Get Mystery Box with random crypto!

የአብነት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ abenet_tmhert — የአብነት ትምህርት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ abenet_tmhert — የአብነት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @abenet_tmhert
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.99K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ መንፈሳዊ ቻናል
፦የግእዝ ቋንቋን ጨምሮ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ፡፡
ለአስተያየቶ @Channel_admin09 ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-03-21 17:16:50 ሰበር ልዩ መረጃ!

በሕገ ወጡ ሹመት ላይ የተሳተፉት ቀሪ 23 ግለሰቦች የይቅርታ ደብዳቤያቸውን ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ለብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እያቀረቡ ይገኛሉ።

ዝርዝር መረጃ ከደቂቃዎች በኋላ የምናደርስ ይሆናል!

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
2.7K views14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 07:39:08 ሰላም ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።

የምንሰጠውን አገልግሎት ለማሳለጥ እና ለፈላጊው በሚፈለገው ሰአት ለማድረስ የሚያግዘን ሰው እንፈልጋለን እና መስፈርቱን የምታሟሉ በውስጥ መስመር @channel_admin09 ላይ አናግሩን።

መስፈርቶቹ
1 አብነት ትምህርት የሚያውቅ
2 ቻናሉ የሚያስፈልገውን ነገር ለመልቀቅ በቂ ጊዜ ያለው
3 የተለያዩ ትምህርቶችን ስብከቶችን ጽሁፎችን ሰብስቦ አዘጋጅቶ መልቀቅ የሚችል እና ፈቃደኛ የሆነ።

በውስጥ መስመር @channel_admin09 ላይ አናግሩን።

@abenet_tmhert @abenet_tmhert
@abenet_tmhert @abenet_tmhert
1.4K viewsedited  04:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 19:48:29
በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለኢየሱስ የተባሉ ግለሰብ በሕገ ወጥ መንገድ በተከናወነው "ሢመተ ጳጳሳት" በመሳተፋቸው በመጸጸት ይቅርታ ጠየቁ !

መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለኢየሱስ የተባሉ ግለሰብ በሕገ ወጥ መንገድ በተከናወነው "ሢመተ ጳጳሳት" በመሳተፋቸው በመጸጸት ይቅርታ ጠየቁ።

ግለሰቡ የይቅርታ ደብዳቤያቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) አቅርበዋል።

ግለሰቡ የይቅርታ ደብዳቤያቸውን ያስገቡት ቅዱስ ሲኖዶስ በሕገወጥ መንገድ ለተሾሙ አካላት የሰጠውን ቀነ ገደብ ተጠቅመው መሆኑ ተገልጿል።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
4.0K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 11:30:52 #ደብረ_ዘይት
(የዐቢይ ጾም አምሥተኛ ሳምንት)

ደብረ ዘይት የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም መምጣት የምናስብበት፣ የመምጫው ምልክት የሆኑትን ነገሮች እየመረመርን ራሳችንን በንስሐ ሕይወት የምናዘጋጅበትና ከዘላለም ፍርድ ኩነኔ ለመዳን እንደ ቃሉ መመላለስ እንዳለብን የምናስብበት ነው። ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁም ተብለናልና ሁልጊዜ ዝግጁና ስንዱ ሆነን እንደቃሉ ለመኖር እስከ መጨረሻው ጸንተን ለመዳን እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይትከወስ ኲሉ ኃይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኲሎሙ ኃጥአነ ምድር፡፡ ወይወርድ እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ ወበ አዕላፍ መላእክቲሁ በንፍሐተ ቀርን ዘእም ኀበ እግዚአብሔር ይምሐረነ አብ በይእቲ ሰዓት እሞተ ኃጢአት እስመ ገባሬ ሕይወት ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት፡፡
ትርጉም:-
ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ ተዘጋጅታችሁም ኑሩ፤ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እስከ መጨረሻው የጸና እርሱ ይድናል፡፡የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ የሰማያትና የምድር ኃይላት ሁሉ ይናወጣሉ። ያን ጊዜ በምድር ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለቅሳሉ አላቸው፡፡ ጌታችንም ከባሕርይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ በመለከት ድምፅ ከአእላፍ መላእክት ጋር በግርማ መለኮቱ ከሰማይ ወደ ምድር ይወርደል፡፡

#የዕለቱ_ምንባባት

1ኛተሰ.4÷13-ፍጻ፡-
ወንድሞቻችን ሆይ÷ ስለ ሞቱ ሰዎች÷ ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ ልታውቁ እንወዳለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ እንደ ተነሣ ካመንን እንዲሁ እግዚአብሔር ሙታንን በኢየሱስ ያስነሣቸዋል ከእርሱም ጋር ያመጣቸዋል፡፡

2ኛ ጴጥ.3÷7-14፡-
አሁንም ሰማይና ምድር በዚያ ቃል ለእሳት ተዘጋጅተዋል፤ ኃጥኣን ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀንም ተጠብቀዋል፡፡ነገር ግን ወንድሞቻችን ሆይ÷ ይህን አትርሱ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ አንዲት ቀን እንደ አንድ ሺህ ዓመት÷ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን ነውና፡፡

ሐዋ. 24÷1-21፡-
በአምስተኛውም ቀን ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከመምህራኑና ጠርጠሉስ ከሚባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳውሎስንም በአገረ ገዢው ዘንድ ከሰሱት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)

#የዕለቱ_ምስባክ

መዝ. 49÷2
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ፡፡
ትርጉም፦
እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፡፡
አምላካችንም ዝም እይልም፤
እሳት በፊቱ ይነድዳል በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ፡፡

#የዕለቱ_ወንጌል

ማቴ. 24÷1-25፡-
ጌታችን ኢየሱስም ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው የቤተ መቅደሱን የሕንጻ አሠራር አሳዩት፡፡ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፤ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፡፡” (ተጨማሪ ያንብቡ)

#የዕለቱ_ቅዳሴ፦ ቅዳሴ አትናቴዎስ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
864 views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 18:54:06 #ተግሣፅ_ዘቅዱስ_ኤፍሬም

ሕይወትህን በአግባቡ መምራት ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ ትሕትናን ተለማመድ፤ ያለ ትሕትና ተገቢውን ሕይወት መምራት አይቻልም፡፡ ሥራህን ሁሉ በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጀምር፡፡ ያን ጊዜ ፍሬዎችህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይደርሳሉ።

ሰው ከትሕትና ከራቀ ከትክክለኛው መንገድ ርቋል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የተወ ሰውን ርኵስ መንፈስ እንደ ሳውል ያስጨንቀዋል። የጠላት ወጥመድ በማር የተቀባ ነው፡፡ በማር ጣዕም የሚማረክ ሰው ሐዘንን ሁሉ በያዘ ወጥመድ ይያዛል። ትሕትናን ውደዱ፤ ያን ጊዜ ከሰይጣን ወጥመድ ውስጥ አትወድቁም፡፡ በትሕትና ክንፍ በበረራችሁ ቁጥር ሁል ጊዜ ከጠላት ወጥመድ በላይ ትሆናላችሁ።

ግልፍተኝነት እንደ በሰበሰ ረጅም ዛፍ ነው፤ ቅርጫፎቹ ሁሉ በቀላሉ የሚሰበሩ ናቸው᎓᎓ አንድ ሰው በወጣባቸው ጊዜ ከወጣበት ከፍታ ወዲያውኑ ይወድቃል፡፡ በመልካም ሐሳብ ልቡናው የበራ ሰው ግን ምስጉን ነው፤ ክብሩም ታላቅና ዘላለማዊ ነው።

እንግዲህ ራሳችንን ለመቆጣጠር እንጣር ያን ጊዜ ኃጢአታችንን እንረዳለን፡፡ ያን ጊዜም ሁል ጊዜ ራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን፤ እንደ እባብ በእብሪት መወጠርን እና ራሳችንን ከፍ ከፍ ከማድረግ እንቆጠባለን፡፡ እንግዲህ ራሳችንን ዝቅ ዝቅ ማድረግን እንውደድ፤ በንጹሕ ልቡና ሆነን ምናልባት የተሰጠንን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኃጢአት ከማቆሸሽ እንታደግ ይሆናል።

መልካም ጸሎት በሳግ እና በዕንባ የታጀበ ነው፤ በተለይ ደግሞ በምሥጢር የሚፈስ ዕንባ፣ በልቡናው ከፍታ ሆኖ የሚጸልይ ጌታውን በፊቱ ያያል። እኛ የምንኖረውና የምንሔደው በእርሱ ፈቃድ ነውና። ልቡናችሁ ከጠነከረ በጌታችን ፊት አልቅሱ እርሱ የዕውቀትን ብርሃን ይገልጥላችኋል፤ ወደ እርሱ የሚወስዳችሁ አዲስ ልብንም ይሰጣችኋል።

ንስሓ የገቡና ምሕረት የለመኑ ሰዎች ዕዳቸው ተሰረዘላቸው፤ ነገር ግን ለሠራኸው በደል ምሕረት ስትለምን ወንጀልን እና በደልን፤ በወንድምህም ላይ ቂም መያዝን መተው ይገባሃል። ፍቅር ሳይኖርህ ወደ እግዚአብሔር የምታደርገው ልመና ከተዘጋው በር ውጭ ይቀራል፡፡ የጸሎትን በር የሚከፍት ፍቅር ብቻ ነው፡፡

ወንድምህን ብታስቀይም እግዚአብሐርን ታሳዝናለህ፤ ካንተ ጋር ካለው ከወንድምህ ጋር ሰላምን ከፈጠርህ ግን በሰማይ ካለው ከእግዚአብሔር ጋር ትታረቃለህ፡፡ ወንድምህን በፍቅር ብትቀበለው፣ በደሉንም ይቅር ካልከው እግዚአብሔርን ተቀበልክ፡፡

ስለዚህ በተናደዱ ሰዎች በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅ፤ እንግዲህ የተበሳጩትን በማስደሰት እግዚአብሔርን አስደስተው፣ በታሰሩት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን ጎብኘው፣ በተራቡት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አብላው፤ በታረዙ ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አልብሰው፣ መንገደኛን በመቀበል እግዚአብሔርን በአልጋህ ላይ አስተኛው፤ እግሮቹንም እጠበው፣ በማዕድህም አስቀምጠው፣ እንጀራህንም ከእርሱ ጋር ተካፈል፤ ጽዋህንም ስጠው᎓᎓ እርሱ ታላቅ ፍቅሩን አሳይቶሃልና፤ እርሱ ስለ አንተ ብሎ ትበላው ዘንድ ሥጋውን ቆርሶልሃል፣ ትጠጣው ዘንድም ደሙን አፍስሷል።

(#ድርሳነ_ቅዱስ_ኤፍሬም ገጽ 334 - 336 -በዲ/ን መዝገቡ ከፍያለው የተተረጎመ)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
974 views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 10:54:04
ማስታወቂያ

ሰላም የዚህ ቻናል ተከታታዮች

ማስታወቂያ ማሰራት ለምትፈልጉ ብቻ

ምርትና አገልግሎታችሁን እንዲሁም አዲስ የከፈታችሁትን  ቻናል ወይም ግሩፕ ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ የማስታወቂያውን ይዘት ተመልክተን ካረጋገጥን በኋላ በተመጣጣኝ ዋጋ የምንሰራ መሆኑን ስንገልፅ በደስታ ነው።

ማስተዋወቅ የምትፈልጉትን በዚህ አድራሻ
@channel_admin09 ላይ መላክ ትችላላችሁ።

በተመጣጣኝ ዋጋ ነው
1.3K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 08:50:52 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መጋቢት አምስት በዚህች ዕለት ተአምራቱና ትሩፋቱ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነ ተጋዳይ አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዕረፍቱ ቀን መታሰቢያ ሆነ።

ለእግዚአብሔር ምሥጋና ይሁን፤ እኛንም በጻድቁ ጸሎት ይማረን፤ በረከቱም ከእኛ ጋር ትሁን፤ ለዘለዓለሙ አሜን።

እንኳን ለጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዕረፍት መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ!

ሙሉ ታሪኩን INSTANT VIEW የሚለውን ነክታችሁ አንብቡት!!

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.4K views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 21:35:49 Share 'መጋቢት 5ማኅሌት.pdf'

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
845 viewsedited  18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 20:18:23 #መጻጉዕ- የዐቢይ ጾም አራተኛ ሣምንት

በዐቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት መካከል አራተኛው እሑድ መጻጉዕ ይባላል፡፡ መጻጉዕ የተባለበት ምክንያት በዚሁ ሰንበት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ድውያንን መፈወሱን ዕውራንን ማብራቱን የሚያነሣ በመሆኑ ነው፡፡ «38 ዓመት የታመመውን መጻጉዕን ኢየሱስ አዳነው» እንዲሁም ልጁ የታመመበት የመቶ አለቃው "ጌታዬ በቃልህ እዘዝ ልጄ ይድናል፡፡ በቤቴ ጣርያ ሥር አንተ ልትገባ አይገባህም" አለው። "ጌታ በሚያልፍበት መንገድ አንድ ዕውር ፈውሰኝ" ብሎ ጮኸ የሚመሩት ሰዎች ዝም በል አሉት፡፡ ዕውሩ ግን እምቢ ብሎ "የዳዊት ልጅ ጌታ ይቅር በለኝ ዕርዳኝ" እያለ ጩኸቱን ቀጠለ፡፡ "በሰንበት ኢየሱስ መጻጉዕን ተነሥ አልጋህን ተሸከም ባለው ጊዜ ቀኑ ሰንበት ነበረ፡፡ መጻጉዕም አልጋውን ተሸክሞ ወደ ቤቱ ገባ የእግዚአብሔር ልጅ በሰንበት ፈውሷልና "በሰንበት ድውያንን ፈወሰ የዕውራንንም ዓይኖች አበራ" እያለ 38 ዓመት በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ ተይዞ ሲማቅቅ የኖረውን መጻጉዕንና ሌሎቹን በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙትን ሕሙማን መፈወሱን በጠቅላላው ለምፅ ማንጻቱን፣ ዕውር ማብራቱን፣ አንካሶችን ማርታቱን፣ ልምሾዎችን ማዳኑን፣ አጋንንትን ማውጣቱን፣ ወዘተ እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ዕለቱና ሳምንቱ መጻጉዕ ተብሏል፡፡

ስለዚህም ይህ ሰንበት የሕሙማን ፈውስ መታሰቢያ ዕለት ነው ማለት ይቻላል፡፡ በነዚህ ሁሉ ታሪኮች የመጻጉዕንና የሌሎቹን ሕሙማን ሁሉ ደኅንነት ታሪክ እንረዳለን፡፡ የሰንበቱም ስያሜ ልብ ወለድ አጠራር ሳይሆን የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢርና የጾመ ድጓውን ይትበሀል ተከትሎ የተሰየመ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

#የዕለቱ_ምንባቦች፦
1ኛ. የቅ.ጳውሎስ መልእክት ወደ ገላ. 5÷1-26
2ኛ. የቅ. ያዕቆብ መልእክት 5÷14-20
3ኛ. የሐዋርያት ሥራ 3÷1-12

#የዕለቱ_ምስባክ፦
መዝ 4ዐ(41)÷3
እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኵሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ።

(እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ላይ ሳለ ይረዳዋል፡፡ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል እኔስ አቤቱ ማረኝ፡፡) መዝ 4ዐ÷3  የሚለው ይሆናል፡፡

#የዕለቱ_የወንጌል፦
በዮሐንስ ወንጌል 5፥1-25 ድረስ ያለው ነው፡፡

ያንን ተስፋ ያልነበረውን በሽተኛ ከደዌ ሥጋው ፈውሶ ሕይወትን የሰጠው አምላክ፣ እኛንም በውስጥ በአፍአ ካለብን ደዌ ሥጋና ደዌ ነፍስ እንዲፈውሰን፤ ቁስለ ኃጢአታችንን እንዲያደርቅልን፣ በሕይወትና በጤና እንዲጠብቀን የእርሱ የጌታች ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.0K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 18:05:32 ህገ ወጦቹ ጳጳስ ነን ባይ አካላት ከጊንቢ ወለጋ እና ነቀምት ከተሞች በፌዴራል ፓሊስ እና ኦሮሚያ ልዩ ኃይል ዛሬ መጋቢት 2 ተለቅመው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑ እየተሰማ ነው::

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.5K views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ