Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የራሳቸውን ሲኖዶስ አቋቁመናል ካሉ የቀድሞ አባቶች ጋር | የአብነት ትምህርት ቤት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የራሳቸውን ሲኖዶስ አቋቁመናል ካሉ የቀድሞ አባቶች ጋር የደረሰችው ስምምነት መጣሱን አሳወቀች።

የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ አዲሱ ሲኖዶስ በሚል አዲስ ስያሜ ስምምነቱን የሚጥስ መግለጫ አውጥቷል ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የምንሰማቸው ነገሮች ሁሉ እንደገና ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍል አባቶችን ከልጆች ልጆችን ከአባቶች የሚያሻክሩ ነገሮችን እየሰማን ሲል ተደምጧል።

ከሁለት ቀናት በፊት በተፈጸመው ስምምነት ሰላም ቢፈጠርም አሁን ግን ሃይማኖቱንም ሕጉንም መልሰው መላልሰው ጥሰውታል፤ ሹመታቸው ሕጋዊ እንደሆነና በምንም ይሁን በምን የማይሻር መሆኑንም መልእክት አስተላልፈዋል።

ሻሚና ተሻሚ በአስተሳሰባቸውም ሆነ በአነጋገራቸው ሁሉ በእኩል ደረጃ እንደሆኑም ተናግረዋል፤ 25 የተባሉትም የትናንትና ካህናት አገልጋዮች አሁንም ኤጲስ ቆጶሳት እንደሆኑ ተደርጎ ተንጸባርቋል።

በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ነገሩን ለማጥራት ብንጠብቅም ቀኑን ሙሉ አንመጣም ሲሉ ዉለው 10 ሰዓት ላይ ግን ለማንም ለማን መጣን ሳይሉ በቤተ ክህነት ግቢ በሚገኘው ማረፊያ ቤታቸው ገብተዋል።

ሆኖም ግን በስምምነቱ መሠረት የብሔር ብሔረሰቦች ኤጲስ ቆጶሳት ሿሚዎች ነን ያሉ 3 ሊቃነጳጳሳት ዛሬ የሰጡትን መግለጫ እስካላስተባበሉ ድረስ ከቤተክህነት እንዲወጡ ይደረጋል ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ አስታውቋል።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌