Get Mystery Box with random crypto!

AMN-Addis Media Network

የሰርጥ አድራሻ: @addismedianetwork
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 35.84K
የሰርጥ መግለጫ

This is an official Telegram channal for Addis Media Network (AMN) We trive to be the prime informer of issues. Hence, our motto says so, 'first to inform'
ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ !!
contact us via:- E-mail:- addisaammaa@gmail.com
twitter.com/AmnAddis

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 59

2022-09-04 20:25:29
2.8K views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 19:52:57 ለሀገርና ለማህበረሰብ በጎ ተግባር የፈጸሙ ሰዎችን የማመስገን ባህልን ማዳበር ይገባል -ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 29 ቀን 2014

ኢትዮጵያውያን ለሀገርና ለማህበረሰብ በጎ ተግባር የፈጸሙ ሰዎችን የማመስገን ባህልን ሊያዳብሩ እንደሚገባቸው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።

10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሐግብር ዛሬ በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የዓመቱ ልዩ የበጎ ሰው ተሸላሚ ሆናለች።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ባስተላለፉት መልዕክት "በጎነት ለተወሰነ ግለሰብ፣ሃይማኖት፣ ባለሥልጣን ብቻ የተወሰነ ምግባርና ተግባር እንዳልሆነ ተናግረዋል።

በጎ ሰዎች ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ሲተርፉ ነገ የተሻለ ይሆናል ያሉት ፕሬዚዳንቷ፤ ሁሉም ሰው ሥራውን በታማኝነት በመፈፀም በጎነትን በተግባር ሊያሳይ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ዛሬ በበጎ ሰው ሽልማት ስማቸው ከፍ ያሉ በጎ አድራጊዎች ታሪክ ለሌሎችም አርዓያ የሚሆን ነው ብለዋል።

በተለይም በዘንድሮ የበጎ ሰው ሽልማት አራት ሴቶች ተሸላሚ መሆናቸው የሴቶች ሚና ሀገራዊና ማህበረሰባዊ ሚና እያደገ መምጣቱን ያሳያል ነው ያሉት።

ለአብነትም የእነ ዶክተር ርብቃ ጌታቸው፣ የኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ታሪክ ትልቅ ምስክር መሆኑን በማንሳት።

ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሀገርና ህዝብን ያገለገሉ ኢትዮጵያውያንን የማመስገን ባህል ሊዳብር እንደሚገባም ተናግረዋል።

"በማኀበረሰባችን በአብዛኛው ሰዎችን የማመስገን እና የዕውቅና የመስጠት ንፉግነት አለብን" ያሉት ፕሬዘዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በጎነትን ምንጊዜም ማበረታታት አለብን ብለዋል።

የበጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በነበሩ ዓመታት ለ187 በጎ ሰዎችና ድርጅቶች እውቅና ሰጥቷል።

የመምህርነትን እና መንግስታዊ ሃላፊነትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ነው ሽልማቱ የሚሰጠው።

ኢዜአ እንደዘገበው ለዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማትም 691 እጩዎች ለዘርፎቹ ቀርበው፥ ለየዘርፎቹ የመጨረሻዎቹ እጩዎች ተለይተው ዛሬ ተሸላሚ ሆነዋል።

በጎ ሰሪዎችን እውቅና በመስጠት ሌሎች በጎዎችን መፍጠር ዓላማው ያደረገው ይህ መርሐግብር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለሀገር እና ለወገን መልካም ለሰሩ እና በጎ ለዋሉ ሽልማትና እውቅና የሚሰጥበት ነው።
2.9K views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 15:52:19 የጋራ ምክር ቤቱ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዳግም ጦርነት የቀሰቀሱ የአሸባሪው ሕወሓት ኃይሎች ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመለሱ ጫና እንዲያደርጉ ጠየቀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ነሐሴ 29/2014

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዳግም ጦርነት የቀሰቀሱ የአሸባሪው ሕወሃት ኅይሎች ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመለሱ ጫና እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጠየቀ።

አንዳንድ የውጪ ኃይሎች የሽብር ቡድኑን በመደገፍ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ከሚያደርጉት ጣልቃገብነት እጃቸውን በመሰብሰብ የሰላም መንገድን እንዲደግፉም ጥሪ አቅርቧል።

53 ፓርቲዎችን በአባልነት ያቀፈው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ቆሞ ሰላማዊ አማራጮች እንዲቀጥሉ ሲል የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

የአቋም መግለጫውን ያነበቡት የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ዶክተር መብርሃቱ አለሙ እንዳሉት፤ ለረጅም ዘመን በዘለቀ ጦርነት ስልጣኔና ዕድገቷ የተገታው ኢትዮጵያ አሁንም ከጦርነት አዙሪት አልወጣችም።

ባለፉት 22 ወራት ገደማ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት ከፍተኛ ሰብዓዊ፣ አኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳቶች ማስከተሉን ጠቅሰዋል።

የጦርነቱ ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋምና መሰረተ ልማት መልሶ ለመገንባት መጠነ ሰፊ ስራዎች ቢከናወኑም ከጉዳቱ ስፋትና ክብደት አንጻር በዘላቂነት መልሶ የማቋቋም ስራው የሚፈለገውን ያክል አለመሆኑን ገልጸዋል።

መንግስት ለወሰደው የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔና ጦርነቱ ሰላማዊ እልባት እንዲሰጠው በአፍሪካ ሕብረት በኩል የተጀመረው ጥረት ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት እንደነበር አንስተዋል።

ሰላማዊ አማራጩ እያለ በወርሃ ነሃሴ በአሸባሪው ሕወሃት ኅይሎች በተከፈተው ጥቃት ሳቢያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ምክር ቤቱን ያሳዘነ ድርጊት መሆኑን ገልጸዋል።

ምክር ቤቱ 'ለኢትዮጵያ የሚበጀው ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ በውይይት መፍታት ነው' ብሎ እንደሚያምን ገልጸው፤ አሁንም ቢሆን በሰላማዊ ውይይት፣ ምክክርና  መግባባት ችግሮች እንዲፈቱ ምክር ቤቱ ጠይቋል።

ምክር ቤቱ ባወጣው ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ ጥቃቱን የጀመሩት የአሸባሪው ሕወሃት ኃይሎች መንግስት በወሰደው የተኩስ አቁም እርምጃ መሰረት ወደ ሠላም አማራጭ እንዲመለሱ ጠይቋል።

አሸባሪው ሕወሃት ለትግራይ ሕዝብ ሠብዓዊ ዕርዳታ የቀረበን ከግማሽ ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም መዝረፉ የትግራይን ህዝብ ለችግር የሚዳርግ ነውረኛ ተግባር መሆኑን ጠቅሶ አውግዟል።

የውጪ ኃይሎች በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ከሚያደርጉት ጣልቃገብነት እጃቸውን እንዲሰበስቡ፣ ይልቁንም  የሰላም መንገድን እንዲደግፉ ጥሪ ማቅረቡን ኢዜአ ዘግቧል።

መንግስት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት የመጠበቅ ኅላፊነት ስላለው በቅርቡ የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ በገባ የጠላት አውሮፕላን ላይ የተወሰደውን እርምጃ ምክር ቤቱ አድንቋል።

ለኢትዮጵያ ሰላምና ሁለንተናዊ ዕድገት ሁሉም የሚዲያ ተቋማትና ዜጎች ጦርነትን ከሚያባብሱ መልዕክቶችና ተግባራት ተቆጥበው በሠላም አማራጭ ላይ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርቧል።
1.4K views12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 15:10:54 https://amn.gov.et/?p=2223
“የእሁድ ገበያዎች ከእሁድ ቀን በተጨማሪም እስከ አዲስ አመት ድረስ ይዘልቃሉ”-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
1.6K views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 15:06:51
"የእሁድ ገበያዎች ከእሁድ ቀን በተጨማሪም እስከ አዲስ አመት ድረስ ይዘልቃሉ"-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ነሐሴ 29/2014

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት መጪውን ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ ለበአል ፍጆታ የሚሆኑ በርካታ ምርቶች ወደ መዲናዋ በመግባት ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

ምርቶቹም በተለያዩ የእሁድ ገበያዎችና የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች እንደሚገኙም ከንቲባ አዳነች ጠቁመዋል።

በዚህም መሰረት የእሁድ ገበያዎች ከእሁድ ቀን በተጨማሪም እስከ አዲስ አመት ድረስ የሚዘልቁ ስለሆነ፣ ህብረተሰቡ ያለ አግባብ ዋጋ ከሚጨምሩና የኢኮኖሚ አሻጥር ከሚፈጥሩ አካላት ራሱን በመጠበቅ በየአካባቢው በሚገኙ የእሁድ ገበያዎችና የሸማች ማህበራት ሱቆች እንዲገበያይ ጥሪ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
1.7K views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 12:04:38 https://amn.gov.et/?p=2210
“አሸባሪው የህወሃት ቡድን በቆቦ ወረዳ ህፃናትና አዛውንቶች ላይ በከባድ መሳሪያ ጥቃት ፈፅሟል”-ተጎጂዎች
2.6K views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 07:05:56 https://amn.gov.et/?p=2198
የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ለ2 ሺህ አይነስውራን የማንበቢያ መነጽር አበረከተ።
576 views04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 22:10:19 https://amn.gov.et/?p=2193
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በሀገር ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለመቀልበስ  የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ገለጹ።
887 views19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 18:33:52 https://amn.gov.et/?p=2188
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለቻን የእግር ኳስ ውድድር ማለፉን አረጋገጠ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በአልጄሪያ አስተናጅነት ለሚካሄደው ....
2.7K views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 16:44:46 https://amn.gov.et/?p=2183
መጪዎቹን በአላት ምክንያት በማድረግ  ከአጎራባች አካባቢዎች በርካታ መጠን ያለው ምርት  ወደ ከተማዋ መግባት ጀምሯ...
3.3K views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ