Get Mystery Box with random crypto!

#ሰበር_ዜና መንግሥት የተመረጡ የህወሓት ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ አ | Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

#ሰበር_ዜና
መንግሥት የተመረጡ የህወሓት ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ


አርብ ነሐሴ 20 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የፌደራሉ መንግሥት የተመረጡ የህወሓት ወታደራዊ ዐቅሞች ዒላማ ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

መንግሥት እስከ አሁን ድረስ ለሰላም በሩን ክፍት አድርጎ ቢጠባበቅም ህወሓት ጥቃቱን እንደቀጠለበት አገልግሎቱ ገልጿል።

በመሆኑም የፌዴራል መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር የገለጸው ዝግጁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለህወሓት ቡድን ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ ርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

"ስለሆነም በትግራይ የምትኖሩ ወገኖቻችን በተለይም የጁንታው ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳችሁን እንድታርቁ ይመከራል።" ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።
______
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n