Get Mystery Box with random crypto!

የአብነት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ abenet_tmhert — የአብነት ትምህርት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ abenet_tmhert — የአብነት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @abenet_tmhert
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.99K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ መንፈሳዊ ቻናል
፦የግእዝ ቋንቋን ጨምሮ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ፡፡
ለአስተያየቶ @Channel_admin09 ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-02-14 21:47:55
ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ክስተት ጋር በተያያዘ የእምነቱ ተከታዮች መታሰራቸውን እና አብዛኞቹም ወደ አዋሽ ሰባት የጦር ካምፕ መወሰዳቸውን የቤተ ክርስቲያኗ ጠበቆች ለቢቢሲ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አያሌው ቢታኔ እስካሁን ባላቸው መረጃ ከ200 በላይ ምዕመናን መታሰራቸውን ተናግረዋል።

ሆኖም በተጨባጭ ደረጃ ቁጥሩ በትክክል እንደማይታወቅ እና በሚቀጥሉት ቀናትም ለዚህ ተግባር የተዋቀረው የመረጃ አካልም ዝርዝሩን ያቀርባል ብለዋል።

እስሩ በአብዛኛው የተከናወነው በአዲስ አበባ እና በአጎራባች አካባቢዎች ሲሆን ወደ አዋሽ ሰባት የተወሰዱ ምእመናን ቁጥርም በርካታ ስለመሆናቸው መረጃ አለን ብለዋል።

አዋሽ ሰባት ውስጥ ምን ያህል ግለሰቦች እንደታሰሩ በትክክል ባያውቁም ከ100 አስከ 200 የሚሆኑ የዕምነቱ ተከታዮች ወደ ስፍራው መወሰዳቸውን ገልጸዋል።

ከቢቢሲ አማርኛ የተወሰደ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.4K viewsedited  18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 21:37:59
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት (EOTC TV) የኦሮሚኛ ቋንቋ ጋዜጠኛ ዲ/ን ዮሴፍ ከተማ ታሰረ።

ዛሬ ሰኞ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 አካባቢ በሥራ ጉዳይ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ መካኒሳ አካባቢ ለጥያቄ እንፈልግሃለን የሚሉ የመንግሥት የጸጥታ አካላት እንደወሰዱት ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል።

የኦሮሚኛ ቋንቋ ጋዜጠኛ ዲ/ን ዮሴፍ ከተማ በወቅታዊ ጉዳይ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተደጋጋሚ ቃለ ምልልሶች በማድረግ ወደ ምእመናን ሲያደርስ ቆይቷል።
(EOTC TV)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.1K viewsedited  18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 13:23:23 " አሁንም ቢሆን በርካታ ሥራዎችን የምንሰራው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ነው " - ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤

ቤተክርስቲያኗ ከባንክ አገልግሎት ጋር በተያያዙ የሚነገሩባት #አሉባልታዎች ትክክል እንዳልሆኑ ገለፀች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤ ከቤተክርስትያኗ የባንክ አገልግሎት  ጋር በተያያዘ በርካታ አሉባልታ ይነሳል ብለዋል።

" ቤተክርስቲያን የምትሰራው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ነው። " ያሉት ብፁዕነታቸው " ከዓባይ ባንክ ጋር ሥራ የጀመርነው በህጋዊ አሰራር በጨረታ በተደረገ ሂደት  አሸናፊ ሆኖ በመገኘቱ ነው። " ብለዋል።

" ከዓባይ ባንክ ይልቅ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኦሮሚያ ባንክ ያለን ገንዘብ ይበልጣል። " ያሉት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤ " ዓባይ ባንክ ያለን ገንዘብ ተንቀሳቃሽና ለሰራተኛው የብድር አገልግሎት በማቅረብ ለሰራተኛው የመኪና፣ የቤትና የልዩልዩ ግዤዎችን ለመፈጸም የሚያስችል አገልግሎት የሚሰጥበት የባንክ አገልግሎት ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል፤ ቤተክርስቲያኗ በኦሮሚያ ባንክ የማይንቀሳቀስ ገንዘብ ማስቀመጧን ብፁዕነታቸው ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው " በጣም መጠነኛ ገንዘብ በአዋሽ፣ በሕብረትና በአቢሲኒያ ባንኮች አስቀምጣለች ፤ ከዚህ ውጪ በሌላ ባንክ  ወይም በአማራ ባንክ የተቀመጠ  ምንም አይነት የማዕከላዊ የቤተክርስቲያን አስተዳደር ገንዘብ የለም። " ሲሉ አሳውቀዋል።

" የተቀመጠ ገንዘብ አለ ከተባለም  #በማስረጃ  ማቅረብ ይቻላል " ያሉ ሲሆን " አሁንም ቢሆን በርካታ ሥራዎችን የምንሰራው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ነው ። " ሲሉ ገልጸዋል።

መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት ነው።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
2.1K views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 10:22:31
ሩሲያ ገብቷል!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ ለሁለትዮሽ ውይይት ሩሲያ/ሞስኮ/ መግባቱ ተገለፀ ።

በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድኑ አባላት

የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጊዜያዊ እና ቋሚ ፕሮጀክቶች መምሪያ ኃላፊ መልአከ ሕይወት አባ ወ/ኢየሱስ ሰይፉ እንደሚገኙበት ተገልጿል።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
7.6K viewsedited  07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 18:21:06
"እውነትን ተረድተው ስለመጡ ቤተ ክርስቲያን ደስተኛ ናት። ሌሎች በማወቅም ባለማወቅም የሄዳችሁ አሁንም ለመምጣት የተቸገራችሁ ቤተ ክርስቲያን በሯ ክፍት ነው::"

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

"መከራውን ቤቴ ሁኜ ልቀበል ብለው ስለመጡ ቤተ ክርስቲያን ደስ ይላታል፤ ሌሎችም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ከእኛ ጋር ናቸው ተብላችሁ ተታላችሁ የሄዳችሁ፤ ፀፀት ውስጥ እንዳላችሁ እናውቃለን። ሌሎች ለመምጣት እየፈለጉ ቁልፍ ተይዞባቸው እንደተቸገሩም ሰምተናል:: "

ብፁዕ አቡነ አብርሃም

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
4.5K viewsedited  15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 15:12:55
ሰበር ዜና
እነ አቶ አካለ ወልድ ሞገስ በሕገወጥ መንገድ ልብሰ ጵጵስና ካለበሷቸው መነኮሳት መካከል በቀድሞ ስማቸው አባ ንዋየ ሥላሴ አክሊሉ ባደረጉት ሥራ ተጸጽተው በዛሬው ዕለት ይቅርታ ጠየቁ !

“...እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።” ሉቃ 15፥7

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
6.3K views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 20:18:32ልጅ_ቢኒ እና ፓስተር_ቢኒያም_ሽታዬ አንድ ላይ ታስረው ከታሰሩበት አዲስአበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዝቅ ብሎ የሚገኘው ከሶርአምባ ሆቴል ፊትለፊት የሚገኘው አራዳ ፍ/ቤት ቀርበው ነበር እናም ፖሊስ ተለዋጭ ቀጠሮ ያስፈልገኛል በማለቱሉ ችሎቱ የ7ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ ለአርብ 5 ሰዓት እንዲቀርቡ አዟል::

መምህር ምሕረተአብ አሰፋ እና የማንቂያ ደውል አገልጋዮች ዲ/ን አማኑኤል አያሌው እንዲሁም ዲ/ን ኪሩቤል አሰፋ በዛሬው ዕለት ታፍነዋል !

● በተለያዩ ስፍራዎች እስሩ ፣ እንግልቱና ማሳደዱ ከማባራት ይልቅ ቀጥሏል። ከነብሱ አምርሮ ቤተክርስቲያንን የሚጠላ ፤ አባቶችን የማያከብር ወደረኛ ገጥሞናል። ከጸናንበት መሰረት አንዛነፍም። ጉዞው የሰማዕታቱ የእምነት ጉዞ ነው።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
2.8K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 19:15:21
በዚሁ (በነገው) ዕለትም ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁሉም በየአጥቢያችሁ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ዓውደ ምሕረት ላይ ባለመቅረት የተለመደውን የዕለተ ሰንበት የሥርዓተ ቅዳሴ፤ የጸሎት፣ የምሕላ እና የትምህርተ ወንጌል ከወትሮው በተለየ የመንፈሳዊ ሥርዓት በማከናወን እንድታሳልፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ

ሼር አርጉት ነገ በየአጥቢያችን ያሉ ቤተክርስቲያኖችን በህዝብ ማእበል አጥለቅልቀን ጠላት ዲያብሎስን በጾም እንደቀጣነው እግዚአብሔርን በማመስገን ደግመን እንቀጣዋለን።
ሼር ሼር ሼር ለተዋህዶ ልጆች

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
8.7K views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 16:40:30 በተያያዘ ዜና
በሻሸመኔ አፈና እንደቀጠለ ነው!

ሕገ ወጡን ሹመት አልቀበልም በማለቷ ምክንያት በኦሮሚያ የጸጥታ ኃይሎች በተደረገው ግድያ ውድ ልጆቿን የገበረችው የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት መናገሻዋ ሻሸመኔ ዛሬም ብዙ ልጆች እየታሠሩባት ይገኛሉ።

እሥሩም ከወጣቶች ወደ ከተማዋ ባለኃብቶችና ሽማግሌዎች ተሸጋግሯል።

በዛሬው ዕለት በከተማዋ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ባለ ኃብቶች፣ የከተማዋ የተከበሩ ሽማግሌዎችና እጅግ ብዙ ወጣቶች ታሥረዋል።

እንደመረጃ አድራሾቻችን ገለጻ ከሆነ በምእመናን ላይ የደረሰውን ሞትና አካል ጉዳት ለመሸፋፈንና ተጠያቂ እንዳይኖር ለማድረግ የመንግሥት አካላት የሚመለከታቸውን ሰዎች ሁሉ ምንም እንዳይናገሩ ለማስገደድ እየሞከሩ መሆናቸውም ተጠቁሟል።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
9.7K views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 16:39:53 መረጃ!

ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ወሊሶ ከተማ ያደረገውን ጉዞ ተከትሎ በተለያዩ ቦታዎች ግድያ፣ እሥርና ድብደባ መድረሱን መዘገባችን ይታወሳል።

በዚሁ ምክንያት የታሠሩት የዓለም ገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን  አገልጋዮች እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡና 'ምርመራ' ተብሎ የተከፈተውን መዝገብ የያዘው መርማሪ እንኳን እንዳልታወቀ ለተ.ሚ.ማ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በተጨማሪም በሰበታ መካነ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሕገ ወጡን ቡድን የሚደግፈው የጸጥታ ኃይል በመኪና አፍኖ ወስዶ አዳራሽ ውስጥ ያጎራቸው 300 የሚደርሱ ኦርቶዶክሳውያን እስካሁን ድረስ እንዳልተለቀቁና ለመጠየቅ ወደ እነርሱ የሚሔዱ ወንዶችን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ እየታሠሩ እንደሆነ ተገልጿል።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
7.3K views13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ