Get Mystery Box with random crypto!

'የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ለሰላም ያለው አቋም ዘላቂና የማይናወጥ ነው' -ከተማ አስተዳደሩ | AMN-Addis Media Network

"የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ለሰላም ያለው አቋም ዘላቂና የማይናወጥ ነው" -ከተማ አስተዳደሩ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ጳጉሜን 3/2014

የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ለሰላም ያለው አቋም ዘላቂና የማይናወጥ ነው ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለጸ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ሰላምን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልእክት፡- የሰላም ዋጋው ውድ ነው፤ ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት ነው፤ ሰላም ሀገር እንዲኖረን፤ ሰርተን እንድንኖር፤ ወልዶ ለማሳደግ፤ የሰው ልጅ ህልውናው እንዲረጋገጥ፤ በእርጋታ ማህበራዊ ህይወቱን እንዲመራ በእጅጉ ወሳኝ ነው ብሏል።

ከብዙ ውድ ነገሮቻችን ሁሉ የሚበልጠው ሰላም መሆኑን የጠቀሰው ከተማ አስተዳደሩ፤ ከእራስ አልፎ ለአህጉር፤ ከአህጉርም አልፎ ለዓለም ሰላም አንዲሆን በርካታ ስራ ከሰራን በአህጉራዊ እና በዓለም ዓቀፍ መድረክ ላይ በእውቅና እና በምስጋና የተመሰከረልን ህዝብ እና ሀገር እንሆናለን! ብሏል።

ሰላም ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠዉ ተግባር በመሆኑ ሀገራችን ለራስዋ ሰላምና ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት ሰላም ግንባር ቀደም ሚናዋን እየተወጣች እንደሆነች ይታወቃል፡፡

ለባለፉት አመታት የሀገራችንን እና የህዝባችንን ሰላም ለማደፍረስ በርካታ እኩይ ጥቃቶች ደርሰውብናልም ነው ያለው ከተማ አስተዳደሩ።

የከተማችን ነዋሪ ሰላም ወዳድ ህዝብ ነው፤ የራሱንና አካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ ብዙ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፤ አሁንም እያከናወነ ይገኛልም ብሏል።

የከተማዋን ሰላም የማስጠበቅ ሀላፊነት የሁሉም ማህበረሰብ መሆኑን የጠቀሰው ከተማ አስተዳደሩ፤ ከህዝቡ የተወጣጡ የሰላም ሠራዊት ግንባታ በማደራጀት ከተማዋ በሁሉም ረገድ ሰላሟ የተጠበቀ እንዲሆን ተግቶ መስራት እንደሚያስፈልግም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

የከተማችን ሰላም የምናስጠብቀው እኛው እራሳችን ነን፤ የሀገራችን ሰላም ለሁለንተናዊ እድገታችን ምሰሶ ነው፤ ለዘላቂ ሰላማችን በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ያለውን የኢትዮጵያ የሰላም አምድ የሆነውን ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን እኔ የሰለም ዘብ ነኝ ብለን ለሰላማችን እንቁም ሲልም መልዕክቱን አስተላልፏል።

ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ
https://www.youtube.com/channel/UC9lAZ1l0TvJG65R-QeCDHkg
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis