Get Mystery Box with random crypto!

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

የቴሌግራም ቻናል አርማ addismaleda — Addis Maleda - አዲስ ማለዳ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ addismaleda — Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
የሰርጥ አድራሻ: @addismaleda
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.91K
የሰርጥ መግለጫ

ዜና ከምንጩ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 09:22:25
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አለፈ

አርብ ነሐሴ 27 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ ውብሸት አያሌው ትላንት ማታ ከሥራ ወጥተው ወደ ቤታቸው በማምራት ከመኪና ላይ ወርደው ሊገቡ ሲሉ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው ማለፉን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።

ውብሸት አያሌው ባለትዳር እና የአንድ ሴትና አንድ ወንድ አባት የነበሩ ሲሆን፤ ወደ ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር በሥራ ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት በቀወት ወረዳ አስተዳደር በተለያዩ ተቋማት በባለሙያነትና በሥራ ኃላፊነት ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል።

ከንቲባው እንደ አንድ የህዝብ አደራ እንደተቀበለ አመራር እና እንደ ተወላጅ ከተማዋ የሚገባትን እድገትና ማዕረግ እንድታገኝ እንዲሁም ነዋሪዎቿ ኹሉን አቀፍ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ በከፍተኛ ቁጭት እየሰሩ የሚገኙ ወጣት አመራር እንደነበሩም የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገልጿል።

"የደረሰብን ሀዘን እጅግ መራርና አስደንጋጭ ነው" ያለው የከተማ አስተዳደሩ "ይህም መስዋእትነት ለህዝብ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና አንድነት የተከፈለ ዋጋ ነው።" ሲል አስታውቋል።

ሥርዓተ ቀብራቸውም በሸዋሮቢት ከተማ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በዛሬው ዕለት ከቀኑ 6 ስዓት ላይ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት እንደሚፈጸም ታውቋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
1.0K views06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:40:21
የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የአገልግሎቶቹን ክፍያ በቴሌብር በኩል መፈጸም የሚያስችል ስምምነት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ተፈራረመ

ሐሙስ ነሐሴ 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የአገልግሎት ክፍያ ሥርዓቱን በማዘመን፤ የአገልግሎቶቹን ክፍያ በቴሌብር በኩል መፈጸም የሚያስችል ስምምነት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርሟል።

በዚህም መሠረት የኤጀንሲው ባለጉዳዮች ያለምንም ውጣ-ውረድ እና እንግልት የመኪና ሽያጭ ውል፣ የስጦታ፣ የውክልና፣ የብድር፣ የማህበር ምስረታ እና ቃለ ጉባኤ የመሳሰሉ ከ27 በላይ አገልግሎቶቹን ክፍያ በቴሌብር መፈጸም እንዲችሉ መደረጉ ተገልጿል፡፡

ባለጉዳዮች ኤጀንሲው የሚሰጣቸውን የክፍያ ማዘዣ ቁጥር በመጠቀም፤ በቴሌብር መተግበሪያ ወይም በአጭር ቁጥር (*127#) የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀላሉ መፈጸም እንደሚችሉም ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡
_
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
2.3K views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:22:30 የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ የፊታችን መስከረም 10 ቀን፤ ለ5 ሺሕ የአገር ውስጥ ሮስካ ተመዝጋቢዎች ዕጣ የማውጣት ሥነሥርዓት እንደሚያከናውን አሰታወቀ

ሐሙስ ነሐሴ 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ ትሬዲንግ ከዚህ ቀደም ጳጉሜ 03 ቀን 2014 አከናውነዋለሁ ብሎት የነበረውን የዕጣ ማውጣት ሥነሥርዓት ወደ መስከረም 10 ቀን 2015 መቀየሩን በዛሬው ዕለት አስታውቋል።

በዕጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓቱ ላይም 5 ሺሕ የአገር ውስጥ ሮስካ ተመዝጋቢዎች እንደሚሳተፉበት ገልጿል።

የጎጆ ሃውሲንግ ትሬዲንግ መሥራችና ምክትል ዳይሬክተር ናደው ጌታሁን ዕጣ የሚወጣበት ጊዜ የተራዘመበትን ምክንያት ሲያስረዱ፤ በተመዝጋቢ አባላት የይራዘምልን ጥያቄና በአባላቱን ቁጥር በመጨመር የዕጣ ብዛቱንም ከፍ ለማድረግ በመታሰቡ መሆኑን ተናግረዋል።

በዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይም የ5 ሺሕ የአገር ውስጥ ሮስካ ተመዝጋቢዎች እጣ እንደሚወጣ፣ 4 ያለቁ ሳይቶችን ካርታ ለህብረት ሥራ ማህበራት የማስረከብ፣ 4 ያለቁ ሳይቶች የግንባታ ፍቃድ ርክክብ እንዲሁም አዲስ ለተመዘገቡ 4 መቶ አባላት የሚደራጁበትን ቦታ የማሳወቅ መርሃ ግብሮች እንደሚከናወን ምክትል ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

በተጨማሪም በዕለቱ ከጤና ሚኒስቴርና ከዳሽን ባንክ ጋር ለጤና ባለሙያዎች የመኖሪያ መንደር ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት እንደሚያደርግም ተገልጿል።

ጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ የተቋቋመው የዜጎችን የቤት ችግር ለመፍታት ቤት ፈላጊዎችን በህብረት ሥራ ማህበራት አደራጅቶ የቤት ባለቤት ማድረግ ነው ያሉት የጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ የማህበራት ማደራጀት ክፍል ሀላፊ አጋ ፉፋ ሲሆኑ፤ እነዚህንም ማህበራት ጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ የራሱን የማህበራት ክፍል በማቋቋም ክትትል እና ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የህብረት ሥራ ማህበራቱ የራሳቸው የክትትል እና ቁጥጥር ኮሚቴ እንዳላቸው የገለጹት አጋ በማህበር መደራጀታቸው በህብረት ሥራ ማህበረት አዋጅ መሰረት የግንባታ ቦታን የማገኘትና የግንባታ እቃዎችን ከግብር ነፃ የማስገባትን ዕድል ይሰጣቸዋል ብለዋል።

ጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ እስካሁን ድረስ 4 ሳይቶች፣ 8 ማህበራት እና 1 ሺሕ 55 አባላትን ማፍራት መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፤ መስከረም 11 በሚጀመረው አዲስ ምዝገባም የተሻሻለውን የሮስካ ክፍያ እና አሠራር ለተጠቃሚ በማስተዋውቅ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት 55 ሺሕ ብር የነበረወሰ ቅድመ ክፍያ ወደ 59 ሺህ ብር እንዲሁም በየወሩ ለ10 ዓመታት ይቆጠብ የነበረው የ2 ሺሕ ብር ወርሃዊ መዋጮ ወደ 2 ሺሕ 200 ብር ማሳደጉን አስታውቋል።
_____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
2.3K views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:21:44
1.9K views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:14:15
በኮልፌ ቀራንዮ በአንድ የመጋዘን ህንፃ ላይ የእሳት አደጋ መከሰቱ ተገለጸ

ሐሙስ ነሐሴ 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ በወረዳ 07 ልዩ ቦታው ቤተል ትምህርት ቤት ጀርባ በተባለ አካባቢ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በአንድ የመጋዘን ህንፃ የእሳት አደጋ መከሰቱ ተገልጿል።

የእሳት አደጋው ዛሬ ከረፋዱ 4:40 ላይ በውስጡ የፒፒሲ፣ የአረቢያን መጅሪስ እና የስፖንጅ መጋዘን ላይ መነሳቱን ኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 07 ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቀዋል።

የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ሰራተኞች፣ የፀጥታ ሀይሎች እንዲሁም ነዋሪዎች እርብርብ በማድረግ እሳቱ በመቆጣጠርና በማጥፋት ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡
_
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
2.1K views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:39:16 "ኹለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም።"፦ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት

ሐሙስ ነሐሴ 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) "ኹለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም ሲል የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ "በሕወሓት ቡድን እየደረሱ የሚገኙ ጥፋቶችን ለማስቆም መንግሥት ለሰላማዊ አማራጭ ያደረጋቸው ጥረቶች ኹሉ እየመከኑ ባሉበት ሁኔታ፣ አሸባሪውን ሕወሐት መጫን ሲገባቸው "ኹለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም።" ሲል ገልጿል።

ሕወሓት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በየአቅጣጫው በለኮሰው እና ዛሬም እያስፋፋ ባለው እሳት ንጹሐን እየተገደሉ ነው፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ፣ ንብረትም እየወደመ እንደሚገኝም አስታውቋል።

"አሁን እንደሚታየው ሕወሓት ከአገር አጥፊነት ተግባሩ የማስቆም ግዴታ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ላይ ወድቋል።" ያለው አገልግሎቱ፤ የዚህንም ምክንያት እንደሚከተለው በዝርዝር አስቀምጧል፦

=> የሽብር ቡድኑ ሰላማችንን እንዳያደፈርስና አገራችንን እንዳያፈርስ መከላከል ስለሚገባ፤

=> ሕወሓት ወደ ትግራይ የሚላከውን እርዳታ ለተቸገረው ሕዝብ እንዳይደርስ፣ በተቃራኒው እርዳታው ለጦርነት እንዲውል እያደረገ በመሆኑ መንግሥት እርዳታው ለተረጂው ሕዝብ እንዲደርስና ትግራይ ውስጥ ምቹ ኹኔታ በመፍጠር ሕዝቡን ከችግር የመከላከል ግዴታ ስላለበት፤

=> ሕወሓት በእኩይ ተግባሩ ሕዝብን በረሃብ ለመቅጣት ዐቅዶ ተደጋጋሚ ጦርነት የሚከፍተው በክረምት የግብርና ወቅት በመሆኑ፤ መንግሥት ወረራውን እየተከላከለ ያለው ሕዝብን ከረሃብ የማዳን ግዴታ ስላለበት ጭምር ነው። ሲል ገልጿል።

በመሆኑም ሕወሓት ተደጋጋሚ የሰላም አማራጮችን በመግፋት የከፈተው ጥቃት አገራችንን እንዳይበትን፣ የመከላከያ ኃይላችን በኹሉም አቅጣጫ የተከፈተበትን ወረራ ከሰላም ወዳዱ ደጀን ሕዝብ ጋር በመሆን በጽኑ ጀግንነት በመከላከል ላይ እንደሚገኝ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው አስታውቋል።
_____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
2.0K views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:38:51
1.9K views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:12:55
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሐረሪ ክልል መጠነ-ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ መጀመሩን አስታወቀ

ሐሙስ ነሐሴ 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መጠነ-ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በሐረሪ ክልል መጀመሩን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት መሆኑን ገልጿል።

በሐረሪ ክልል የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ፤ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች የሚካሔድ ሲሆን ደንበኞች በዐ7 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት እንደሚችሉም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አስታውቋል።

ደንበኞች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርዶችን የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤ ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶች ጥቅል እንደሚያገኙ ተገልጿል።

የደንበኝነት ማስጀመሪያ ጥቅሉ በሚያልቅበት ጊዜ ደንበኞች የአየር ሰዓት ከሽያጭ ማዕከላት ወይም መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች በመግዛት መሙላት እና አገልግሎቱን መቀጠል ይችላሉም ተብሏል።

በሐረሪ ክልል አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ፤ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገልጿል።
_
#አዲስ_ማለዳ
2.1K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:58:59
10 ከፍተኛ የምግብ ዋጋ ግሽበት የታየባቸው አገራት

እንደ ዓለም ባንክ መረጃ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት በተለይ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባለቸው አገሮች ከፍተኛ የሆነ የምግብ ዋጋ ግሽበት ተከስቷል። በተለይ በሚያዚያ እና ግንቦት ወራት ግሽበቱ ከፍተኛ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ውስጥ ከኹለቱም በኩል 92 በመቶ በላይ በሚሆኑት ግሽበቱ ታይቷል። እንዲሁም ከበለጸጉ አገራት 89 በመቶ በሚሆኑት ይኼው የምግብ ዋጋ ግሽበት ተጋርጦባቸዋል።

ለተጨማሪ ንባብ -> https://bit.ly/3TtS0aw
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
2.3K views06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:52:59 የእኛን እናጥና!

በኢትዮጵያ ሴቶች ትግል መች ተጀመረ የሚለው በጥናት መሠረት የተቀመጠ አይመስለኝም፤ ወይም መረጃው የለኝም። ነገር ግን እንቅስቃሴዎች የተጀመሩት ከደርግ ዘመነ መንግሥት በኋላ ወይም የሴቶች ቀን መከበር ከጀመረ ወዲህ እንዳልሆነ እሙን ነው።

በቀደመው ዘመን የሴቶች የእኩል መብት ትግል ተሳታፊዎችን ባናወሳ እንኳ፣ ዛሬ ላይ ሆነን ከሴቶች መብት አንጻር ‹ነበር› ብለን በግምት ዝቅ በምናደርገው ዘመን የነበሩ ሴት መሪዎችን ታሪክ እንኳ አንዘክርም። ሴት ንግሥት በኢትዮጵያ ምድር ነበረች። በአድዋም ሆነ በኹለተኛው የኢትዮጵያና ጣልያን ጦርነት ተሳትፈው ታሪክ የሠሩና የተጋደሉ ሴቶችንም አናወሳም።

ለተጨማሪ ንባብ -> https://bit.ly/3pYAdL6
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
2.6K views12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ