Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ የ6ኛ ክፍል ፈተና ከነገ ጀምሮ ይሰጣል AMN-ሰኔ 11/2016 ዓ.ም የ6ኛ ክ | AMN-Addis Media Network

በአዲስ አበባ የ6ኛ ክፍል ፈተና ከነገ ጀምሮ ይሰጣል

AMN-ሰኔ 11/2016 ዓ.ም

የ6ኛ ክፍል ፈተና ከነገ ሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በ183 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለ86 ሺ 222 ተማሪዎች እንደሚሰጥ የቢሮው መረጃ ያሳያል።

በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች ከ2 ሺ 200 በላይ ፈታኝ ፤ ከ700 በላይ ሱፐር ቫይዘር እና 183 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ፈተናውን ለማስፈጸም መመደባቸው ተገልጿል።

ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፈተና ህትመት ጀምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የተጠናቀቁ መሆናቸው ተመላክቷል።