Get Mystery Box with random crypto!

ለበዓሉ የሚያሰፈልጉ ምርቶች በብዛት መቅረባቸው የበዓል ገበያው የተረጋጋ እንዲሆን ማስቻሉ ተገለፀ | AMN-Addis Media Network

ለበዓሉ የሚያሰፈልጉ ምርቶች በብዛት መቅረባቸው የበዓል ገበያው የተረጋጋ እንዲሆን ማስቻሉ ተገለፀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መስከረም 01/2015
ለበዓሉ የሚያሰፈልጉ ምርቶች በብዛት መቅረባቸው የበዓል ገበያው የተረጋጋ እንዲሆን ማስቻሉን  የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለፀ ።

የከተማ አስተዳደሩ ለበዓል በተለየ መልኩ የገበያ ዋጋ መረጋጋት እንዲችል አስቀድሞ ከአምራቾች ጋር ትስስር በመፍጠር ምርቶች በስፋት እንዲገቡ ሲሰራ መቆየቱ ተገልጿል።

በዚህም ለዘመን መለወጫ የቁም ከብቶች የእንስሳት ተዋፅኦዎች ፤የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች እንዲሁም የተለያዩ የእህል ሰብሎች በሽማች ማህበራትና በነጋዴዎች በብዛት ማቅረብ መቻሉን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያሳያል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ ፤በተለይ በዚህ የአዲስ አመት በዓል አላግባብ ዋጋ በመጨመር የዋጋ ንረት ለማስከተል የሚሞክሩ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር አስተዳደሩ ቀደም ሲል በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በርካታ ምርት በማስገባት ገበያው እጥረት እንዳይገጥምና ዋጋውም ሚዛናዊ እንዲሆን ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በከተማዋ በሚገኙ የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት እንዲሁም በየአካባቢው የተቋቋሙ የእሁድ ገበያዎች  ሰፊ የገበያ አማራጭ በመሆን ገበያውን ሚዛን መጠበቅ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

አሁንም ህብረተሰቡ ከእነዚህ አማራጮች በመሸመት ከህገወጥ ነጋዴዎች ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡