Get Mystery Box with random crypto!

ህወሓት ጦርነት በከፈተበት ግንባር ናፍታ እና ቤንዚን ሊያቀብል የነበረ አይሱዙ ተሽከርካሪ በቁጥጥር | Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

ህወሓት ጦርነት በከፈተበት ግንባር ናፍታ እና ቤንዚን ሊያቀብል የነበረ አይሱዙ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ

አርብ ነሐሴ 20 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) መነሻውን ከሰመራ ያደረገ ኮድ 3 ታርጋ ቁጥር A47679 አይሱዙ ተሽከርካሪ መዳረሻውን ወደ አሸባሪው ህወሓት ቡድን በማድረግ 3000 /ሦስት ሺሕ/ ሊትር ናፍጣ እና 2000 /ኹለት ሺሕ/ ቤንዚል ካልዋን ላይ ሲደርስ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል።

በግዳጅ ቀጠናው የሚገኙት መ/አለቃ መንግስተአብ አበራ እንደተናገሩት፤ "በአሁኑ ሰዓት አሸባሪው ህወሓት በሀገራችን ላይ ጦርነት ቢከፍትም በጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን አፀፋዊ ምላሽ እየተሠጠ ባለበት ወቅት በህገ ወጥ መንገድ ለጠላት ሊደርስ የነበረን ነዳጅ መቆጣጠር ችለናል" ብለዋል።

መ/አለቃ መንግስተአብ አበራ አክለውም፤ በቀጣይም ለአሸባሪው የትህነግ ቡድን በህገወጥ መንገድ ሊደርስ የሚችል ማንኛውም ነገር ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በጋራ እንደሚሠሩ መናገራቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n