Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ AMN - ሰኔ 5/2016 | AMN-Addis Media Network

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

AMN - ሰኔ 5/2016 ዓ.ም

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡

ምሁራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው በማስተማር ውጤታማነት፤ ባሰተሟቸው ጥናታዊ ጹሁፎች፤ ለማህበረሰብ ለበረከቱት አካዳሚያዊ አገልግሎትና በዩኒቨርሲቲው በነበራቸው የተቋም አስተዳደር ድምር ውጤት መሆኑን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።
በዚሁ መሰረት፡-

ፕሮፌሰር ይምጡበዝናሽ ወ/አማኑኤል በ ሜዲካል ማይክሮ ባዮሎጂ

ፕሮፌሰር አንተነህ በለጠ በፍርማሴዩቲክስ

ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ በፕላንት ጄኔቲክስ

ፕሮፌሰር አህመደ ሁሴን በ አናሊቲካል ኬሚስትሪ

ፕሮፌሰር ታደሰ እጓለ በማይክሮባዮሎጂ

ፕሮፌሰር ተክለሀይማኖት ኃ/ሥላሴ በፕላንት ባዮቴክኖሎጂ

ፕሮፌሰር ተሾመ ሰንበታ በኮንደንስድ ማተር ፊዝክስ

ፕሮፌሰር እንጉዳይ አደመ በካሪኩለም ጥናት

ፕሮፈፌሰር ሀብቴ ተኪኤ በሜዲካል ኢንቶሞሎጂ

ፕሮፌሰር ቃላብ ባዬ በ ሂዩማን ኒውትሪሽን

ፕሮፌሰር ሰለሞን ሙሉጌታ በአርባን ፕላኒንግ

ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ፍሰሀ በፖሊዮኢንቨሮመንታል ጥናት ናቸው።