Get Mystery Box with random crypto!

ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከአስተዳደሩ አመራሮች ጋር የ'ሙያ ኢትዮጵያ' ሀላፊነቱ የተወሰነ | AMN-Addis Media Network

ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከአስተዳደሩ አመራሮች ጋር የ"ሙያ ኢትዮጵያ" ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን ጎበኙ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጳጉሜን 2ቀን 2014

ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ከፍተኛ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች አምራቾችንና አምራችነትን ለማበረታታት የ"ሙያ ኢትዮጵያ" ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን ሠጎብኘታቸውን የአስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።

የሸክላ እና የሽመና ውጤቶችን ወደ ውጭ ሀገር የሚልከው ሙያ ኢትዮጵያ፣ ለበርካታ የዕደ-ጥበብ ባለሙያዎች የስራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ የውጭ ምንዛሬ ለሀገራችን ማስገኘት የቻለ ማህበር ነው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ ከተማ አስተዳደሩ በጥበበኛ እጆች የሚሰሩ መሰል የዕደ-ጥበብ ስራዎችን ያበረታታል፣ ድጋፍ ያደርጋልም ብለዋል።

የሙያ ኢትዮጵያ ባለቤት፣ ስራ አስኪያጅና ዲዛይነር ወይዘሮ ሳራ አበራ በበኩላቸው፣ ለጥበበኞች ልዩ ስልጠና በመስጠት የስራ ዕድል በመፍጠራቸው ከማገኘው ገቢ የበለጠ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል ብሏል የጽህፈት ቤቱ መረጃ ።