Get Mystery Box with random crypto!

አሸባሪው ህወሓት የእርዳታ ድርጅቶች ለርሃብተኞች የሚለግሡትን ምግቦች ለውጊያ እየተጠቀመበት መሆኑን | AMN-Addis Media Network

አሸባሪው ህወሓት የእርዳታ ድርጅቶች ለርሃብተኞች የሚለግሡትን ምግቦች ለውጊያ እየተጠቀመበት መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ነሐሴ 30/2014

አሸባሪው ህወሓት የእርዳታ ድርጅቶች ለርሃብተኞች የሚለግሡትን ምግቦች ለውጊያ እየተጠቀመበት መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሽብር ቡድኑ ከሠሞኑ በከፈተብን ጦርነት በምግብ እጥረት ለተጎዱ ዜጎች የሚቀርበውን ኮርን ሶያ ብሌንድ /Corn Soya Belend/ የተሰኘ አጣዳፊ የምግብ እጥረትን ለማከም የሚውል የዓለም ጤና ድርጅት /WFP/ መመሪያን አሟልቶ የተዘጋጀውን አልሚ ምግብ ለታጣቂዎቹ ተጠቅሟል ነው ያለው ሚኒስቴሩ።

አልሚ ምግቡ ዜጎችን ከርሀብ ሞት የሚታደግ እና የሚያክም መሆኑንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ሚኒስቴሩ አሸባሪው የህወሃት ቡድን ዜጎች በርሃብ ጠኔ ታመው እየሞቱ እሱ ግን በምሽግ ከዝኖ ታጣቂዎችን እየቀለበ እንደሚያዋጋበት በከፈተብን ጦርነት ማረጋገጥ ተችሏልም ብሏል።

ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ
https://www.youtube.com/channel/UC9lAZ1l0TvJG65R-QeCDHkg
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis