Get Mystery Box with random crypto!

የአብነት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ abenet_tmhert — የአብነት ትምህርት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ abenet_tmhert — የአብነት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @abenet_tmhert
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.99K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ መንፈሳዊ ቻናል
፦የግእዝ ቋንቋን ጨምሮ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ፡፡
ለአስተያየቶ @Channel_admin09 ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-02-23 08:24:38
"እስመ ትቤ ለዓለም አሐንጽ ምሕረተ
በሰማይ ጸንዓ ጽድቅከ
ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩይንየ።"
-መዝሙር 88፥2-4

"እንዲህ ብለሃልና። ምሕረት ለዘላለም ይመሠረታል፥ እውነትህም በሰማይ ይጸናል።
ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ፥"

-መዝሙር 88(89)፥2-4

እንኳን አደረሳችሁ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
790 viewsedited  05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 21:46:42 ዘግይተን በመልቀቃችን ይቅርታ እንጠይቃለን በቀጣይ ቀደም ብለን እንደምንለቅላችሁ እንገልፃለን !!
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
894 views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 21:43:15 የ የካቲት ኪዳመምህረት ሙሉ ስርአተ ማህሌት

እንኳን አደረሳችሁ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
957 viewsedited  18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 07:50:24 ዘወረደ - የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው እሑድ መዝሙርና ዝማሬ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
2.2K viewsedited  04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 16:30:54
ዘመቻ 15ሺ
እያንዳንዳችን ለ 10 ሰው ሼር እናድርግ

የአብነት ትምህርቶችን ለመማር በ telegram ብቻ መጽሐፍትን በpdf & voice ያግኙ
ውዳሴ ማርያም
የግእዝ ትምህርት
ወንጌለ ዮሐንስ
መዝሙረ ዳዊት
መጽሐፈ ሰዓታት እና ሌሎችን
ለመማር ይቀላቀሉን
ለ 10 ሰው ሼር በማድረግ እንዲቀላቀሉ እንርዳቸው !!!

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር ለ10 ሰው // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @abenet_tmhert •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•              
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.6K views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 08:20:46 ዘወረደ (የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት )

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡
‹‹ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ›› የሚልና ይህንን የመሳሰለ ጌታ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ሌላም ስም አለው #ጾመ_ሕርቃል ይባላል፡፡ ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን #ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

#ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ?
በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም ቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል። እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡

በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡

«ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምስጢሩ አምላክ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም በቅዱስ ፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት፣ ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ ይህም የሚታወስበት፣ የሚወሳበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ.3፥13፡፡

ሳምንቱ ሙሴኒ የተባለበትም ምክንያት በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት» «ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ» ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚያጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ከአለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው ምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን የሚያስታውስ ነው፡፡ /ዘፀ.24፥18፤ 1ኛ.ነገ.19፥8፤ ማቴ. 4፥1-4/፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
645 views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 16:30:40
ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው?
********************
“በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? ሰባት ጊዜ ነው? አለው። ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም።”
ማቴዎስ 18፥21-22

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.5K views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 15:04:09
እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ ስምምነቱን ሳይሸራረፍ እንደሚቀበሉና ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በቅዱስ ሲኖዶስ በመገኘት ቃላቸውን ሰጥተው አረጋግጠዋል ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳውቃለች።

እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አሕመድ በተገኙበት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ/ም በተደረገው ውይይት የተስማሙባቸውን (10) ዐሥር ነጥቦች ያለመሸራረፍ ለመፈጸም እንዲሁም ቀጣዩን ተግባር በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት ለማከናወን ተስማምተናል ሲሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት በመገኘት ቃላቸውን መስጠታቸው ተገልጿል።

EOTC

ምን ሆነዋል?

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
6.3K viewsedited  12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 22:25:45 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የራሳቸውን ሲኖዶስ አቋቁመናል ካሉ የቀድሞ አባቶች ጋር የደረሰችው ስምምነት መጣሱን አሳወቀች።

የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ አዲሱ ሲኖዶስ በሚል አዲስ ስያሜ ስምምነቱን የሚጥስ መግለጫ አውጥቷል ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የምንሰማቸው ነገሮች ሁሉ እንደገና ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍል አባቶችን ከልጆች ልጆችን ከአባቶች የሚያሻክሩ ነገሮችን እየሰማን ሲል ተደምጧል።

ከሁለት ቀናት በፊት በተፈጸመው ስምምነት ሰላም ቢፈጠርም አሁን ግን ሃይማኖቱንም ሕጉንም መልሰው መላልሰው ጥሰውታል፤ ሹመታቸው ሕጋዊ እንደሆነና በምንም ይሁን በምን የማይሻር መሆኑንም መልእክት አስተላልፈዋል።

ሻሚና ተሻሚ በአስተሳሰባቸውም ሆነ በአነጋገራቸው ሁሉ በእኩል ደረጃ እንደሆኑም ተናግረዋል፤ 25 የተባሉትም የትናንትና ካህናት አገልጋዮች አሁንም ኤጲስ ቆጶሳት እንደሆኑ ተደርጎ ተንጸባርቋል።

በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ነገሩን ለማጥራት ብንጠብቅም ቀኑን ሙሉ አንመጣም ሲሉ ዉለው 10 ሰዓት ላይ ግን ለማንም ለማን መጣን ሳይሉ በቤተ ክህነት ግቢ በሚገኘው ማረፊያ ቤታቸው ገብተዋል።

ሆኖም ግን በስምምነቱ መሠረት የብሔር ብሔረሰቦች ኤጲስ ቆጶሳት ሿሚዎች ነን ያሉ 3 ሊቃነጳጳሳት ዛሬ የሰጡትን መግለጫ እስካላስተባበሉ ድረስ ከቤተክህነት እንዲወጡ ይደረጋል ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ አስታውቋል።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.6K views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 07:20:57 እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ቤተ ክርስቲያናችን ከመከፋፈልና ሀገራችንም ከመፍረስ ድናለች። መጨረሻው ፍጹም እውነት ይሆንልን አምላከ ቅዱሳን ይርዳን። ከዳግም መከራ እንዲሰውረን እንዲሁም ችግር ቢመጣም እንደተለመደው በአይን ጥቅሻ በመናበብ እንወጣው ዘንድ በጾመ ነነዌ እንዳሳለፍነው በዐቢይ ጾምም በቤተክርስቲያን በመሰባሰብ በንስሐና በትህትና ሆነን ከአባቶች የሚወርዱ ትዕዛዛትን ብቻ በመፈጸም እናሳልፍ ዘንድ ማሳሰብ እንወዳለን።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
775 views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ