Get Mystery Box with random crypto!

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

የቴሌግራም ቻናል አርማ addismaleda — Addis Maleda - አዲስ ማለዳ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ addismaleda — Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
የሰርጥ አድራሻ: @addismaleda
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.91K
የሰርጥ መግለጫ

ዜና ከምንጩ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-31 15:15:59 ኦፌኮ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም በተቀሰቀሰው ጦርነትና በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ግጭት በመባባሱ እጅግ ማዘኑን ገለጸ

በኹሉም ወገን ያሉ ተፋላሚ ሀይሎች ግጭቱን በማብረድ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲሹ ጠይቋል

ዕረቡ ነሐሴ 25 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አገራችንን ለከፍተኛ ሰብዐዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ኪሳራ የዳረጋት ጦርነት ዳግም በሰሜን ኢትዮጵያ በማገርሸቱና በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ግጭት በመባባሱ እጅግ ማዘኑን ገልጿል።

ፓርቲው በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ ”የእነዚህ ግጭቶች መባባስ እና መቀጠል ህዝቡን ዳግም ለከፋ ሞት እና መፈናቀል የሚዳርግ ከሆኑ ባሻገር ለንብረትና መሰረተ ልማቶች ውድመት የተዳረጉ አካባቢዎችን ለበለጠ አለመረጋጋት ይዳርጋል።“ ብሏል።

ጦርነት ለኢትዮጵያ ውስብስብ የፖለቲካ ችግሮች መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል የገለጸው ኦፌኮ፤ እነዚህ ችግሮች በዘላቂነት ሊፈቱ የሚችሉት በእውነተኛ እና ኹሉን አቀፍ ድርድር ብቻ መሆኑ ፅኑ እምነቱ መሆኑንም አስታውቋል።

ስለዚህም በኹሉም ወገን ያሉ ተፋላሚ ሀይሎች ግጭቱን በማብረድ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲሹ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ጠይቋል።

በተጨማሪም በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች ኹሉ ተጨማሪ ሞት እና የዜጎችን መከራ ለማሰቀረት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በንቃት እና በተቀናጀ ልኩ እንዲረባረብም ጥሪ አቅርቧል።

አለም አቀፉ ማህበረሰብ በመላው ኦሮሚያ የተሰፋፋውን ጦርነት ለመፍታት ቀርቶ እውቅና ሊሰጠው አለቻሉን እንዳሳሰበው የገለጸው ኦፌኮ፤ በክልሉ በተለይም በግጭት እና በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ያለው ሰብዓዊ ኹኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጿል። በመሆኑም የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እየተባባሰ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ በድርድር እንዲፈታ ኹኔታዎችንን እንዲያመቻች ጠይቋል።

በመጨረሻም ፖርቲው ከኢትዮጵያ ህዝብን፣ ገዥው ፓርቲን፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሚዲያ ተቋማትን፣ የማህበራዊ ሚዲያ ባለሙያዎች እና አክቲቪስቶች ግጭቱን ከሚያባብሱ ንግግሮች እንዲታቀቡና ችግሩን ለማርገብና ለመፍታት በአንድ ድምፅ እንዲተባበሩ ጥሪውን አቅርቧል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
2.5K views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 09:08:00
ሲቪል ማኅበራት እና ፖለቲካ ፓርቲዎች ለአገራዊ ምክክር

ኢትዮጵያ የገጠሟትን ችግሮች ያቃልላል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን አገራዊ ምክክር ለማድረግ ምክክሩን የሚመራ ኮሚሽን በአዋጅ ተቋቁሞ የዝግጅት ሥራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል። ምክክሩን እንዲመራ ከተሠየመው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በተጨማሪ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አገራዊ ምክክሩ እውን እንዲሆን የየራሳቸውን አበርክቶ ለማዋጣት ጥረት እያደረጉ ነው።

ለተጨማሪ ንባብ -> https://bit.ly/3e1ecIR
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
745 views06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:59:57
የሸኔ ታጣቂ በአፋር ክልል በከፈተው አዲስ ጥቃት ንጹሐንን እየገደለ መሆኑ ተሰማ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የሸኔ ታጣቂ ቡድን በአፋር ክልል ቡርቃ ከተማ አዲስ የጥቃት ዘመቻ መጀመሩንና ንጹሐን ሰዎች እየተገደሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

የአዲስ ማለዳ ምንጮች በገለጹት መሠረት፤ ሸኔ ጥቃቱን የከፈተው ባሳለፍነው ነሐሴ 18/2014 ነው። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ የቡርቃ ከተማ ነዋሪዎች እየተገደሉ ነው ያሉት ምንጮች፤ ‹‹ድሮም ከሕወሓት ጋር ጥብቅ ትስስር አለው። አሁንም ጥቃቱን በተመሳሳይ ጊዜ ከፍተዋል።›› ሲሉ ተናግረዋል።

ለተጨማሪ ንባብ -> https://bit.ly/3dP5qNS
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
2.3K views11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 13:55:57
እውነት ኢትዮጵያዊ መልኩን አልቀየረም?

ብዙዎች ይሟገቱበታል። ‹‹አሁን እየታየ ያለውን የእርስ በእርስ ግጭትና ጭካኔ የተሞሉ ድርጊቶችን እያየን ‹ኢትዮጵያዊ ደግ ነው› ማለት መታበይ ነው›› የሚሉ ብዙዎች ናቸው። በአንጻሩ ‹‹የለም! ክፋት በየዘመኑ አለ። እንጂ አሁንም ኢትዮጵያዊያን መልካችን አልጠፋም።›› የሚሉ አሉ። በምግባርም ሆነ በስብእና በኩል በፍጽምና ሰናይም ሆነ እኩይ የለም የሚሉቱ፣ አማካዩ ነው መልካችን ሲሉ ይደመጣል።

ይህ ሁሉ ዕይታ ከምን መጣ? እውነት እንደሚባለው ኢትዮጵያዊ መልኩን አልቀየረም? መልኩስ ምን ነበር? ቀይሮስ ከሆነ ምን ይደረግ? እነዚህ ጥያቄዎች ተነስተዋል። የአዲስ ማለዳዋ ሊድያ ተስፋዬ ይህን ጉዳይ በማንሳት፣ የተለያዩ ጥናቶችን በማጣቀስና በተለያየ ዘርፍ ያሉ ባለሞያዎችን በማነጋገር የሐተታ ዘ ማለዳ ርዕሰ ጉዳይ አድርጋዋለች።

ለተጨማሪ ንባብ -> https://bit.ly/3cqRqcY
__
ትክክ
ለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
2.3K viewsedited  10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:52:58
ተሰረቅን ወይስ ተወረስን?

ግመል ሰርቆ አጎንብሶ እንዲሉ፤ የዓለም ምግብ ፕሮግራም 12 ቦቴዎች ተሰረቁብኝ ማለቱ ብዙዎችን አነጋግሯል። የተሰረቀ ይሰወራል፤ የእነሱ ግን በግላጭ መወሰዳቸውን የሚናገሩ፣ ተሽከርካሪዎቹ እንዴት ጂፒኤስ አልተገጠመላቸው ሲሉ ሞግተዋል።

ከዚህ ቀደም በሺሕ የሚቆጠሩ የእርዳታ መኪኖች ከትግራይ አልተመለሱም ተብሎ ከነነዳጃቸው ለጦርነት ሲውሉ እየታየ፤ አሁን ከ570 ሺሕ ሊትር በላይ የጫኑ ቦቴዎች እንዲገቡና እንዲሰወሩ ሲደረግ አስቀድሞ አልታወቀም ማለት እንደማይቻል ብዙዎች ተናግረዋል።

ለተጨማሪ ንባብ -> https://bit.ly/3CRgogz
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
2.3K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:37:57
የተማሪዎች መማሪያ ደብተር እስከ 80 ብር እየተሸጠ ነው

የ2015 የትምህርት ዘመን ሊጀመር ጥቂት ጊዜያት በቀሩበት በዚህ ወቅት የተማሪዎች መማሪያ ደብተር እስከ 80 ብር እየተሸጠ ይገኛል።

አዲስ ማለዳ እንዳረጋገጠችው በተለይ በአዲስ አበባ ራዲካል ተብሎ የሚጠራው ባለሃምሳ ገፅ አንድ ደብተር እስከ 80 ብር የሚሸጥ ሲሆን፣ በክፍለ አገር ከተሞች መጠነኛ ቅናሽ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል።

ሌሎች ‹ዝቅተኛ› የወረቀት ጥራት ያላቸው የመማሪያ ደብተሮችም ከወትሮው በተለየ በጭማሪ ዋጋ እየተሸጡ ነው። በዚህም ባለሃምሳ ገፅ ደብተር ከ50 ብር ጀምሮ ይሸጣል።

ለተጨማሪ ንባብ -> https://bit.ly/3RaqyMY
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
2.4K views05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:01:12
#አዲስ_ማለዳ #199
#ትንታኔ
#ሐተታ_ዘማለዳ
#አቦል_ዜና
ሙሉውን ጋዜጣ ከታች በሚገኘው ሊንክ ላይ ያገኙታል
https://bit.ly/3NzhEGO
መልካም ንባብ
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
2.5K views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 16:11:56 ፍርድ ቤቱ ከኮንዶሚኒየም ዕጣ ማጭበርበር ወንጀል ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ 5 የሶፍትዌር ባለሙያዎች በ60 ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ፈቀደ

አርብ ነሐሴ 20 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ከኮንዶሚኒየም ዕጣ ማጭበርበር ወንጀል ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ 5 የሶፍትዌር ባለሙያዎችን በ60 ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ፈቅዷል።

ዋስትና የተፈቀደላቸው ተጠርጣሪዎች የቤቶች ልማት ዳታ ቤዝ ቡድን መሪ ስመኘው አባተ እና የሶፍትዌር ባለሙያዎች ሀብታሙ ከበደ፣ ዮሴፍ ሙላት፣ ጌታቸው በሪሁን እንዲሁም ቃሲም ከድር ናቸው።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች በዋስ ቢወጡ እንደማይቃወም ፖሊስ ለችሎቱ አስተያየት መስጠቱን ተከትሎ ዋስትና ተፈቅዶላቸዋል።

ቀሪዎቹ ማለትም፤ የአ/አ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና አይሲቲ ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አብርሐም ሰርሞሌ፣ የቤቶች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ሚኪያስ ቶሌራ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አይሲቲ ሀላፊ ኩምሳ ቶላ በሚመለከት ደግሞ በመርማሪ ፖሊስ በተገለጸው ከተለያዩ ተቋማት የሚሰበሰቡ ማስረጃዎች እና የቀሪ ሥራ በመኖሩ ችሎቱ አሳማኝ ምክንያት ነው ሲል የ12 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መፍቀዱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።

በአጠቃላይ ተጠርጣሪዎቹ ከ14ኛው ዙር 20/80 እና የ3ኛ ዙር የ40/60 የአ/አ ከተማ ከኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ላይ ያልቆጠቡና በወቅቱ ያልተመዘገቡ ግለሰቦችን ያለአግባብ በዕጣው እንዲያካትቱ አድርገዋል ተብለው በቁጥጥር ሥር ውለው ከአንድ ወር በላይ በእስር ላይ የነበሩ ናቸው።

በሌሎች መዝገቦች በተለያዩ ቀናት ከዚህ በፊት የቀረቡ ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱን ጨምሮ 7 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ግን እንደቀጠለ ነው።

በተለይም ለኮዶሚኒዬም ዕጣ ጉቦ ተቀብለው 5 ሰዎችን በዕጣው እንዲካተቱና ቤት እንዲደርሳቸው አድርገዋል የተባሉ 3 የስፍትዌርና ዳታ ቤዝ ባለሙያዎች ባሳለፍነው ሳምንት በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛሉ።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች 1ኛ የአ/አ ቴክኒክና ሙያ ስልጠናና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሶፍትዌር ባለሙያ የነበረ አሚ አምባዬ የሚባል ሲሆን፤ 2ኛ ተጠርጣሪ የዳታ ቤዝ ሰራተኛ የነበረ ዮናስ ወ/ጊዮርጊስ እና 3ኛ የዳታ ቤዝ ሰራተኛ የሆነችው አብረኸት ልዑል ናቸው።

በተለይም 3ኛ ተጠርጣሪ አብረኸት ልዑል በበኩሏ "አንድ ሰው መጥቶ ገንዘብ እየተከፈለ የቤት ዕጣ መካተት ይቻላል ወይ ሲል ጠይቆኝ ነበር እኔ ደግሞ 2ኛ ተጠርጣሪን ዮናስን ስጠይቀው አዎ ገንዘብ ተከፍሎ የሚያካትት አለ አለኝ። ከዛ በኋላ ግለሰቡ የባንክ ሂሳቤ ላይ የሶስት ሰዎችን አጠቃላይ 850 ሺህ ብር ካስገባልኝ በኋላ ኹሉንም ገንዘብ ለ1ኛ ና ለ2ኛ ተጠርጣሪዎች በባንክ ሂሳባቸው አዛውሬላቸዋለው" ስትል ለፍርድ ቤቱ መግለጿን መዘገባችን ይታወሳል።
________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
2.7K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 16:11:32
2.3K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:36:28
ህወሓት ጦርነት በከፈተበት ግንባር ናፍታ እና ቤንዚን ሊያቀብል የነበረ አይሱዙ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ

አርብ ነሐሴ 20 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) መነሻውን ከሰመራ ያደረገ ኮድ 3 ታርጋ ቁጥር A47679 አይሱዙ ተሽከርካሪ መዳረሻውን ወደ አሸባሪው ህወሓት ቡድን በማድረግ 3000 /ሦስት ሺሕ/ ሊትር ናፍጣ እና 2000 /ኹለት ሺሕ/ ቤንዚል ካልዋን ላይ ሲደርስ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል።

በግዳጅ ቀጠናው የሚገኙት መ/አለቃ መንግስተአብ አበራ እንደተናገሩት፤ "በአሁኑ ሰዓት አሸባሪው ህወሓት በሀገራችን ላይ ጦርነት ቢከፍትም በጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን አፀፋዊ ምላሽ እየተሠጠ ባለበት ወቅት በህገ ወጥ መንገድ ለጠላት ሊደርስ የነበረን ነዳጅ መቆጣጠር ችለናል" ብለዋል።

መ/አለቃ መንግስተአብ አበራ አክለውም፤ በቀጣይም ለአሸባሪው የትህነግ ቡድን በህገወጥ መንገድ ሊደርስ የሚችል ማንኛውም ነገር ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በጋራ እንደሚሠሩ መናገራቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
2.4K views11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ