Get Mystery Box with random crypto!

ከኡራኤል ወደ ወሎ ሰፈር አዲስ የተገነባው የአስፋልት መንገድ የሰላም ጎዳና ተብሎ ተሰየመ አዲስ | AMN-Addis Media Network

ከኡራኤል ወደ ወሎ ሰፈር አዲስ የተገነባው የአስፋልት መንገድ የሰላም ጎዳና ተብሎ ተሰየመ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ጳጉሜን 3/2014
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኡራኤል ወደ ወሎ ሰፈር ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የተገነባውን አዲስ የአስፋልት መንገድ የሰላም ጎዳና ብሎ ሰየመ፡፡

በመርሀግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር፣ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቀንዓ ያዴታ እና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡

የሰላም ቀንን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቅርቡ መርቀውት ለሕዝባዊ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጎ የነበረው ከኡራኤል ወደ ወሎ ሰፈር ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የተገነባው የአስፓልት መንገድን የሰላም ጎደና ብለው ሰይመውታል።

በሰላም ጎዳና ስያሜ መረሀግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት፡- ዛሬ መንገድ የመሰየማችን ዓላማ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ጉዞ የሰላም መሆኑን ለተቀረው ዓለም ማመላከት ነው ብለዋል።

ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያ አስቀድማ ለሰላም ዘርግታው የነበረው እጇ አለመታጠፉን ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር አብረው ለሚወጉን አካላት ሁሉ ለማሳወቅ እንወዳለን ነው ያሉት ከንቲባዋ፡፡

የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለሞ በበኩላቸው፡- ከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች ለሰላም ለሰጡት የላቀ ስፍራና ለጎዳናው ስያሜ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አቶ ብናልፍ ለሰላም አስፈላጊውን ሁሉ መስዋዕትነት ከፍለን ሁላችንም በአንድነት የአገራችንን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ይጠበቅብናል ያሉ ሲሆን፤ በሁሉም ረገድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ወጥተው የዕለት ተግባራቸውን በተሳካ ሁኔታ እንዲያከናውኑ ሰላም ቁልፍ እሴት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም ለሰላም መረጋገጥ በየደረጃው አቅማችን በሚፈቅደው ሁሉ ኃላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል ማለታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመርሀግብሩ ላይ የተገኙት የተለያዩ የሐይማኖት መሪዎችም፤ ኢትዮጵያ ወጣቶች ሰርተው የሚለወጡባትና አረጋዊያን የሚጡሩበት አገር እንድትሆን ከሁሉም በላቀ የኃይማኖቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሐይማኖት መሪዎቹ ለአገር ብልጽግና መጸለይን፣ የሕዝብ ለሕዝብ ወንድማማችነትና ትስስር እንዲጎለብት መስራትን ጨምሮ በላቀ ግብረገብነት ወጣቶች የዕድሜ ታላላቆቻቸውን የሚያከብሩ፣ በአንድነት የሚያምኑና አገራቸውን የሚወዱ እንዲሁም በሁሉም ረገድ ለሰላም መረጋገጥ አብዝተው የሚጥሩና አገራችን ከውስጥም ከውጪም የሚቃጣባትን ጥቃት አቅማቸው በሚፈቅደው ሁሉ የሚቃወሙ እንዲሆኑ አድርገው ኃይማኖቶች ማስተማርና መምከር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ
https://www.youtube.com/channel/UC9lAZ1l0TvJG65R-QeCDHkg
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis