Get Mystery Box with random crypto!

በጂቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እን | AMN-Addis Media Network

በጂቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን)መስከረም 01/2015
በጂቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ጥሪ አቅርበዋል።

በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የአትዮጵያ ወዳጆች ጳጉሜ 5 የተከበረውን “የአንድነት ቀን” እና የ2015 የአዲሱን ዓመት በድምቀት አክብረዋል።

በጅቡቲ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች “የአንድነት ቀን” በሚል መሪ ቃል ጳጉሜ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ተከብሮ የዋለውን በዓል እና የአዲሱን ዓመት በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር-ገቢ ውስጥ አክብረዋል።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ልዩ-መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ አንድነት፣ ሰላምና ብልጽግና ላይ የተቃጡ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም፤ እነዚህን ፈታኝ ሁኔታዎች ተቋቁማ በበርካታ ዘርፎች ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አንጸባራቂ ድሎችን ማስመዝገቧን አንስተዋል።

የህዝብ የጸና አንድነትና የላቀ ተሳትፎ ምልክት የሆነውን የዓባይ ግድብ ሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት ማጠናቀቅ ሁለተኛው የኃይል ማመንጫ ተርባይን  ስራ መጀመር  ቀዳሚዎቹ የስኬት ተግባራት እንደነበሩ አምባሳደሩ ገልጸዋል።

በጂቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን ለአገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።