Get Mystery Box with random crypto!

AMN-Addis Media Network

የሰርጥ አድራሻ: @addismedianetwork
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 35.84K
የሰርጥ መግለጫ

This is an official Telegram channal for Addis Media Network (AMN) We trive to be the prime informer of issues. Hence, our motto says so, 'first to inform'
ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ !!
contact us via:- E-mail:- addisaammaa@gmail.com
twitter.com/AmnAddis

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 61

2022-09-02 14:14:18
አሸባሪው ሕወሓት በወልቃይት ግንባር ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት የሽብር ቡድኑ ምርኮኞች ተናገሩ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 27 ቀን 2014

አሸባሪው ሕወሓት በወልቃይት ግንባር በከፈተው ማጥቃት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት የሽብር ቡድኑ ምርኮኞች ተናገሩ


የሽብር ቡድኑ ሕወሓት በወልቃይት ግንባር በከፈተው ማጥቃት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት የሽብር ቡድኑ ምርኮኞች ተናገሩ።

የሽብር ቡድኑ የትግራይ ወጣቶችና ታዳጊዎችን በየግንባሩ ለጦርነት በመማገድ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል ።

አሸባሪው ሕወሓት ያለንን አቅም ሁሉ ተጠቅመን ወልቃይትና ራያን አስመልሰን ታላቋ ትግራይን እንመሰርታለን ብሎ ጦርነት ቢያስገባንም ሳናሳካ ሙት ፣ ቁስለኛና ምርኮኛ ለመሆን መገደዳቸውን ምርኮኞቹ መናገራቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ማህበራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
3.7K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 14:05:38
ትዴፓ አሸባሪው ህወሐት በህዝብና አገር ላይ የጀመረውን ጦርነት አወገዘ


አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 27 ቀን 2014

የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) አሸባሪው ሕወሓት በህዝብና አገር ላይ የጀመረውን የሶስተኛ ጊዜ ጦርነት በጽኑ አወገዘ።

ትዴፓ በመግለጫው እንዳመለከተው፤ አሸባሪው ሕወሓት ተቀባይነት የማይኖራቸው ቅድመ ሁኔታዎችን በመደርደር የሰላም አማራጭ እንዳይሳካ አድርጓል።

አሸባሪው ሕወሓት ፀረ ሰላም መሆኑንና ለህዝብም ደንታ እንደሌለው፣ ዘራፊና አሸባሪ ስለመሆኑ መላው ዓለም መገንዘቡን አመልክቷል።

ጦርነቱን እንደጀመረ የፈጸመው የ570 ሺህ ሊትር በላይ የነዳጅ ዝርፊያ ጸረ ህዝብ መሆኑን ያሳየበት ተግባር መሆኑን ጠቅሷል።

ኢዜአ እንደዘገበው አሸባሪው ሕወሓት በህዝብና አገር ላይ የጀመረውን ጦርነት ያወገዘው ትዴፓ፤ በጦርነቱ ለሚደርሰው ጥፋት ሁሉ ተጠያቂው ሕወሓት መሆኑን ገልጿል።

መንግስት የአገርንና የህዝብን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚወስደውን ርምጃ እንደሚደግፍ ገልጾ፤ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ አረጋግጧል።

መላው ኢትዮጵያዊ በዚህ አገርን የማስከበርና የህዝብን ደህንነት የማረጋገጥ እርምጃ ከመንግስት ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ አቅርቦ፤ በተለይም የትግራይ ህዝብ ህወሐት ጦርነትን እንዲያቆምና የሰላም አማራጩን እንዲቀበል ለማድረግ፣ የልጆቹን ደም ይገታ ዘንድ በህወሐት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ እምቢታ እንዲቀሰቅስ ጥሪ አቅርቧል።

እንዲታጠቅ የተገደደውና ለግለሰቦች የስልጣንና የጥቅም ፍላጎት በማለቅ ላይ ያለው ወጣት ለወላጆቹ ሰላም፣ ለራሱም ነፃነት ጥቅምና እድገት በማሰብ በተመቸው መንገድ አፈሙዙን ወደ ጨቋኞቹ የህወሐት አመራሮች እንዲያዞር ወይም በሰላም እጁን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል እንዲሰጥ በመግለጽ ትዴፓ መልዕክቱን አስተላልፏል ።
3.5K views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 13:07:37
ሕሊናቸውን ጨጓራቸው ውስጥ የከተቱየአሸባሪው ሕወሓት ተካፋዮቹ እየተለዩ ነው

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 27 ቀን 2014

አሸባሪው ሕወሓት በሕዝብ አመጽ ከስልጣን መባረሩን ተከትሎ አገር ለማፍረስ ሲነሳ ለእኩይ አላማው ስኬት እንደዋና ማስፈጸሚያ የተማመነው የዘረፈውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ስራ ለይ ማዋል ነው።

ይህንንም በሚገባ ጥቅም ላይ አውሎታል ማለት ይቻላል ።ከሃዲዎችን በገንዘብ በመግዛት አገር የማፍረስ ፕሮፖጋንዳውን ሲያሠራጭ ቆይቷል።

ሕወሓት ያስፈጽሙልኛል በሚል ከመረጣቸው ግለሠቦች መካከል
በተለይ ለሆዳቸው ያደሩት ፤ፀጋዬ አራርሳ፣ህዝቄል ገቢሳ፣እና ኤርሚያስ ለገሰ ተጠቃሾች ናቸው።

እነዚህ አካላት ህሊናቸውን ጨጓራቸው ውስጥ ከከተቱ የቆዩ ቢሆንም በዚህ ደረጃ ቋሚ የሕወሓት ተከፋይ መሆናቸውን ለማመን የሚቸገሩ ቢኖሩ የሚገርም አይደለም።

ነገር ግን "ጉድ እና ጅራት ወደኋላ ነው" እንደሚባለው የአሸባሪው ሕወሓት ቅጥረኛ መሆናቸው ገሀድ ወጥቷል።

ከትግራይ ሚዲያ ሀውስ የሒሳብ ቁጥር ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሠሩት ልክ እየተከፈላቸው መሆኑ የሚያሳዩ ከመረጃ ያለፉ ማሥረጃዎች መውጣት ጀምረዋል።
3.6K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 12:00:38
ኢትዮጵያዊያን በብሔርና በሀይማኖት ሳንከፋፈል በአንድነት መቆም እንዳለብን ተገለጸ


አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 27 ቀን 2014


ኢትዮጵያዊያን በብሔርና በሀይማኖት ሳንከፋፈል በአንድነት ለሀገራችን ህልውና በደጀንንት መቆም እንዳለብን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ ገለጹ፡፡

አቶ አህመድ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለገንዘብ ሚኒስቴርና ለተጠሪ ተቋማት ሰራተኞችና አመራሮች ማብራሪያ ኢትዮጵያዊያን በብሔርና በሀይማኖት ሳንከፋፈል በአንድነት ለሀገራችን ህልውና በደጀንነት መቆም አለብን ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የመንግስት ሰራተኛው የእለት ተዕለት ስራውን በሀላፊነት ስሜት ተግባራዊ ከማድረጉም ባሻገር ለሶስተኛ ጊዜ የተከፈተብንን ጦርነት ለመመከትና በድል ለማጠናቀቅ ለመከላከያ ሰራዊታችን የሎጂስቲክና የስነልቡና ድጋፍ በመስጠት ደጀንነቱን እንዲያረጋጥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተለይም የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ሰራተኞችና አመራሮች ከልማት አጋሮች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ተጠቅመው አለም አቀፉ ማህበረሰብ በወራሪው ሀይል ላይ ጫና በማሳረፍ ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጣ ግፊት እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው ወረራውን ለመቀልበስና የሀገርን ህልውና ለማስቀጠል በሚደረገው ትግል በደጀንነት ከመቆም በተጓዳኝ ባለፉት አመታት በሀገራዊ ለውጡ የተመዘገቡትን ኢኮኖሚያዊ ስኬቶችን ለማስቀጠል ሳይዘናጉ መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

መንግስት ለሰላም የዘረጋውን እጅ ምን ጊዜም እንደማያጥፍ ዶ/ር ኢዮብ አስታውሰው መንግስት የ120 ሚሊዮን ዜጎችን የመጠበቅ ሀላፊነት ስላለበት ወረራውን እየተከላከለ ለዘላቂ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለመረጋገጥ ከእያንዳንዱ ሀገር ወዳድ ዜጋ ይጠበቃል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡
3.4K views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 10:58:28 ከቀረጥ ነፃ የቆዳ እና ቆዳ ውጤቶች መሸጫ ሱቅ በይፋ ተከፈተ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን)ነሃሴ 27/201

4የኢንዱስተሪ ሚኒስቴር ከአጋር አካላቱ ጋር በመሆን በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከቀረጥ ነፃ የቆዳ እና ቆዳ ውጤቶች መሸጫ ሱቅ በይፋ አስመርቋል።

የመሸጫ ሱቁ መከፈት ዋናኛ ዓላማም የኢትዮጵያን ምርቶች ማስተዋወቅ እና የዘርፉን ወጪ ንግድ ማሳደግ እንደሆነ ተገልጿል።

የኢንዱትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው፣ በዘርፉ ሁለንተናዊ እድገት ለማምጣት ከአጋር አካላት ጋር እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

የወጪ ንግድ ገቢን፣ የማምረት አቅም አጠቃቃምን በማሳደግ እና የገጽታ ግንባታ ሥራ በመሥራት በኩል እንደ ሀገር ለተጀመረው ኢትዮጵያ ታምርት አገራዊ ንቅናቄ መሳካት የዚህ ፕሮጀክት እውን መሆን አስተዋጽኦ እንዳለውም ጠቁመዋል።

ምንም እንኳን ፕሮጀክቱ ጅምር ቢሆንም ባለፉት ሁለት ወራት 200 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከሽያጭ ማዕከሉ መገኘቱን እና አበረታች ውጤቶች እየታየ መሆኑን ገልጻዋል።

በ2014 በጀት ከቆዳ እና የቆዳ ውጤቶች ወጪ ንግድ 40 ነጥብ 6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መገኘቱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ዓለም አቀፍ የጃፓን ኮርፖሬሽን (JICA) የኤክስፖርት ማስተዋወቅ ፐሮጀክት ዋና አማካሪ ኖሪክ ናጋይ፣ ድርጅታቸው የኢትዮጵያን ቆዳ እና ቆዳ ውጤቶች በተለይም የሃይላንድ ቆዳ በሚል የሚታወቀውን ብራንድ ለዓለም ገበያ ለማስተዋወቅ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረረገ ነው ማለታቸውን የሚኒስትሩ መረጃ ያመለክታል።
3.4K views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 21:41:06
አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ለተቸገሩ የትግራይ ወገኖች የተለገሠን ምግብ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለጦርነት እየተጠቀመበት ነዉ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 26 ቀን 2014

አሸባሪው የሕወሓት ቡድን አለም አቀፍ የርዳታ ድርጅቶች ለተቸገሩ የትግራይ ወገኖቻችን የሚለግሱትን ምግብ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለጦርነት እየተጠቀመበት መሆኑ ተመለከተ።

አሸባሪው ሕወሓት ከአለም አቀፍ ድርጅቶች የሚላኩ ምግቦችን ከህዝቡ ጉሮሮ እየቀማ ለጦርነት ማዋሉ ለህዝቡ ደንታ የሌለው መሆኑ ማሳያ ነው።

ይህን የርዳታ እህል ከተረጅዎች ጉረሮ በመንጠቅ ለሽብር ቡድኑ አባላት ቀለብ እያዋለው መገኘቱን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መረጃ አመልክቷል ።
2.3K viewsedited  18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:51:30 የትግራይን ህዝብ ለዳግም ጦርነት እየዳረገ ያለው አሸባሪው ሕወሓት እየፈፀመ ያለው ጥፋት፣ ህዝባዊ ውግንና እንደሌለውና አሸባሪነቱን በተግባር ያረጋገጠ ነው-የመከላከያ ሚኒስትር

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 26 ቀን 2014

የትግራይን ህዝብ ወደ ዳግም ጦርነት ያስገባው አሸባሪው ሕወሓት ህዝባዊ ውግንና የሌለውና አሸባሪነቱን የሚያሳይ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሐም በላይ ተናገሩ።

ከሽብርና ጦርነት ውጭ ሌላ ህልውና የሌለው አሸባሪው ህወሃት ለ3ኛ ጊዜ የትግራይን ህዝብ ወደ ጦርነት ማስገባቱንም ገልጸዋል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሐም በላይ በመግለጫቸው የተዘረጋን የሰላም አማራጭ በመናቅ ሌላ ዙር ጦርነት ማወጁ የቡድኑ ተፈጥሯዊ ባህሪ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

ከትግራይ ህዝብ ጥያቄ በመፍራትና የሌሎች ፀረ ኢትዮጵያ ሃይሎችን ፍላጎት ለማሳካት በማለም ዳግም የጀመረው ጦርነት መሆኑንም ገልጸዋል።

አሸባሪው ህወሃት ከአፈጣጠሩ ጀምሮ የተለየ ሀሳብና አጀንዳ መቀበልና መስማት የማይሻ መሆኑን የሚናገሩት ዶክተር አብርሃም፤ የተለየ ሃሳብ ያለውን አካል እየገደለና እያስወገደ የመጣ ቡድን መሆኑን አስረድተዋል።

በንግግርና በሰላም አምኖ ችግር የፈታበት አንዳችም የታሪክ አጋጣሚ የለም ሲሉም ተናግረዋል ።

አሸባሪ ቡድኑ በቀሰቀሰው ጦርነት የትግራይ ህዝብ ክፉኛ መጎዳቱን አስታውሰው ህዝቡ ሰላም ባለማግኘቱ ጥያቄዎችን የማቅረብ እድል መነፈጉንም ይናገራሉ።

የትግራይ ህዝብ ሰላም ካገኘ በርካታ ጥያቄዎችን ያነሳል በሚል ስጋት የሰላም በሮችን በመዝጋት በጦርነት አማራጭ መቀጠሉን ገልጸዋል።

በዚህም ቡድኑ "ልጆቻችን የት አሉ" የሚለውን የክልሉን ህዝብ ጨምሮ በባለፈው ጦርነት ህዝቡ የደረሰበትን ጉዳት ስለሚጠይቅና ዕድሜዬ ያጥራል በማለት በስጋት ውስጥ ሆኖ እየፈፀመ ያለው ወንጀል መሆኑን ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል ጦርነቱ የትግራይ ህዝብ ሳይሆን የኢትዮጵያን አንድነትና ሰላም የማይፈለጉ ታሪካዊ ጠላቶች የቤት ስራን ተቀብሎ እየሰራበት ያለ ነው ብለዋል።

የትግራይ ህዝብ የጦርነትን አውዳሚነት በታሪኩ የተረዳ ሰላም ፈላጊ ህዝብ መሆኑን ገልጸው የጥፋት ቡድኑ ባለው ድብቅ ፍላጎት ሀሰተኛ ፕሮፓጋነዳ እየነዛ ህዝቡን ለሌላ ዕልቂት እየዳረገው መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ሕወሓት የሀሰት ትርክትና ፕሮፖጋንዳ በመፍጠር የትግራይ ክልል ህዝብ ለዘመናት በሠላምና በአንድነት አብሮ ከኖረው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመለያየት እየሰራ መሆኑን ነው ያስረዱት።

የሽብር ቡድኑ በሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት መንግሥት ረጅም እርቀት ተጉዞ የሠላም ጥረት ማድረጉንም ጠቅሰዋል።

አሁንም ቢሆም መንግሥት ለሠላም የዘረጋውን እጅ ሳያጥፍ ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት እንዲመጣ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግስት በተደጋጋሚ የሰላም አማራጭን ቢያቀርብም አሸባሪው ሕወሓት የሰላምን መንገድ በመዝጋት በጥፋት እንቅስቃሴው መቀጠሉን ገልጸዋል።

መንግስት የዘረጋውን የሰላም እጅ በመግፋት የትግራይን ህዝብ በማደናገርና በማስገደድ ወደ ሌላ ዙር ጦርነት ያስገባው ተጠያቂነት እንዳይኖር አጀንዳ ለመፍጠር እንደሆነም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በጀግንነቱ፣ በዲስፕሊኑና በህዝባዊነቱ የሚታወቅ ሰራዊት እንደሆነ ገልጸው፤ከለውጡ በኋላም ሰራዊቱ በዕውቀት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሚመራና ኢትዮጵያን የሚመስል ሰራዊት ስለመገንባቱ ገልጸዋል።

የኢፌዴሪ የአገር መከላከያ ሠራዊት አሸባሪውን ሕወሓት ጨምሮ ከማንኛውም ወገን የሚሰነዘርን ጥቃት በብቃት መመከት በሚያስችል ቁመና ላይ የሚገኝ መሆኑንም ሚኒስትሩ ማረጋገጣቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
2.9K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:37:29
ዲፕሎማቶች ሀገር በማዳን እንቅስቃሴ ውስጥ ኃላፊነታችንን በብቃት መወጣት ይገባናል"-አምባሳደር ብርቱካን አያኖ


አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 26 ቀን 2014

""ዲፕሎማቶች የተሰጠንን ተልዕኮ በብቃት በመተግበር ሀገር በማዳን እንቅስቃሴ ውስጥ ኃላፊነታችንን መወጣት ይገባናል" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገለጹ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኞችና ተጠሪ ተቋማት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ባደረጉት ንግግር÷ ሁሉም ሠራተኞች ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን እውነታ እንዲገነዘብ በማድረግ ለሀገራቸው ሁለተናዊ ተሳትፎ በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸዊ አሳስበዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰላማዊ መፍትሔ ረጅም ርቀት መጓዙን አብራርተው፥ ለግጭቱ ዳግም መቀስቀስ ሽብርተኛው ሕወሓት መንስኤ መሆኑን ጠቅሰዋል።

መንግሥት በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ሥር ለሚደረግ የሰላም ድርድር ዝግጁ መሆኑንም ጠቁመዋል ።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም መንግሥት የሰላምን አማራጭ ቀዳሚ ማድረጉ ትክክል መሆኑን ገልጸው፥ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ለአገራቸው የሚችሉትን ለማበርከት በትጋት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን መጠቆማቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
2.7K views17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:18:43
ውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሃገራቸውን ማገዝ እንዲችሉ የተከፈቱ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥሮች፤

Euro- 1000439142832 (ዩሮ)
Usd -1000439142786 (ዶላር)
Gbp -1000443606304 (ፓውንድ
2.5K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 18:25:30 "የኢትዮጵያን ትንሳኤ ከማረጋገጥ ሊያስቆመን የሚችል አንዳች ምድራዊ ሃይል አይኖርም!" -ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ነሐሴ 26/2014

የኢትዮጵያን ትንሳኤ ከማረጋገጥ ሊያስቆመን የሚችል አንዳች ምድራዊ ሃይል አይኖርም! ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሻደይ፣ አሸንድዬና ሶለል ልጃገረዶች ወጣቶችና ሴቶች አሸባሪው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የፈፀመውን ወረራ የሚያወግዝና፤ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ድጋፍ የሚያደርግ ንቅናቄ ተካሂዷል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የኢፌዴሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ፣ የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበባትና ቱሪዚም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው እና ሌሎችም የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፡- የዛሬውን የሻደይ/አሸንድዬ እና ሶለል በዓል ማክበራችን ዋናው አላማው፤ እኛ እንዲህ በሰላም እንድንንቀሳቀስ መተኪያ የሌላው ውድ ህይወታቸውን እየሰጡን ያሉትን ጀግኖች ክብር ለመስጠት፤ ለማጀገን ጉዳት ለደረሰባቸው ንፁሀን ወገኖቻችን ድምፃችንን ልናሰማላቸው ፤አብረናቸው እንደሆንን ልናሳያቸው እና ወራሪውን ባንዳ ለማውገዝ ነው፡፡ " ብለዋል።

ከንቲባዋ አክለውም ሁላችንም ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ክብር እንድንሰጥ በታላቅ አክብሮት እጠይቃችኋለሁ ያሉም ሲሆን፤ የሻደይ/አሸንድዬ እና ሶለል ልጆች፤ ባህሎቻችንና ሃገራዊ እሴቶቻችን የኢትዮጵያን ህዝብን ያስተሳሰሩ፤ ትውልድ ያሻገሩ፤ የጀግንነት ወኔን እየቀሰቀሱ ትውልድን ያጀገኑ፤ የአገር ካስማና ማገር ናቸዉም ብለዋል።

ከንቲባዋ ኢትዮጵያውያን ከየትኛውም አይነት ትንንሽ ልዩነቶች በላይ ሀገርን በማስቀደም፤ በሁሉም ግንባሮች በንቃትና በትጋት በአንድነት መሰለፍ ግድ ይለናል" ማለታቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያን ትንሳኤ ከማረጋገጥ ሊያስቆመን የሚችል አንዳች ሃይል አይኖርም! ያሉት ከንቲባዋ መላው የከተማዋ ነዋሪዎች በዚህ ወቅት አካባቢውን በብቃት እና በትጋት እንዲጠብቅ፤ ለሰራዊቱም ያልተቆጠበ የደጀንነት ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው፤ ወጣት ሴቶች በባህላዊ ልብስና ጭፈራ ደምቀው በአደባባይ ስለ ሰላም የሚሰብኳቸው አገር በቀል ባህሎችን በጋራ ጠብቀን ልናበለጽጋቸው ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ
https://www.youtube.com/channel/UC9lAZ1l0TvJG65R-QeCDHkg
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis
3.1K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ