Get Mystery Box with random crypto!

የአብነት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ abenet_tmhert — የአብነት ትምህርት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ abenet_tmhert — የአብነት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @abenet_tmhert
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.99K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ መንፈሳዊ ቻናል
፦የግእዝ ቋንቋን ጨምሮ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ፡፡
ለአስተያየቶ @Channel_admin09 ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-04-14 08:41:31
"ከመ ኪያነ ይቤዙ እግዚእ ኮነ ገብረ"
"እኛን ይቤዠን (ቤዛ ይሆነን) ዘንድ ጌታ ባሪያ ሆነ "

ለኛ ብሎ ራሱን ላዋረደልን ራሱን ለሰጠን መከራችንን ለተሸከመልን ስለበደላችን ለደቀቀልን በሞቱ ህይወትን ለሰጠን እጆቹን እግሮቹን ለተቸነከረልን ራሱን በዘንግ ለተመታልን መራራ ሀሞት ለጠጣልን በሞቱ የእግዚአብሔር ልጆች ላደረገን ለአምላካችን ለጌታችን የስቅለት በአል መታሰቢያ እንኳን አደረሳችሁ።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

@abenet_tmhert
@abenet_tmhert
@abenet_tmhert
699 viewsedited  05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:56:30 በሕማማት ወቅት የሚሰሙ የምንላቸው ከሌላ ቋንቋ የተወሰዱ ቃላት ትርጉም

በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

"ኪርያላይሶን"

ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ “ኪርዬ ኤሌይሶን” ነው፡፡ “ኪርያ” ማለት “እግዝእትነ” ማለት ሲሆን “ኪርዬ” ማለት ደግሞ “እግዚኦ”ማለት ነው፡፡ ሲጠራም “ኪርዬ ኤሌይሶን” መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም “አቤቱ ማረን” ማለት ነው፡፡ “ኪርያላይሶን” የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው “ዬ”ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ “ኤ” በመሳሳባቸው በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረው ነው፡፡

"ናይናን"

የቅብጥ(ጥንታዊው የግብጻውያን ) ቃል ሲሆን ትርጉሙ “መሐረነ፣ ማረን” ማለት ነው፡፡

"እብኖዲ"

የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “አምላክ” ማለት ነው፡፡ “እብኖዲ ናይናን” ሲልም “አምላክ ሆይ ማረን” ማለቱ ነው

"ታኦስ"

የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ጌታ፣ አምላክማለት ነው፡፡ “ታኦስ ናይናንማለትም “ጌታ ሆይ ማረን” ማለት ነው፡፡

"ማስያስ"

የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ “መሲሕ” ማለት ነው፡፡ “ማስያስ ናይናን” ሲልም “መሲሕ ሆይ ማረን” ማለት ነው

"ትስቡጣ"

ደግ (ቸር) ገዥ ማለት ሲሆን "ትስቡጣ ናይናን" ማለት ቸር ገዥ ማረን ማለት ነው።

"አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ"

የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ” ማለት ነው፡፡

"አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ"

የቅብጥ ቃል ሲሆን “ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን” ማለት ነው

"አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ"

የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ፤የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን” ማለት ነው፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

@abenet_tmhert
@abenet_tmhert
@abenet_tmhert
1.3K views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 16:50:03 #የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ፡፡…..
ትርጉም: “በፋሲካ በዓል ሰሞን የእውነት አምላክ ደቀ መዛሙርት ወደ ደብረ ዘይት ቀረቡ፤ በሀገረ እግዚአብሔር (ኢየሩሳሌም) አቀበቱ ላይ ብዙ አረጋውያንና ሕፃናት የዘንባባ ቅጠል ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት፣ በአህያ ውርንጫ ላይ ተጭኖ በፍጹም ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ለእነዚህ ኃይልና ሥልጣንን ይሰጣቸዋል።

#መልዕክታት
ዕብ.8÷1-ፍጻ. ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተተከለች ናት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)

1ኛ ጴጥ.1÷13 ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)

#ግብረ_ሐዋርያት
የሐዋ.8÷26-ፍጻ. የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡” እሆም÷ (ተጨማሪ ያንብቡ)

#ምስባክ
"ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ፡፡ በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡ እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ" መዝ.80÷3
ትርጉም፦ በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና÷ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና፡፡
ወይም
"እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ፡፡ በእንተ ጸላዒ፡፡ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡" መዝ.80÷2
ትርጉም፦ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡ ስለ ጠላት÷ ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡

#ወንጌል
ዮሐ.12÷1-11 ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)

ቅዳሴ ፡- ቅዳሴ ዘጎርጎርዮስ፡፡

@abenet_tmhert
@abenet_tmhert
@abenet_tmhert
1.7K views13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 12:14:32 @Memhir_sirak
640 views09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 19:32:44
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ጥንተ ስቅለቱ አደረሳችሁ።

መጋቢት 27 የአመቱ መድኀኔዓለም ወይም ጥንተ ስቅለቱ ለመድኀኔዓለም ለምን እንደሚባል ከላይ የተለቀቀውን ጽሁፍ በማንበብ መረዳት ትችላላችሁ።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

@Z_TEWODROS
@Z_TEWODROS
@Z_TEWODROS

Comment @Channel_admin09
633 views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 21:41:09 የመጋቢት 27 ሥርዓተ ማኅሌት
@abenet_tmhert
@abenet_tmhert
@abenet_tmhert
1.8K viewsedited  18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 19:24:36 ወረብ ዘመጋቢት መድኃኔዓለም

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE

•✥• @Z_TEWODROS •✥•
•✥• @Z_TEWODROS •✥•
•✥• @Z_TEWODROS •✥•
2.0K viewsedited  16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 22:43:43 #የዕለቱ_የሰንበት_መዝሙር_እና_ግጻዌ

#መዝሙር፦
ሖረ ኀቤሁ ዘስሙ ኒቆዲሞስ ወይቤሎ ለኢየሱስ ረቢ ሊቅ ንሕነ ነአምን ብከ ከመ እምኃበ አብ መጻእከ ከመ ትኩን መምህረ፤ ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ አንሥአኒ በትንሣኤከ፡፡ (ስሙ ኒቆዲሞስ የተባለው ሰው ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄደ፤ መምህር ሆይ ልታስተምር ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ እንደመጣህ እናምንብሃለን አለው። የአንበሳ ደቦል ተኛህ፣ አንቀላፋህም፤ በትንሣኤህ አንሣኝ።)

#መልዕክታት፦
ሮሜ 7÷1-12
"ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን? ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች።...

1ኛ ዮሐ. 4 ÷18 - ፍጻሜ
ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። .....

የሐዋ.ሥራ 5÷34 - ፍጻሜ
በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ በሸንጎ ተነሥቶ ሐዋርያትን ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ......

#ምስባክ፦
መዝ.16፥3
ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡፡
አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፡፡
ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመ ሕያው፡፡
ትርጉም፦
በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው÷
ፈተንኸኝ÷ ዐመፅም አልተገኘብኝም፡፡
የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር

#ወንጌል፦
ዮሐንስ 3፥1-12
"ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ። መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ
የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው።....

#ቅዳሴ - ዘእግዝእትነ ማርያም [ጎሥዐ]

@abenet_tmhert
@abenet_tmhert
@abenet_tmhert
476 views19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 19:58:22 #እንደ_አባቶቻችን_ከተመለስን_ይምረናል

#ጥንት በአባቶቻችን ዘመን አስጨናቂ መከራ በተነሣ ጊዜ፣ ልመናን የሚያውቁ አባቶችና እናቶቻችን ራሳቸውን አዋርደው በፍጹም ንስሐ የፈጣሪያቸውን ምሕረት ደጅ ጠኑ። እርሱም ጩኸታቸውን ሰምቶ ዘንበል አለላቸው። መዓቱንም ከእነርሱ መልሶ በገጸ ምሕረቱ ጎበኛቸው። በቁጣው ቀን ተስፋ ያደረጉት ቸርነቱ አላሳፈራቸውም።

#ዛሬስ? ዛሬም የእኛ ንስሐ እንደ አባቶቻችን እውነተኛ ከሆነ፣ በፈጣሪያችን ቸርነት ላይ ያለን መተማመን ከቀደሙት እናቶቻችን ካላነሰ፣ አምላካችን እኛን ይቅር ለማለት የታመነ ነው። መድኃኔዓለም መለወጥ እንደሚስማማው ደካማ የሰው ልጅ አይደለም። ልክ በፀሐይና በመሬት መካከል ባለ ዑደት (ዙረት) ምክንያት፣ አንዱ የመሬት ክፍል ከፀሐይ ብርሃን ተቀብሎ ሲያበራ በሌላኛው በኩል ያለው ደግሞ በግርዶሽ እንደሚጨልም እንዲሁ፣ የእግዚአብሔር ብርሃን (ቸርነት፣ ምሕረቱ) ለአንዱ አብርቶ ለሌላው የሚጋረድ አይደለም። ለብርሃኑ የተዘጋጀና በኃጢአት ጉድፍ ያልታወረ ዓይነ ልቡና እስካለን ድረስ የምሕረቱ ነጸብራቅ ለዘወትር በእኛ ላይ እንዳበራ ነው። ብቻ ንስሐችን እንደ ቀደሙት እናቶቻችን፣ መመለሳችንም በቃልና በተግባር እንደ ተመለሱት እውነተኞቹ አባቶቻችን ይሁን!።

"በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ"
ያዕ 1፥17

@abenet_tmhert
@abenet_tmhert
@abenet_tmhert
1.5K viewsedited  16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 19:09:46
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በመግለጫው አሳወቀ።

ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ማዕረግ እንዲጠሩም ገልጿል።

በዚህ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብለው እንደሚጠሩና ወደ ነበረ የአባትነት ኃላፊነታቸው የሚመለሱ ሲሆን በይቅርታ የተመለሱት በቁጥር 20ዎቹ መነኮሳትም ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው የክህነት አገልግሎት እንዲያገለግሉ ሆኖ በምንኩስና ስማቸው እንዲጠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE

•✥• @Z_TEWODROS •✥•
•✥• @Z_TEWODROS •✥•
•✥• @Z_TEWODROS •✥•
755 views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ