Get Mystery Box with random crypto!

ሲሪል ራማፎሳ በድጋሚ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ AMN - ሰኔ 08/2016 ዓ.ም | AMN-Addis Media Network

ሲሪል ራማፎሳ በድጋሚ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

AMN - ሰኔ 08/2016 ዓ.ም

በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ የፓርላማ አብላጫ ድምጽ ያጣው የደቡብ አፍሪካ ገዢ ፓርቲ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ (ኤ ኤን ሲ) እና ተቃዋሚው ዴሞክራቲክ አሊያንስ (ዲ ኤ) ፓርቲ የብሄራዊ አንድነት መንግስት ለመመስረት ከስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ሲሪል ራማፎሳን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አድርጎ በድጋሚ መርጧል።

ፕሬዝደንቱ በድጋሚ መመረጣቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር ፤አዲሱን ጥምረት ያወደሱ ሲሆን ህዝቡ ለደቡብ አፍሪካ ሁለንተናዊ ዕድገት በጋራ እንድንሠራ ይጠብቃል ብለዋል።

በባለፈው ወር ምርጫ የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረንስ ፓርቲ (ኤ ኤን ሲ) ከ30 ዓመታት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ አብላጫውን ድምፅ በማጣቱ ነው ከተቃዋሚው ዴሞክራቲክ አሊያንስ (ዲኤ) ፓርቲ ጋር የብሄራዊ አንድነት መንግስት ለመመስረት ከስምምነት ላይ የደረሱት፡፡

የኤ ኤን ሲ ዋና ፀሐፊ ፊኪሌ ባሉላ የጥምር ስምምነቱን "አስገራሚ እርምጃ" ያሉ ሲሆን ብሄራዊ አንድነት ለመፍጠር ትልቅ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይነት በጥምር መንግሥቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ፓርቲዎች በአገሪቱ ካቢኔ ውስጥ የተለያዩ የሥልጣን ቦታዎችን እንደሚጋሩ ቢቢሲ ዘግቧል።