Get Mystery Box with random crypto!

AMN-Addis Media Network

የሰርጥ አድራሻ: @addismedianetwork
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 35.84K
የሰርጥ መግለጫ

This is an official Telegram channal for Addis Media Network (AMN) We trive to be the prime informer of issues. Hence, our motto says so, 'first to inform'
ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ !!
contact us via:- E-mail:- addisaammaa@gmail.com
twitter.com/AmnAddis

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 60

2022-09-03 13:34:42
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
3.9K views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 12:42:46
በጎዳና ላይ የንግድ ተግባር ሲያከናውን የነበረ ግለሰብ 10 ሺህ ሐሰተኛ ብር ይዞ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )ነሀሴ 28/2014 ዓ.ም

በየካ ክፍለ ከተማ በጎዳና ላይ የንግድ ተግባር ሲያከናውን የነበረ ግለሰብ 10 ሺህ ሃሰተኛ ብር ይዞ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው መገናኛ ተርሚናል አካባቢ ነው፡፡

ግለሰቡ በአካባቢው ላይ የጎዳና ላይ የንግድ ተግባር የሚያከናውን መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ በጥርጣሬ የተመለከተውን ጉዳይ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠቱ በወንጀል መከላከል ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ሊያዝ መቻሉ ተገልጿል፡፡

በግለሰቡ ላይ በተደረገ ፍተሻም በባለ ሁለት መቶ የብር ኖት አስር ሺህ ሃሰተኛ ብር ይዞ በመገኘቱ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራትን በመፈፀም በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ለማድረስ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መካከል የሃሰተኛ ገንዘቦች ዝውውር አንዱ ነው።

በተለይም በበዓላት ወቅት የሚኖረውን ግብይት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሃሰተኛ ገንዘብ ለማዘዋወር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት ፖሊስ የሚያከናውነውን የቁጥጥርና ክትትል ስራ በመደገፍ ነጋዴውም ሆነ ሸማቹ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል።

ህብረተሰቡ አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።
3.8K views09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 11:32:20
"የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ80 ዓመታት የስኬት ጉዞውን በድምቀት አክብሯል!!

ለሃገራችን አንቱ የተሰኙ ባለሙያዎችንና ታላላቅ ሰዎችን ሲያፈራ የኖረው አንጋፋውና የሃገር ባለውለታው የአዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው እለት የ80ኛ አመት በአሉን ማክበር በመቻሉ ለመላው የኮሌጁ ማህበረሰብና ቤተሰብ በአጠቃላይ እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን ለዚህ አበቃችሁ ለማለት እወዳለሁ!!

ይህንን የካበተ አቅሙን በላቀ ሁኔታ ለመጠቀምና የትውልድ ግንባታ ስራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል በዚሁ ቀን የከተማ አስተዳደራችን አዳዲስ ህንፃዎችን በመገንባት ዛሬ ማስመረቅ ተችሏል፡፡ አሁንም የተከበረውን የቴክኒክና ሙያ ክህሎት ስልጠና ተቋሞቻችንን በማጠናከር የኢትዮጵያን ብልፅግና በኢትዮጵያ እጆች እውን የማድረግ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
579 views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 09:38:01 ˝ለሰሜን ኢትዮጵያ የሰላም መጥፋት ምክንያቱ የአሸባሪዉ ሕወሓት የጦረኝነት ባህሪ˝ ነዉ
አለማቀፉ የኢትዮጵያ ተሟጋች ድርጅቶች
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም

የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ሕወሓት) የጦረኝነት ባህሪ ለሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም መጓደል ምክንያት ነው ሲል አለማቀፉ የኢትዮጵያ ተሟጋች ድርጅቶች "ጥምረት˝ አስታወወቀ።
በመላው አለም ያሉ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች በማደረጀት የተቋቋመዉ ይህ ˝ጥምረት"ባወጣዉ መግለጫ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ለተፈጠረዉ ቀዉስ ተጠያቂዉ አሸባሪዉ ሕወሓት መሆኑን አለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲረዳ ጠይቋወል፡፡
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሀት) እ.ኤ.አ. ነሐሴ 24 ቀን 2022 ግጭቱን በማቀጣጠል እና ኢሰብአዊ ድርጊቶችን በፈጸም ወታደራዊ ጥቃት መፈጸሙን የጠቆመዉ መግለጫዉ አሁንም የኢጥዮጵያን መንግስት የሰላም ጥሪ ወደ ጎን በመተዉ ጦርነት መቀጠሉን አስታዉቋል፡፡

ለትግራይ ክልል ያልተገደበ አገልግሎት እንዲቀርብ በመንግስት በኩል መንገድ ከፋች ርምጃ የተወሰደ ቢሆንም፣ አሸባሪዉ ሕወሓት የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን የሰላም ርምጃ መቀበል ባለመቻሉ ሰላማዊ ዜጎችን ለመደገፍ የታሰበውን የሰብአዊ ርዳታን ወደ ጦር መሳሪያ ማዘዋወር መቀጠሉንና ከፍተኛ ሰባዊ ቀዉስ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች እንዲደርስ ማድረጉን አስታዉቋል፡፡
ሕወሓት በአፋርና በአማራ አጎራባች ክልሎች ወታደራዊ ጥቃት ከመጀመሩ በፊት ከመንግስታቱ ድርጅት የአለም የምግብ ፕሮግራም መጋዘኖች 570,000 ሊትር ነዳጅ መዝረፉን ያስታወሰዉ የቡድኑ መግለጫ ህጻናትን ያለ እድሜያቸዉ ወደ ዉትድርና ማሰለፍ በግልጽ አለም አቀፍ ሕግጋትን የሚጥስ በመሆኑ በቃ ሊባል እንደሚገባም አመልክቷል፡፡

በተለይ እንደ የተባበሩት መንግስታት ፤ የአዉሮፓ ሕብረት አባል አገራት እና ሌሎች አለማቀፍ ተቋማት የዚህን በአሸባሪነት የመመዝገብ ታረክ ያለዉንና አሁንም እያሸበረ ያለ የሕወሓት ቡድን ገሀድ የወጣ ጥፋት አይተዉ እንዳላዩ ማድረጋቸዉን እንደሚቃወመዉ በአጽንኦት አስታዉቋል፡፡

የአለም አቀፉ ማህበረሰብ አፍሪካ ህብረት በሰላም ማምጣቱ ሂደት ያለዉ የመሪነት ሚና አስፈላጊ መሆኑን እንዲገነዘብ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ያልተገደበ ሰብአዊ ርዳታ ለማቅረብ የሚያደርገውን ጥረት እና በትግራይ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት የሚበረታታ መሆኑ እንዲሁም ሕወሓት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ህወሓት ወደ ድርድር እንዲመጣ ግፊት ማድረግ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis
1.6K views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 21:59:40
ውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሃገራቸውን ማገዝ እንዲችሉ የተከፈቱ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥሮች፤

Euro- 1000439142832 (ዩሮ)
Usd -1000439142786 (ዶላር)
Gbp -1000443606304 (ፓውንድ
3.3K views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 20:59:26 ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
ሀገራችን ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበትን የህልውና ጦርነት በጋራ ለመመከት በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊን ከሕዝባቸው ጎን በቆራጥነት በመቆም የሐገርን ሉአላዊነት ለማስከበር በሚደረገው ዘመቻ የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን:: ይህ የህልውና ጦርነት በውጭ ሀገር የምንገኘውን ኢትዮጵያውያን እንቅልፍ የነሳና ሐገራችን እንደ ሐገር እንዳትቀጥል በወያኔ ጁንታ ቡድን በአልሸባብና በሸኔ እንዲሁም በውጭ ሐገር የሚገኙ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በቅንጅት የከፈቱብን ጦርነት ብሔራዊ. ክብራችንና የሚነካ የሀገራችንን ሰላም የሚያውክ በመሆኑ በእጅጉ አሳስቦናል::
ስለዚህ መንግስት በሆደ ሰፊነት ቀደም ሲል የወሰዳቸውን ቁርጠኛ የሰላም ፍላጎቶቹን በማድነቅ የሰላም ድርድሩ ውጤታማ እንዲሆን ሙሉ ድጋፍ ስንሰጥ መቆየታችን እንደተጠበቀ ሆኖ በአሸባሪነት የተፈረጀቱ ፀረ ሰላም ሐይሎች ከሰላም ይልቅ ጦርነትንና እልቂትን መርጠው የከፈቱብንን የአጥፍቶ መጥፋት ጦርነትን በጥብቅ አውግዘን መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደግፋለን::
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት የአሸባሪውን ጁንታ ቡድን እንዲሁም አልሸባብና ሸኔን ፣ማውገዝ ብቻ ሳይሆን ለሐገር ሕልውናና ለህዝባችን ሰላምና ጥቅም ስንል ከመንግስትና እንዲሁም ከመከለከያ ሰራዊታች ጎን በመቆም የዜግነት ድርሻችንን ለመወጣት የትግባር ምክር ቤቱ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን::
በእርግጥ ዲያስፖራው ዛሬም ነገም ለሀገሩ ለወገኑ ድጋፉን አጠናክሮ እንደቀጠለ ቢሆንም በሐገራችን ውስጥ በተፈጠረው ሐገር የማዳን ዘመቻ በዘር በሐይማኖት በፖለቲካ እምነት ሳንከፋፈል ከስሜታዊነትና ከኩሪፊያ በመውጣት ለነገዋ ኢትዮጵያ የተሻለ ነገር ለማምጣት የተሻለችውን ኢትዮጵያ ለማየት ትግሉን የሚጠይቀውን ማንኛውንም ድጋፉ እንድናደርግ ምክር ቤታችን በድጋሚ በመላው አለም ለሚገኙ የኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ጥሪ ያቀርባል::
መንግስት ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ከፍታ ለማድረስ ችግሮችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የሐገራችንን ፖለቲካ ለማዘመን ውስጣዊ ችግሮቻችን በተገቢው መንገድ ለመፍታት ግጭቶችና የጦርነትን ውድመት እንዳይቀጥል በቁርጠኝነት ተነሳስቶ ለሀገረ መንግሥት ግንባታው መሠረት ለመጣል ፖለቲካዊ ችግሮችን በአግባቡ ፈትሾ ሁሉን ዓቀፍ ውይይትና ድርድር ማድረግ በሐገሪቱ ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጁትን ቡድኖች ወደ ዘላቂ ሰላም የጠረንጴዛ ድርድር እንዲቀመጡ ወስዶት የነበረውን የሰላም ጥረት አሁንም ወደፊትም እንዲቀጥል ምክር ቤታችን መደገፉን ይቀጥላል::
ነገርግን ከጦርነት በተሻለ ሰላምን መምረጥ ትርፋማነቱ ቢያዋጣም አሸባሪውና ጎጠኛው የጁንታው ቡድን የአማራና አፋርን ሕዝብ. በመውረር የትግራይን ሕዝብ አግተው በሰላማዊ ሕዝብና በመሰረተዊ የልማት ተቋሞች ላይ ያደረሱትን መጠነ ሰፊ ውድመት መልሰን ለማቋቋም እርብርብ በምናደርግበት ወቅት የሐገርን ሉአላዊነት አደጋ ላይ ለመጣል ለሶስተኛ ዙር የተከፈተብን ታሪክ ይቅር የማይለው ጦርነት በእጅጉ አስቆጥቶናል:: ስለዚህ
1ኛ የአማራና የአፋር ክልልን በመውረር ሲዋጉና አመራር ሲሰጡ የነበሩትን: : እንዲሁም እድሚያቸው ለውትድርና ሞያ ያልደረሱ የትግራይ ህፃናትን በመመልመል ለጦርነት ያሰልፉትን የወያኔ ጁንታ አመራሮች ተለይተው በጦር ወንጀለኞነነትና በሐገር ክህደት ክስ ተመስርቶባቸው በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ መንግስትን እንጠይቃለን::
2ኛ ሀገሪችን በገጠማት የሰላም ማጣት ችግርና ተገዳ ከገባችበት የህልውና ጦርነት በተጨማሪ የሕዝብ ሞትና የስነ ልቦና ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ የሐሰት ቅስቀሳና የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በሚያደርጉ ቅጥረኛ ሚዲያዎች ፣ አለአግባብ ለመበልፀግ የኢኮኖሚ አሻጥር በሚፈፅሙ ነጋዴዎች፣ በተለይ የመንግስት ሙሰኞችና ሌቦች ላይ ያለምንምንም ይቅርታ ጠንካራ እርምጃ መንግስት እንዲወስድ እናሳስባለን::
3ኛ መንግስት የሚቻለው ሁሉ ጥረት በማድረግ ለሐገር ጠቀሜታ ሲል ዘላቂ መፍትሔ የሚያመጡ አካሄዶችና አዳዲስ ስትራቴጂዎች መንደፍ አለበት: : በተለይ ከዲያስፖራው ኮምኒቲ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ በጋራ የአለም አቀፉን ህብረተሰብ በተሳሳተ ፕሮፖጋንዳ የሚያውኩትን የሚዲያ ተቋማትን ተጠያቂ ለማድረግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለድፕሎማቶቹን. ጥብቅ መመሪያ እንዲሰጥና ለተግባራዊነቱም ልዩ ክትትል እንዲያደርግ በጥብቅ እናሳስባለን::
በመጨረሻም ምክር ቤታች ወደፊት ከሚያደርጋቸው የድጅታል ዲፕሎማሲ ትግል በተጨማሪ ጦርነቱን በአጭር ጊዜ ለመጨረስ በሚደረገው የህልውና ጦርነት የዘማቹ ሰራዊት ደጀን በመሆን ጠንካራ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆናችንን ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት እናረጋግጣለን::
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ኢትዮጵያንና ሕዝቧቿን እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክ!!

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ የተግባር ምክር ቤት
3.6K views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 20:11:02 በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ!

ኢትዮጵያ ለሰላም ያላትን የማይናወጥ አቋም በየጊዜው ስትገልፅና ይህንኑ አቋሟን በተግባር ስታረጋግጥ መቆየቷ የአደባባይ ሃቅ ነው፡፡

ሆኖም ስለሰላም የተዘረጉትን እጆች አሻፈረኝ በማለት ለ3ኛ ዙር በሃገራችን ላይ የጥፋት በትሩን የዘረጋው አሸባሪው የህወሓት ቡድን የከፈተውን ጦርነት ተገደን ለመመከት ወደመከላከል መግባታችን ይታወቃል፡፡

የህወሓት አሸባሪ ቡድን ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጰያውያን ላይ ተነግረው የማያልቁ እልፍ አዕላፍ መከራና ሰቆቃ ሲፈፅም የኖረ እኩይ እና ፀረ ህዝብ ቡድን በመሆኑ የጭካኔ በደሉ በበረታባቸው ኢትዮጵያውያን የጋራ ክንድ ከስልጣን የተወገደው ይህ የአሸባሪ ስብስብ አሁንም ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር አብሮ አገራችንን የማፈራረስ ግብ አንግቦ ወረራ ፈፅሟል፡፡

ሆኖም በጀግናው የመከላከያ ሰራዊቻችንና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አኩሪ ተጋድሎ የአሸባሪው ቡድን የጥፋት ላንቃ እየተዘጋና ወረራውን በብቃት እየተመከተ ይገኛል፤ ለዚህም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትልቅ ክብርና አድናቆት አለው፡፡ ምንጊዜም ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን መሆናችንን በተግባር እያረጋገጥን ሃላፊነታችንን በብቃት እንወጣለን፡፡

በተመሳሳይ ዛሬም እንደ ትናንቱ በጦርነቱ ግንባር የአማራና የአፋር ንፁሃን ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከልና ጉዳት የደረሰባቸውን ለመደገፍ ያለንን ቁርጠኝነት ተግባራዊ በማድረግ እንቀጥላለን፡፡
ይህ እኩይ ቡድኑና ተላላኪዎቹ አልሆነላቸውም እንጂ በተደጋጋሚ አዲስ አበባንም ለማተራመስ የሽብርና የእርስ በእርስ እልቂት ውስጥ ለመክተት የማያባራ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ አሁንም ይህንኑ ቅዠታቸውን ለመፈፀም ሲጥሩ ተስተውሏል፡፡

በተለይም በሃሰት ፕሮፖጋንዳ፤ ህዝብ ከህዝብ የሚያጋጩና አንድነታችንን የሚበትኑ የተፈበረኩ መረጃዎችን በማሰራጨት ፤ በከተማዋ ውስጥ የሽብር ቡድኖቹ የህወሓትና የኦነግ ሸኔን የተለያዩ የፅንፍ አስተሳሰብ የሚረጩ አባላትን በማስረግና የጥፋት ሴሎችን በማደራጀት ፤ ሰላማችንን ለማወክ፤ የጸጥታ ስጋት ለመፍጠርና የእኩይ እቅዳቸውን ለማሳካት በግልጽ እንቅስቃሴ እያካሄዱ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለረጅም ዘመናት በዘረጋው የሌብነትና የዝርፊያ አደረጃጀቶችና አሰርጎ ባስገባቸው ተላላኪዎች ተጠቅሞ በተለያዩ ወንጀሎችና የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈፀም፤ ህብረተሰቡን በማማረር መንግስት ላይ ጫና ማሳደር በሚለው ያረጀ ስልት ለመጠቀም ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ከእነዚህ ስልቶችም መካከል፤ በየቦታው ህገ ወጥነትን ማስፋፋትና የመሬት ወረራ እንዲካሄድ በማድረግ፤ የፖለቲካ ግብ ያላቸው የደረቅ ወንጀሎች እንዲስፋፉ በማድረግ፤ የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈጸም የኑሮ ውድነት እንዲባባስና ህዝቡ አንዲማረር ለማድረግ የቀን ቅዠታቸውን ለማሳካት ግብ ያደረጉ እንቅስቃሴዎቻቸው በየአካባቢው መታየት ጀምረዋል፡፡

ይህ ከህዝብ ልብ ተተፍቶ የወጣ ሃይል ፤ በህዝብ ውስጥ ሊሸሸግ የሚስችለው አንዳችም እድል እንደሌለው የታወቀ ቢሆንም በማናቸውም ሁኔታ የዚህ እኩይ ተግባር ተሳታፊ ሆነው ያገኘናቸው አካላትም ሆኑ ሰዎች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ የምንወስድ ይሆናል፡፡

የከተማችን ነዋሪዎችም ወቅታዊ የኑሮ ጫናን ለማቃለል ለበዓል የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን የከተማ አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ በህብረት ስራ ማህበራት በኩል እንዲቀርብ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን በማወቅ ፤ ለህገወጦች እቅድ ተጋላጭ ከመሆን ራሱን እንዲጠብቅ ማሳሰብ እንወዳለን!
በተለይም ቀጣዮቹ ሳምንታት በርካታ ሃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት የሚከበሩበት ወቅት በመሆኑ እነዚህ በአላት በሰላም እንዲጠናቀቁ የከተማችን ነዋሪ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ አካባቢውን ብሎም ከተማውን በንቃት ተደራጅቶ እንዲጠብቅ ፤ ከፀጥታ ሃይሉ እና ከሰላም ሰራዊቱ አደረጃጀት ጋር በመተባበር እንዲንቀሳቀስ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

በየአካባቢው በህገወጥ ድርጊት የተሰማሩ፤ ፀጉረ ልውጦችን፤ የሽብር ወሬ የሚነዙና የኢኮኖሚ አሻጥር ለመፈፀም የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም የተለያዩ ህዝባዊና መንግስታዊ አገልግሎቶች እንዲስተጓጎሉ የሚያደርጉ አካላትን ለፀጥታ ሃይሉ በመጠቆም እንዲሁም በማጋለጥ አገራዊ ሃላፊነታችንን እንድንወጣም የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በመጨረሻም የከተማችን ህዝብና አስተዳደር ከግንባር እስከ ደጀን ለሰራዊታችን አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን እያረጋገጥን ፤ ሁላችንም በየተሰማራንበት ውጤታማ በመሆን የእኩይ ሴራዎችን እያከሸፍን ፤የመዲናችንን ሰላም ዘላቂነት በማረጋገጥና ኢትዮጵያን ለመጠበቅ ከምንጊዜውም በላይ በተደራጀና በተቀናጀ አመራርና ከህዝባችን ጋር እጅና ጓንት ሆነን መስራትን አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡

እውነትና ሃቅ ከኢትዮጵያ ጎን ነው፡፡ ኢትዮጵያ የያዘቸውን ምንጊዜም የማይናወጥ የፍትሃዊነትና ፤የሰላማዊነት አቋም የአሸናፊነት ጋሻዎቻችን ናቸው፡፡

ከሩቅ ታሪካዊ ጠላቶቻችን እስከ ቅርብ ባንዳዎች ድረስ ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ፣ የሞከሩት ሁሉ አሸንፈን መልሰናቸዋል። ዛሬም እንመልስላቸዋለን!!

አዲስ አበባ በኢትዮጵያውያን የጋራ ትብብርና አንድነት ሃላፊነቷን በብቃት ትወጣለች!!
ኢትዮጵያ ድል እያደረገች ትቀጥላለች!!

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ነሃሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
3.5K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 17:24:56
በበዓላት ወቅት ከግብይት ጋር ተያይዞ ሊያጋጥም የሚችል የሃሰተኛ ገንዘብ ዝውውርን ህበረሰቡ እንዲከላከል ተጠየቀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 27 ቀን 2014


በበዓላት ወቅት ከሚፈፀም ግብይት ጋር ተያይዞ ሊያጋጥም የሚችል የሃሰተኛ ገንዘብ ዝውውርን ለመከላከል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖለሲ አሳሰበ፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 396 ባለ ሁለት መቶ ሀሰተኛ የብር ኖት ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 3 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ሀሰተኛ ገንዘቡን ይዘው ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር የዋሉት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ልዩ ቦታው ኦሮሚያ ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደገለፀው ግለሰቦቹ ባጃጅ ተሳፍረው ለመጓዝ በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ ህብረተሰቡ በተመለከተው አጠራጣሪ ጉዳይ እና ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል፡፡

በበዓላት ወቅት የሚኖረውን ግብይት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሃሰተኛ ብሮችን ለማዘዋወር እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ግለሰቦች ስለሚያጋጥሙ ነጋዴውም ሆነ ሸማቹ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲገጥሙት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።
3.7K views14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 16:50:13
የ2015 ዓም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መስከረም 20 እንደሚጀምር ተገለጸ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ነሐሴ 27/2014

የ2015 ዓም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መስከረም 20 እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡

የሊጉ የ1ኛ ዙር መርሃ ግብርም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም የፊፋና ካፍ የውድድር ሰሌዳዎችን በማየት፣ ለውድድር ዝግጁ የሆኑ ስታድየሞችን በመገምገም እና የሊጉን ስፖንሰር አስተያየት ተካቶ በመዘጋጀት ለፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ክለቦች መላኩ ተገልጿል፡፡

መስከረም 20 ቀን 2015 ዓም በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም የሚጀምረው ውድድር ለአምስት ሳምንታት በባህር ዳር ቆይታ ካደረገ በኋላ ከ6ኛ እስከ 10ኛ ሳምንት በድሬደዋ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡

እንዲሁም ከ11ኛ እስከ 15ኛ ሳምንት ያለው ውድድር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

የሁለተኛው ዙር የሊጉ ውድድር መርሃ ግብርም የስታዲየሞች ሁኔታ ከተገመገመ በኋላ በቀጣይ ለክለቦች እንደሚገለጽ መጠቆሙን ከሊጉ ኩባንያ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ
https://www.youtube.com/channel/UC9lAZ1l0TvJG65R-QeCDHkg
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis
3.4K views13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 16:41:16 ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት የዶክተር ቴድሮስን ከድርጀቱ ስነ ምግባር ያፈነገጠ ድርጊት እንዲያስቆም ጠየቀች

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ቦርድ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ከተቋሙ ሰራተኞች ስነ ምግባር በተፃረረ መንገድ ኢትዮጵያን በተመለከተ የሀሰት መረጃ የማሰራጨት ድርጊትን እንዲያስቆም በጄኔቫ የኢትዮጵያን ቋሚ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤት ጠየቀ።


ጽኅፈት ቤቱ ባወጣዉ መግለጫ፥ በፈረንጆቹ ኅዳር 3 ቀን 2020 አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ጦር ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታዉሶ ፤ጥቃቱን ተከትሎ ከሕወሓት አመራሮች አንዱ የሆነዉ ዶክተር ቴድሮስ ፤በሕወሓት የቁጥጥር ሠንሠለት ሥር ሆኖ ትዕዛዝ በመፈፀም የሽብር ቡድኑን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሲያሠራጭ መቆየቱን አመላክቷል፡፡

ሕወሓት በአማራና በአፋር ክልሎች ትምህርት ቤቶችን፣ ጤና ተቋማትን፣ የህዝብ አገልግሎት ተቋማትን እና መሠረተ-ልማቶች ሲያወድም ዶክተር ቴዎድሮስ ሲያወግዝ አለመታየቱን መግለጫዉ ጠቁሟል፡፡

ዶክተር ቴድሮስ አብዝቶ የሚደግፈው ይህ ቡድን አሁንም በአጎራባች ክልሎች ላይ የፀብ-ጫሪ ተግባሩን መቀጠሉን አመላክቷል፡፡
ባለፈው ወረራ የፈጸማቸውን የህዝብ ተቋማት የማውደም ፣ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን የመፈጸም እና የመጨፍጨፍ ተግባራት አሁንም በክልሎቹ መቀጠሉንም አውስቷል፡፡

በዓለም ጤና ድርጅት ውስጥ ያለውን ስልጣን የኢትዮጵያን መንግስት ስም ለማጥፋት እየተጠቀመ መሆኑን ያመለከተዉ መግለጫዉ በዚህም ተግባሩ የዓለም ጤና ድርጅት መልካም ስምን፣ ገለልተኝነት እና ተዓማኒነት ክፉኛ መጉዳቱን አታዉቋል፡፡

ይህ የዓለም ጤና ድርጅት የሰራተኞች ስነ ምግባር ደንብን የጣሰዉን የዶክተር ቴዎድሮስ ድርጊትን የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ቦርድ በፍጥነት እንዲመረምር ጠይቋል።

በአንድ አባል አገር ላይ ከፍተኛ በደል መፈፀሙን በማመልከት የኢትዮጵያን ቅሬታን ለቦርዱ ማስገባቱን ጽህፈት ቤቱ ስታዉቋል፡፡


ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter.com/AmnAddis
3.3K viewsedited  13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ