Get Mystery Box with random crypto!

AMN-Addis Media Network

የሰርጥ አድራሻ: @addismedianetwork
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 35.84K
የሰርጥ መግለጫ

This is an official Telegram channal for Addis Media Network (AMN) We trive to be the prime informer of issues. Hence, our motto says so, 'first to inform'
ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ !!
contact us via:- E-mail:- addisaammaa@gmail.com
twitter.com/AmnAddis

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 54

2022-09-23 17:23:42 ታዳጊ አገራት እና የባህር በር የሌላቸው አገራት የምክክር መድረክ በኒውዮርክ እየተካሄደ ነው

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መስከረም 13 ቀን 2014

በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው 77ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የታዳጊ አገራት እና የባህር በር የሌላቸው አገራት ከፍተኛ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

በምክክር መድረኩ አገራቱ እያጋጠሟቸው ያሉ ችግሮችን በትብብር እና በመደጋገፍ መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

የበለጠ ትብብርን ለማበረታታት እና የጋራ ዘላቂ ልማት ለማሳካት የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅፋቶችን ለመቀነስ ቃል ገብተዋል ። የዚህ ቡድን አንዷ አባል ኢትዮጵያም በውይይቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረገች መሆኑን የወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል ።

በመድረኩ የኢትዮጵያን አቋም ያቀረቡት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ አየለ ሊሬ የባህር በር የሌላቸው አገራት በኮቪድ -19፣በአየር ንብረት ለውጥ ፣ በምግብ ፣በኢነርጂ እና ፋይናንስ ቀውስ እየተፈተኑ መሆኑን አመልክተዋል ።

እነዚህ አገራት እያጋጠማቸው ያለውን ችግር ለመፍታት ከአሁን በፊት የተቀመጠውን የዶሃ ፕሮግራም ትግበራ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ማስገባት እንደሚገባ አቶ አየለ በንግግራቸው ገልፀዋል።

አቶ አየለ ኢትዮጵያ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈች ቢሆንም ከፍተኛ የፖለቲካ ቁርጠኝነት በማሳየት የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ አዘጋጅታ በድህነት ቀነሳ፣ስራ ፈጠራ ፣መዋቅራዊ ለውጥ ፣ሰላም እና መልካም አስተዳደርን ለማሻሻል እየሰራች መሆኑን ገልፀዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ያለውን ችግር ለመከላከልም ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብርን በመተግበር 25 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን መናገራቸውንም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል ።
2.5K views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 16:29:27
አምባሳደር ባጫ ደበሌ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የደስታ መልዕክት ለዊሊያም ሩቶ አደረሱ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መስከረም 01/2015
አምባሳደር ባጫ ደበሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ  አዲስ ለተመረጡት የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ያስተላለፉትን የደስታ መልዕክት ለፕሬዝደንቱ ማድረሳቸውን በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በልማት፣ ቀጠናዊ ሠላም እና ፀጥታ እንዲሁም በኢኮኖሚ  ትሥሥር በጋራ መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉም አምባሳደሩ አስታውቀዋል።
1.8K views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 15:46:49
በጂቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን)መስከረም 01/2015
በጂቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ጥሪ አቅርበዋል።

በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የአትዮጵያ ወዳጆች ጳጉሜ 5 የተከበረውን “የአንድነት ቀን” እና የ2015 የአዲሱን ዓመት በድምቀት አክብረዋል።

በጅቡቲ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች “የአንድነት ቀን” በሚል መሪ ቃል ጳጉሜ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ተከብሮ የዋለውን በዓል እና የአዲሱን ዓመት በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር-ገቢ ውስጥ አክብረዋል።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ልዩ-መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ አንድነት፣ ሰላምና ብልጽግና ላይ የተቃጡ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም፤ እነዚህን ፈታኝ ሁኔታዎች ተቋቁማ በበርካታ ዘርፎች ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አንጸባራቂ ድሎችን ማስመዝገቧን አንስተዋል።

የህዝብ የጸና አንድነትና የላቀ ተሳትፎ ምልክት የሆነውን የዓባይ ግድብ ሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት ማጠናቀቅ ሁለተኛው የኃይል ማመንጫ ተርባይን  ስራ መጀመር  ቀዳሚዎቹ የስኬት ተግባራት እንደነበሩ አምባሳደሩ ገልጸዋል።

በጂቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን ለአገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።
2.0K views12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 14:27:17
ለበዓሉ የሚያሰፈልጉ ምርቶች በብዛት መቅረባቸው የበዓል ገበያው የተረጋጋ እንዲሆን ማስቻሉ ተገለፀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መስከረም 01/2015
ለበዓሉ የሚያሰፈልጉ ምርቶች በብዛት መቅረባቸው የበዓል ገበያው የተረጋጋ እንዲሆን ማስቻሉን  የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለፀ ።

የከተማ አስተዳደሩ ለበዓል በተለየ መልኩ የገበያ ዋጋ መረጋጋት እንዲችል አስቀድሞ ከአምራቾች ጋር ትስስር በመፍጠር ምርቶች በስፋት እንዲገቡ ሲሰራ መቆየቱ ተገልጿል።

በዚህም ለዘመን መለወጫ የቁም ከብቶች የእንስሳት ተዋፅኦዎች ፤የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች እንዲሁም የተለያዩ የእህል ሰብሎች በሽማች ማህበራትና በነጋዴዎች በብዛት ማቅረብ መቻሉን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያሳያል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ ፤በተለይ በዚህ የአዲስ አመት በዓል አላግባብ ዋጋ በመጨመር የዋጋ ንረት ለማስከተል የሚሞክሩ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር አስተዳደሩ ቀደም ሲል በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በርካታ ምርት በማስገባት ገበያው እጥረት እንዳይገጥምና ዋጋውም ሚዛናዊ እንዲሆን ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በከተማዋ በሚገኙ የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት እንዲሁም በየአካባቢው የተቋቋሙ የእሁድ ገበያዎች  ሰፊ የገበያ አማራጭ በመሆን ገበያውን ሚዛን መጠበቅ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

አሁንም ህብረተሰቡ ከእነዚህ አማራጮች በመሸመት ከህገወጥ ነጋዴዎች ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
2.2K views11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 13:31:45
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ለአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ 

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መስከረም 01/2015
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት ለኢትዮጵያ  አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሊቀመንበሩ በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፦ "አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የሰላም፣ የእርቅ እና የልማት እንዲሆን እመኛለሁ" ብለዋል፡፡
2.3K views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 12:10:24
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት ለጡረተኞች እና አቅመ ደካሞች የምሳ ግብዣ አደረጉ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መስከረም 01/2015
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት ለጡረተኞች እና አቅመ ደካሞች የምሳ ግብዣ ማድረጋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
2.6K views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 10:52:43
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አዲስ በተገነባው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማእከል ድጋፍ ከሚሹ ወገኖች ጋር በዓሉን በጋራ አሳለፉ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) መስከረም 1/2015

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በ60 እና 90 ቀናት ፕሮጀክት በቢኬጂ ፋውንዴሽን በተገነባው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማእከል በመገኘት ድጋፍ ከሚሹ ወገኖች ጋር ዓመት በአልን አሳልፈዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች እንደተናገሩት፦ ዛሬ አዲሱ አመት ገና ሲጀምር ከእናንተ ጋር ማዕድ በመቋደስ ለእናንተ ፍቅር በመስጠት ማሳለፍ መታደል ነው፤ ትልቅ ደስታንም የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡

ወገን ለወገን  መተሳሰብ እሴታችን ማደግ ያለበት ለትውልድ  መተላለፍ ያለበት ነው ያሉት ከንቲባዋ፤
ለእናንተ ድጋፍ አድርጎ ለእናንተ ያለውን አቋድሶ፤ የጎደለበት እንደሌለ አውቃለው  ይልቁንም ተባርከዋል ሲሉም  ድጋፍ ያደረጉትን አመስግነዋል፡፡

የቢኬጂ ፋውንዴሽን ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ በበኩላቸው፤  ድርጅታቸው በማህበራዊ ግልጋሎት በትምህርት በጤና በስፖርት የተለያየ ሃገራዊ ጉዳዮች እየተሳተፈ እንደሚገኝ ገልጸው፦ ይህም የምገባ ማእከል በ20 ሚሊዮን ብር ተገንብቶ ወደ ተግባር መግባቱን አስታውሰዋል፡፡

አሁንም በምገባ ማእከሉ ሴቶችን አደራጅቶ ወደ ስራ በማስገባት  የ800 ሺህ ብር እቃ ምገባውን የሚያከናውኑበት እንዲሁም ለስራ ማስጀመርያ የ200 ሺህ ብር ድጋፍ እንደሚያስረክቡም መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የቂርቆስ ቢኬጂ ፋውንዴሽን  የተስፋ ብርሃን  የምገባ ማእከልም በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የማይችሉ ዜጎች የሚመገቡበት መሆኑም ተገልጿል፡፡
2.7K views07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 10:16:13 ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ ዳይሬክተር ጀነራል ኮሎኔል አብዱረህማን አሊ ጋር ተወያዩ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ጳጉሜን 3/2014

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል አዲሱን የጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ ዳይሬክተር ጀነራል ኮሎኔል አብዱረህማን አሊን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና የጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ ድንበር ዘለል ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ፖሊስ ተቋማት የጋራ የፀጥታ ግብረ ኃይል አቋቁመው በድንበር አካባቢ የጋራ ጥበቃ በማድረግ የጀመሩትን ተግባራት የገመገሙ ሲሆን እስካሁን የተገኙ ውጤቶችንም አጠናክረው ለማስቀጠል ተስማምተዋል።

በሁለቱ ሀገራት የወንጀል ተግባር ፈጽመው የሚሸሸጉ ተጠርጣሪዎችን ለፈላጊው ሀገር አንዱ ለአንዱ አሳልፎ ለመስጠት የተጠናከረ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ሁለቱ የፖሊስ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በውይይታቸው ወቅት አንስተዋል።

ሁለቱ የፖሊስ ተቋማት በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር (የተለያዩ ሀገራት ገንዘብ) ላይ በወሰዱት እርምጃ ከፍተኛ ውጤት መገኘቱንና ይህንን የወንጀል መከላከል ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በምክክር መድረኩ ላይ ገልጸዋል።

የሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢን ከየትኛውም የሽብርና ከሌሎች የወንጀል ተግባራት የማጽዳት ሥራ በጋራ ተቀናጅተው እየሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል።

የጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ ዳይሬክተር ጀነራሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ቴክኖሎጂ ማስፋፊያን ጎብኝተው በስምሪት ላይ ላሉት ለፖሊስ አመራርና አባላትም የፖሊስ ሥራ ከባድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዘመናዊ መገናኛ ራድዮ አማካኝነት መልዕክት ማስተላለፋቸውንም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።
95 views07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 09:58:51
በዛሬው ዕለት የሰላም ቀንን በማስመልከት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር "የሰላም ጎዳና" በመባል በተሰየመው መንገድ (ከኡራኤል ወደ ወሎ ሰፈር) የተደረገ የእግር ጉዞ በፎቶ፡-

ፎቶ ምንጭ፡- ከከተማ አስተዳደሩ
472 views06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 09:16:17 ከኡራኤል ወደ ወሎ ሰፈር አዲስ የተገነባው የአስፋልት መንገድ የሰላም ጎዳና ተብሎ ተሰየመ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ጳጉሜን 3/2014
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኡራኤል ወደ ወሎ ሰፈር ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የተገነባውን አዲስ የአስፋልት መንገድ የሰላም ጎዳና ብሎ ሰየመ፡፡

በመርሀግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር፣ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቀንዓ ያዴታ እና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡

የሰላም ቀንን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቅርቡ መርቀውት ለሕዝባዊ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጎ የነበረው ከኡራኤል ወደ ወሎ ሰፈር ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የተገነባው የአስፓልት መንገድን የሰላም ጎደና ብለው ሰይመውታል።

በሰላም ጎዳና ስያሜ መረሀግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት፡- ዛሬ መንገድ የመሰየማችን ዓላማ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ጉዞ የሰላም መሆኑን ለተቀረው ዓለም ማመላከት ነው ብለዋል።

ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያ አስቀድማ ለሰላም ዘርግታው የነበረው እጇ አለመታጠፉን ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር አብረው ለሚወጉን አካላት ሁሉ ለማሳወቅ እንወዳለን ነው ያሉት ከንቲባዋ፡፡

የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለሞ በበኩላቸው፡- ከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች ለሰላም ለሰጡት የላቀ ስፍራና ለጎዳናው ስያሜ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አቶ ብናልፍ ለሰላም አስፈላጊውን ሁሉ መስዋዕትነት ከፍለን ሁላችንም በአንድነት የአገራችንን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ይጠበቅብናል ያሉ ሲሆን፤ በሁሉም ረገድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ወጥተው የዕለት ተግባራቸውን በተሳካ ሁኔታ እንዲያከናውኑ ሰላም ቁልፍ እሴት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም ለሰላም መረጋገጥ በየደረጃው አቅማችን በሚፈቅደው ሁሉ ኃላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል ማለታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመርሀግብሩ ላይ የተገኙት የተለያዩ የሐይማኖት መሪዎችም፤ ኢትዮጵያ ወጣቶች ሰርተው የሚለወጡባትና አረጋዊያን የሚጡሩበት አገር እንድትሆን ከሁሉም በላቀ የኃይማኖቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሐይማኖት መሪዎቹ ለአገር ብልጽግና መጸለይን፣ የሕዝብ ለሕዝብ ወንድማማችነትና ትስስር እንዲጎለብት መስራትን ጨምሮ በላቀ ግብረገብነት ወጣቶች የዕድሜ ታላላቆቻቸውን የሚያከብሩ፣ በአንድነት የሚያምኑና አገራቸውን የሚወዱ እንዲሁም በሁሉም ረገድ ለሰላም መረጋገጥ አብዝተው የሚጥሩና አገራችን ከውስጥም ከውጪም የሚቃጣባትን ጥቃት አቅማቸው በሚፈቅደው ሁሉ የሚቃወሙ እንዲሆኑ አድርገው ኃይማኖቶች ማስተማርና መምከር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ
https://www.youtube.com/channel/UC9lAZ1l0TvJG65R-QeCDHkg
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis
1.0K viewsedited  06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ