Get Mystery Box with random crypto!

AMN-Addis Media Network

የቴሌግራም ቻናል አርማ addismedianetwork — AMN-Addis Media Network A
የቴሌግራም ቻናል አርማ addismedianetwork — AMN-Addis Media Network
የሰርጥ አድራሻ: @addismedianetwork
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.32K
የሰርጥ መግለጫ

This is an official Telegram channal for Addis Media Network (AMN) We trive to be the prime informer of issues. Hence, our motto says so, 'first to inform'
ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ !!
contact us via:- E-mail:- addisaammaa@gmail.com
twitter.com/AmnAddis

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 57

2022-09-05 17:37:12 የፍትህ ሚኒስቴርና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የጋራ መድረክ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 30 ቀን 2014

ከነሐሴ 26 ቀን 2014 ጀምሮሲካሄድ የነበረው የፍትህ ሚኒስቴርና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የጋራ መድረክ ቀጣይ የአፈፃፀም አቅጣጫዎች በማስቀመጥ መጠናቀቁ ተገለጸ።

የጋራ መድረኩ የፍትሕ ሚኒስቴርና የክልል ፍትሕ ቢሮ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና የአጋር ድርጅት ተወካዮች በተገኙበት ለሦስት ተከታታይ ቀናት የተካሄድ ሲሆን ፤ የሶማሌ፣ የሐረሪ፣ የኦሮሚያ፣ የአማራ፣ የጋምቤላ፣ የሲዳማ፣ የደቡብ ብ/ብ/ህዝቦች፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ የአፋር ክልል እንዲሁም የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮዎች የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርገል ተብሏል፡፡

አጋር ድርጅቶች የፍትሕ ዘርፉን ለመደገፍ ያስቀጡት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና እያሰገኘ ያለው ውጤት፣ በክልሎች የተደረገ ሱፐርቪዥን ሪፖርትና የጋራ ምክር ቤት መነሻ ዕቅድ እንዲሁም የ2015 በጀት ዓመት ተቋማዊ የትኩረት አቅጣጫዎች በተለያዩ አቅራቢዎች ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል፡፡

ክልሎች ባቀረቡት የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት በተለይም በህግ ጉዳይ የህብረተሰብ ተሳትፎን ማሳደግ፣ የወንጀል ህግ አፈፃፀም በተለይም የወንጀል መዝገብ የማጥራት፣ የማስቀጣት እንዲሁም የፍርድ ዉሳኔ የማስፈፀም ምጣኔ ያለበት ደረጃ፣ የመንግስትና የህዝብ ፍትሐብሔራዊ ጥቅም የማስጠበቅ፣ ሰብአዊ መብትን የማስክበርና የማክበር፣ የንቃተ ሕግ ትምርትና ስለጠና፣ አቅም ለሌላቸው ዜጎች የነፃ ህግ ድጋፍ አገልግሎት አሰጣጥ፣ የህግ ረቂቅ ዝግጅት ጥራትና ውጤታማነት እንዲሁም የሌሎች ተግባራት አፈፃፀም በሪፖርቱ ቀርቦ መገምገሙ ታውቋል፡፡

በመድረኩ ማጠናቀቂያ ወቅት የፍትሕ ሚኒሰትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ መድረኩ ሀገራዊ የሆነ የፍትሕ መረጃ ማግኘት የሚያስችል፣ አንዱ ከአንዱ ልምድ የሚቀስምበት በመሆኑ በቀጣይም ተጠናከሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በዚህ ዓመት ተኩረት የሚሰጥባቸዉን ጉዳዮች ሲያብራሩ ማህበረሰብ ተኮር የሆነ የፍትሕ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አዲስ አሰተሳሰብና አዲስ ዕይታ ይዞ መምጣት እንደሚገባ ጠቁመው ፤ መነሻ የሚሆን አሰራር እንደየክልሉ ነባራዊ ሁኔታ ተዘጋጅቶ መቅረብ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ፍቃዱ ፀጋ በበኩላቸው በጋራ ምክር ቤቱ ዕቅድ የተቀመጡ ጉዳዮችን በሚገባ በማየት ሊሰተካከል ይገባል ተብሎ የሚነሳ ጉዳይ ካለም በማንሳት የክስና ምርመራ አፈፃፀምን በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ፣ እንዲሁም ዜጎችን በሚፈለገው ልክ ለማገልገል መደላድል መፍጠር ይገባል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡
2.9K views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 17:17:25 የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን የስንቅ ዝግጅት ጀመሩ


አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 30 ቀን 2014

በክፍለ ከተማዉ ወረዳ 3 በተዘጋጀው የስንቅ ዝግጅት መረሃ ግብር ላይ የከተማና የክ/ከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዉ ስንቅ የሚያዘጋጁ ነዋሪዎችን አበረታተዋል።

የክ/ከተማው ዋና ስራ አሰፈጻሚ ዶ/ር አበራ ብሩ ሀገር መከታና አለኝታ የሆነውን መከላከያን ለመደገፍ በክፍለ ከተማው በርካታ ስራዎች የሚሰሩ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ በሚደረጉ ድጋፎች ህብረተሰቡ ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

መከላከያ ሰራዊቱን በመወከል በስንቅ ዝግጅቱ የተገኙት ልፍተናንት ኮሎኔል ትዕግስት ፈረደ ለ3ኛ ጊዜ በተከፈተብንን ወረራ ለመቀልበስ በምታደርጉት የደጀንነት ድጋፍ ላይ በመገኘተ በመከላከያ ስም ኩራትና ክብር ተሰምቶኛል ብለዋል።

የወረዳ 3 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ሰይፉ ለሀገሩ ክብር እየተዋደቀ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊትና ጥምር ጦሩ ስንቅ ዝግጅት ላይ መሳተፍ የሚያስመሰግን በመሆኑ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

በስንቅ ዝግጅቱ ላይ የተሳተፉት ነዋሪዎች የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ሀገራችንን ለሚጠብቀው መከላከያ ሀይላችን ያላቸውን ደጀንነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ጥምር ጦሩ ደጀን ከመሆን ባሻገር አገባቢያችን በመደራጀት ከሰርጎ ገቦችና ከጸጉረ ልውጦች ነቅተው እየጠበቁ መሆናቸውንም ገልጸዋል ።
2.6K views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 15:30:26
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለጀግናዉ መከላከያ ሰራዊት ስንቅ ማደራጀት ተጀመረ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 30 ቀን 2014

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኙ የሴት አደረጃጀቶች ለጀግናዉ የኢትዮጵያ ሰራዊት ስንቅ በማዘጋጀት ደጀንነታቸዉን እያረጋገጡ መሆኑ ተጠቆመ።

የክፍለ ከተማውው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉነህ ፈይሳ አሸባሪዉ ሕዋሓት ከመንግስት የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ወደ ጎን በመተው ጦርነቱን መቀጠሉን ገልጸው ይህንንም ለመመከት የሴት አደረጃጀቶች የስንቅ ድጋፍ ለማድረግ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀዋል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እንደተናገሩት የከተማዋ የትምህርት ተቋማት ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን ሀገራቸውን ለመከላከል ሰራዊት ደጀን በመሆን ሀገራቸውን ከአደጋ ሊጠብቁ ይገባል ብለዋል።

ዶክተር ዘላለም አክለውም ትምህርት ቢሮው ይህን በማስተማር ኃላፊነቱን ይወጣል ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙስጠፌ ትኩ በበኩላቸው የበለፅገችና ሰላሟ የተርጋገጠችን ሀገር ለመፍጠር ከጦርነት ነፃ መሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
3.2K views12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 13:22:49 በጉለሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት የሚሆን የስንቅ ዝግጅት ተጀመረ


አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ ክፍለ ከተማ አሸባሪዉ ሕወሓት የከፈተዉን ጦርነት በመመከት ላይ ለሚገኘዉ መከላከያ ሠራዊት የሚሆን የስንቅ ዝግጅት ተጀመረ፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ በክፍለ ከተማዉ ወረዳ 1 ተገኝተው የስንቅ ዝግጅቱ ላይ ተገኝተው የስንቅ ዝግጅቱን ተሳታፊዎች አበረታትተዋል፡፡ነዋሪዎችን ባበረታቱበት ወቅት የሃገር መከታና አለኝታ የሆነውን መከላከያን ለመደገፍ በክፍለ ከተማው በርካታ ስራዎች የሚሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች የሃገር መከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍ በገንዘብ ፣በጉልበትና በእውቀት ከመደገፍ ባሻገር በሰው ሃይልም በመቀላቀል ድጋፉን ማበርከት እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በበኩላቸው ህዝቡ ላደረገው ተነሳሽነት ምስጋናቸውን አቅርበው ይህ የሚያሳየው ለሀገራችሁ ሉዓላዊነት ህይወታችሁን ለመስጠትም ቢሆን የየተዘጋጃችሁ መሆናችሁን ነውና ኢትዮጵያ በታሪክ ስትዘክራችሁ ትኖራለች ብለዋል።

የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ሀገራችንን ለሚጠብቀው መከላከያ ሀይላችን ተከፍሎ የማያልቅ ውለታ አለብን ያሉ የስንቅ ዝግጅቱን የጀመሩት ነዋሪዎቹ በሁሉም ግንባር ድጋፋቻዉን አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ መግለጻቸዉን ከአስተዳሩ ከንቲባ ታህፈት ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡


ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis
3.3K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 11:43:22 "አሸባሪው ህወሃት የቀረበለትን የሰላም አማራጭ ረግጦ ዳግም ጦርነት መክፈቱ በትግራይ ህዝብ ጫንቃ ላይ ቆሞ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ነው" -በተለያዩ ግንባሮች እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት የሰጡ ምርኮኞች

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ነሐሴ 30/2014

አሸባሪው ህወሃት የቀረበለትን የሰላም አማራጭ ረግጦ ዳግም ጦርነት መክፈቱ በትግራይ ህዝብ ጫንቃ ላይ ቆሞ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ነው ሲሉ በተለያዩ ግንባሮች እጃቸውን ለጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊት የሰጡ ምርኮኞች አጋለጡ፡፡


ምርኮኞቹ እንደተናገሩትም የትግራይን ህጻናት ሳይቀር ወደ ጦር ግንባር እየማገደ የሚገኘው አሸባሪው ህወሃት በሃሰተኛ ትርክት የትግራይን ወጣት ራሱ ወደለኮሰው ጦርነት እየማገደ ክልሉን ትውልድ አልባ የማድረግ እኩይ አላማውን ገፍቶበታል።

ይህም ተግባሩ የሽብር ቡድኑን የባንዳነት ትክክለኛ ባህሪ በተጨባጭ እያረጋገጠ መሆኑንም ነው ምርኮኞቹ የተናገሩት።

ምርኮኞቹ አሸባሪው የህወሃት ቡድን በትግራይ ህዝብና ህፃናት ላይ እየፈፀመ ያለውን ስቃይና እንግልት በመቃወም በፕሮፖጋንዳ ተታለው ከገቡበት ጦርነት በመውጣት ለጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊት እጃቸውን መስጠታቸውን ገልፀዋል፡፡

የሰላም አማራጭ በሰፊው ቀርቦለት ጦርነትን መርጦ ህጻናትን ሳይቀር ወደ ጦርነት እየማገደ ያለው የሽብር ቡድኑ ህወሃት የራሱን የስልጣን ላይ ቆይታ ለማራዘም ትግራይ ላይ ምንም አይነት ጥፋት ከመፈጸም ወደኋላ እንደማይመለስ ምርኮኞቹ አረጋግጠዋል።

"የትግራይ ከፍታ የሚረጋገጠው በኢትዮጵያ መቃብር ላይ ነው" በሚል ቀቢፀ ተስፋ በመነሳሳት ኢትዮጵያን ለማፍረስና ህዝቦቿን ለመበተን ዳግም ጦርነት ቢከፍትም አላማ ቢስ ለሆነው የሽብር ቡድኑ አላማ መሰለፍ ከንቱ በመሆኑ እጃቸውን ለመስጠት እንዳስገደዳቸው ተናግረዋል።

በቡድኑ የውሸት ወሬና ፕሮፓጋንዳ ተታለው በመሰለፍ ለፈፀሙት ጥፋት በመፀፀት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ፤ ለመከላከያ ሰራዊቱና ለሌሎች የፀጥታ ኃይል ይቅርታ ጠይቀው የህወሃት የሽብር ቡድንን ከንቱ ራስ ወዳድ አላማ ለማስፈፀም የተሰለፉ የትግራይ ወጣቶችም የሚጓዙበት መንገድ ፈጽሞ እንደማያዋጣ ተረድተው ፈጥነው እነዲነቁ ምርኮኞቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ምርኮኞቹ በመከላከያ ሰራዊትና በሌሎች የፀጥታ ሃይሎቻችን ለተደረገላቸው መልካም አቀባበልና እንክብካቤም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ከጦርነት ኪሳራ እንጂ ትርፍ እንዳማይገኝ የገለፁት ምርኮኞቹ፤ አሸባሪ ቡድን ለዳግም እልቂት የከፈተውን ወረራ በማውገዝ ወደ ሰላም እንዲመጣ የትግራይ ህዝብ፤ ወጣቶችና ልዩ ኃይል አባላት ጫና መፍጠር እንደሚገባቸው ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ
https://www.youtube.com/channel/UC9lAZ1l0TvJG65R-QeCDHkg
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis
733 views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 11:30:57
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ማኅበር ተመሠረተ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ነሐሴ 30/2014
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ማኅበር ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ተመሥርቷል።

ማኅበሩን ከዚህ በፊት የተቋቋሙ አምስት ማኅበራት በጋራ እንደመሰረቱት ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ እንደተናገሩት ማኅበሩን ለመመስረት ባለፉት አራት ዓመት ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል።

የማኅበሩ መመስረት ለቡና ልማቱ የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመው አርሶ አደሩንም ለመደገፍ ድርሻው ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረዋል።

ማኅበሩ ፕሮጀክት በመቅረጽ ትልልቅ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅበትም መመላከቱን ኢዜአ ዘግቧል።

በአርሶ አደሩ በኩል የሚነሱ የግብአት አቅርቦት ችግርን መፍታት፣ በዓለም ገበያ መቀዛቀዝ ምክንያት አርሶ አደሩ እንዳይጎዳ የመድን ተጠቃሚ ማድረግ የማህበሩ ቀጣይ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የማኅበሩ መስራች ጉባኤ እየተካሄደ ሲሆን የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።

ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ
https://www.youtube.com/channel/UC9lAZ1l0TvJG65R-QeCDHkg
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis
944 views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 11:08:10 በአሜሪካ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ከ100 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ነሐሴ 30/2014

በአሜሪካ በዋሺንግተን ዲሲ ዓለምአቀፉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የትግበራ ቡድን ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ከ100 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ መሰብሰቡን አሰታወቀ።

ዳያስፖራ ቡድኑ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብሩን ያካሄደው የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋምና በተፈጥሮ አደጋዎች የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ ነው ተብሏል፡፡

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር ያቀናጁትንና ገንዘባቸውን በመለገስ የተሳተፉትን የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት አመስግነዋል፡፡

ዳያስፖራው በሁሉም ዘርፍ ተሳትፎውን እንዲያሳድግ አምባሳደሩ ጠይቀዋል፡፡

በገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብሩ ላይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፣ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በተለይም የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስገንዘብ፣ በዕውቀትና በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በተቋማት ግንባታ፣ በዲጂታልና በህዝብ ለህዝብ ዲፕሎማሲ የዳያስፖራው ተሳትፎ ማደግ እንዳለበት መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ
https://www.youtube.com/channel/UC9lAZ1l0TvJG65R-QeCDHkg
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis
1.0K viewsedited  08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 09:59:20
ፈተና፣ ድል፣ ተስፋ የተሰኘው የ2014ን ዐበይት የመንግሥት ክዋኔዎች የሚዳስስ የአዲስ ወግ የውይይት መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ነሐሴ 30/2014
ፈተና፣ ድል፣ ተስፋ የተሰኘው የ2014ን ዐበይት የመንግሥት ክዋኔዎች የሚዳስስ የአዲስ ወግ የውይይት መርሀ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚደንት አደም ፋራህ እንዲሁም የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ጋዜጠኛዋ ሮዛ መኮንን አወያይነት ሀሳባቸውን እንደሚያቀርቡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ
https://www.youtube.com/channel/UC9lAZ1l0TvJG65R-QeCDHkg
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis
1.6K views06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 09:51:11
አሸባሪው ህወሓት የእርዳታ ድርጅቶች ለርሃብተኞች የሚለግሡትን ምግቦች ለውጊያ እየተጠቀመበት መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ነሐሴ 30/2014

አሸባሪው ህወሓት የእርዳታ ድርጅቶች ለርሃብተኞች የሚለግሡትን ምግቦች ለውጊያ እየተጠቀመበት መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሽብር ቡድኑ ከሠሞኑ በከፈተብን ጦርነት በምግብ እጥረት ለተጎዱ ዜጎች የሚቀርበውን ኮርን ሶያ ብሌንድ /Corn Soya Belend/ የተሰኘ አጣዳፊ የምግብ እጥረትን ለማከም የሚውል የዓለም ጤና ድርጅት /WFP/ መመሪያን አሟልቶ የተዘጋጀውን አልሚ ምግብ ለታጣቂዎቹ ተጠቅሟል ነው ያለው ሚኒስቴሩ።

አልሚ ምግቡ ዜጎችን ከርሀብ ሞት የሚታደግ እና የሚያክም መሆኑንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ሚኒስቴሩ አሸባሪው የህወሃት ቡድን ዜጎች በርሃብ ጠኔ ታመው እየሞቱ እሱ ግን በምሽግ ከዝኖ ታጣቂዎችን እየቀለበ እንደሚያዋጋበት በከፈተብን ጦርነት ማረጋገጥ ተችሏልም ብሏል።

ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ
https://www.youtube.com/channel/UC9lAZ1l0TvJG65R-QeCDHkg
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis
1.6K views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 09:43:35
አዲስ ወግ ፈተና፣ ድል፣ ተስፋ በሚል ርዕስ እየተካሄደ ይገኛል

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ነሐሴ 30/2014

የ2014 የመጨረሻው አዲስወግ 'ፈተና፣ ድል፣ ተስፋ' በሚል ርዕስ 2014ን በመቃኘት እየተካሄደ እንደሚገኝ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ
https://www.youtube.com/channel/UC9lAZ1l0TvJG65R-QeCDHkg
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis
1.7K views06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ