሻጠሩብን ወደኋላ የሚመልሱንን ጠላቶቻችንን አሽንፈናል ብልን እፎይ ማለት አንችልም። ሁሌም ክንዱ የፈረጠመ የማይተኛ ጠላት እንዳለብን መዘንጋት የለብንም። ቅንነት መልካም ነው። ያን ያህል ግን ከተደቆስን በኋላ ዘራፍ የምንል ሳንሆን ቀድመን መጪውን የምናይ፥ አስተዋዮች መሆን ይጠበቅብናል። ከዚህም በኋላ የነባር ጠላቶቻችንን ግጥምና ዜማ እየተቀበሉ ጦርነትን የሚያጓሩብን ባንዳዎች ፈፅመው ይጠፋሉ ብላችሁ እንዳታስቡ። ትግሉ ይቀጥላል። ዛሬ ኢትዮጵያውያን ብሎም አፍሪካውያን አንድ እንድንሆን የመጣብን ችግር የመጣው በምክንያት ነው። የተያያዘው እጃችን በተገኙ ድሎች ተደስተን ለማጨብጨብም እንኳን ቢሆን እንዳይፈታ።
ይሄኛው ጦርነት በድል ይጠናቀቃል። ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፥ አፍሪካ ታሸንፋለች። ጊዜው የባለጆች ነው፥ እኛ ደግሞ ባልጆች ነን፤ ዋዛ ፈዛዛ፥ ልመናና ተመፅዋችነት ብሎ ነገር የማይሞክረን።
ከድህነት ጋር ለሚደረግ ጦርነት
በቀጥታ ወደፊት•••••••
ባለ'ጅ ነቢዩ ተፈራ
329 viewsNebiyu T. Lemma, 14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-03 19:30:48

429 viewsNebiyu T. Lemma, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-17 07:08:38

436 viewsNebiyu T. Lemma, 04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-14 21:38:10 Channel photo updated
18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-14 21:30:40 መጽሐፍ በነፃ እንዴት ማውረድ ይቻላል?

361 viewsNebiyu T. Lemma, 18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ