Get Mystery Box with random crypto!

የአከራይና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ወቅት የመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራይ ማሟላት ያለባቸው መረጃ | AMN-Addis Media Network

የአከራይና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ወቅት የመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራይ ማሟላት ያለባቸው መረጃዎች

AMN - ሰኔ 1/2016 ዓ.ም

በአዲስ አበባ የአከራይና ተከራይ ህጋዊ ውል በምዝገባ ወቅት ማንኛውም የመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራይ ማሟላት ያለባቸው መረጃዎች፤-

በህግ አግባብ የተዘጋጀ የመኖሪያ ቤት ውል ሰነድ

የአከራይና ተከራይ የነዋሪነት መታወቂያ ፣ የመስሪያ ቤት መታወቂያ ፣ መንጃ ፍቃድ ፣ ፓስፖርት ፣ የጠበቃ ፍቃድ ፣ የሰራተኞች ጡረታ መታወቂያ ፣ የዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ ተማሪ የሙያ ስራ ፍቃድ ኦርጅናል ኮፒ ፤

የመኖሪያ ቤት ውሉ የሚመዘገበው በወኪል ከሆነ ህጋዊ ውክልና የሁለት ምስክሮች የታደሰ መታወቂያ ኦርጅናል ኮፒ፤

አከራይ የመኖሪያ ቤቱን ለማከራየት የሚያስችል መብት እንዳለው የሚያሳይ ህጋዊ ሰነድ :-

- የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ

- ሰነድ አልባ ይዞታዎች መሆኑን ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ወይም

- በፍርድ አፈፃፀም የተሸጠ ንብረት ሰነድ ወይም የተከራየው ቤት በውርስ የተገኘ ሆኖ
ስም ዝውውር ካልተፈፀመ የወራሽነት ማረጋገጫ ኦርጅናል እና ኮፒ ይዘው መገኘት እንዳለባቸው ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡