Get Mystery Box with random crypto!

'የእሁድ ገበያዎች ከእሁድ ቀን በተጨማሪም እስከ አዲስ አመት ድረስ ይዘልቃሉ'-ከንቲባ አዳነች አቤ | AMN-Addis Media Network

"የእሁድ ገበያዎች ከእሁድ ቀን በተጨማሪም እስከ አዲስ አመት ድረስ ይዘልቃሉ"-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ነሐሴ 29/2014

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት መጪውን ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ ለበአል ፍጆታ የሚሆኑ በርካታ ምርቶች ወደ መዲናዋ በመግባት ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

ምርቶቹም በተለያዩ የእሁድ ገበያዎችና የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች እንደሚገኙም ከንቲባ አዳነች ጠቁመዋል።

በዚህም መሰረት የእሁድ ገበያዎች ከእሁድ ቀን በተጨማሪም እስከ አዲስ አመት ድረስ የሚዘልቁ ስለሆነ፣ ህብረተሰቡ ያለ አግባብ ዋጋ ከሚጨምሩና የኢኮኖሚ አሻጥር ከሚፈጥሩ አካላት ራሱን በመጠበቅ በየአካባቢው በሚገኙ የእሁድ ገበያዎችና የሸማች ማህበራት ሱቆች እንዲገበያይ ጥሪ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።