Get Mystery Box with random crypto!

የአብነት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ abenet_tmhert — የአብነት ትምህርት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ abenet_tmhert — የአብነት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @abenet_tmhert
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.99K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ መንፈሳዊ ቻናል
፦የግእዝ ቋንቋን ጨምሮ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ፡፡
ለአስተያየቶ @Channel_admin09 ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-03-09 06:10:01 አረጋዊ መንፈሳዊ

መጽሐፈ መነኰሳት ክፍል ሦስት
➥ይህ አረጋዊ መንፈሳዊ የተባለው መጽሐፍ ከጥንት የኢትዮጵያ ሊቃውንት የጻፉትና የተረጐሙት የኢትዮጵያ ቅርስ እንዳይጠፋ ቤተከርስቲያን በመጽሐፍ እጦት አንዳትቸገር የተለመደው ጸሎች እንዳይታጐል መነኰሳት ዘወትር እየመረመሩ እንዲጠቀሙበት ታተመ።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
609 viewsedited  03:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 13:52:35 የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አባቶች ጋር በወቅታዊ የቤተክርስትያን ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተገልጿል።

በዚህም ውይይት ወቅት ችግሮችን ለመፍታት ቃል የገቡ ቢሆንም አሁንም ችግሮች አልተፈቱም ተብሏል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ያቋቋመችው የሕግ ኮሚቴ አባል የሆኑት የሕግ ባለሙያና ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ለአዲስ ማለዳ የሰጡት ቃል ፦

" ፕሬዝዳንቱ በቤተክርስያን ጉዳይ የታሰሩ ሰዎች እስከ ዛሬ ማክሰኞ ድረስ ይፈታሉ ብለው ቃል የገቡ ቢሆንም፣ ሽንገላ የሚመስል ነገር እየተከናወነ ነው።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥትና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ሕግን የማስፈጸም ግዴታ እያለባቸው ያለባቸውን ኃላፊነት ባለመወጣታቸው ምክንያት አሁንም በርካታ የሕግ ጥሰቶችና የንብረት ውድመቶች እየደረሱ ነው።

ትናንት ሰኞ በፍርድ ቤት እግድ የተጣለባቸውና ከቤተክርስትያኗ ቀኖና ውጭ የተሾሙ ግለሰቦች በአሰላ የአቡነ ያሬድ መንበረ ጵጵስናን ሰብረው የገቡ ሲሆን፣ ይህም በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ድጋፍ የሚደረግ ሕገ-ወጥ ድርጊት ነው።

ሻሸመኔና አርሲ ነገሌን ጨምሮ በበርካታ የኦሮሚያ አካባቢዎች አሁንም በርካታ ካህናትና ምዕመናን ያለምንም ጥፋት ታስረው ይገኛሉ።

ከዚህ በፊትም በመንግሥት በሁለት ቀን ውስጥ ይፈታሉ ተብለው የነበሩ ታሳሪዎች ሳይፈቱ በርካታ ቀናት ተቆጥረዋል።

ይህንንም ተከትሎ መንግሥት ራሱ ለገባው ቃል ተገዢ እየሆነ አይደለም። በዚህም ምክንያት ካህናትና ምዕመናን ለበርካታ ችግሮች ተጋልጠዋል ቤተክርስትያኗም ጉዳት እየደረሰባት ይገኛል።

ቤተክርሰትያኗ ከመንግስት ጋር የደረሰችው ስምምነት በመንግሥት በኩል  ሊደረግ ታስቦ የነበረውን ሰልፍ የማስቀረት ጉዳይ ብቻ ተደርጎ መታየት የለበትም።

አሁን ባለው ሁኔታ ችግሩ እየከፋ ነው እየሄደ ያለው።

ምዕመናኑ ምንም እንኳን በሚፈጸሙ ድርጊቶች ያዘኑ ቢሆንም የቤተክርስትያን አባቶችን ትዕዛዝ እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

መንግስት የገባውን ቃል አልመፈጸሙ፣ በሕግ እንዲያስፈጽም የተሰጠውን ኃላፊነት አለመወጣቱና የያዘው አካሄድ ሕዝብና አገርን ዋጋ የሚያስከፍል ነው።

ለዚህም እስከ ዛሬ ማክሰኞ ድረስ ሁሉንም ጉዳዮችና የሕግ ጥሰቶች ለማስተካከል በኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት ሽመልስ አብዲሳ የተገባው ቃል እንዲፈጸም እንጠይቃለን።

የቤተክርስትያን ጉዳይ ወደ ከፋ ነገር ሳያመራ መንግስት ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል። "

በሌላ በኩል ፤ በአዋሽ ሰባት ከታሰሩ ወጣቶች መካከል ከ300 በላይ የሚሆኑት መለቀቃቸው የተሰማ ሲሆን ወጣቶቹ ብጹአን አባቶች በቦታው ሊያደርጉት የታሰበው ጉብኝት መሰማቱን ተከትሎ መፈታታቸው ተነግሯል፡፡

ይሁንና አሁንም ድረስ በቦታው ታስረው የሚገኙ ወጣቶች እንዳሉ የታወቀ ሲሆን፣ ከሰላሳ የማይበልጡት ታሳሪዎች እንዲፈቱ ጊዜያዊ የሕግ ኮሚቴው እየሰራ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

(አዲስ ማለዳ ጋዜጣ)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
3.0K viewsedited  10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 09:20:12 መፃጉዕ - የዐቢይ ጾም ዐራተኛ ሳምንት መዝሙር እና ዝማሬ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.2K views06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 21:32:39 #ምኩራብ
(የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት)

ምኩራብ ማለት ለአምልኮትና ለትምህርት ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጥ የአይሁድ ቤተ ጸሎት ነው። ጌታ በመዋዕለ ስብከቱ በእስራኤል ሀገር ብዙ ምኩራቦች ስለነበሩ እየገባ ወንጌልን አስተምሮባቸዋል። በዚህም “ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሀረ ቃለ ሃይማኖት” እንዲል ቅዱስ ያሬድ ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገብቶ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ። ከሚለው የቅዱስ ያሬድ ዜማ ሥያሜውን አግኝቷል።

በምኩራብ ጸሎትና ትምህርት ይፈጸምበታል። መሥዋዕት ግን አይከናወንም። መሥዋዕት ግን በታላቁ ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ብቻ ይፈጸም ነበር። በዚህ ሳምንት የሚነገረው ታሪክ ጌታ ቤተ መቅደሱን የገበያ ማዕከል አድርገው ሸቀጥ ዘርግተው በጉን ላሙን ርግቡን እየሸጡ አገኛቸው። በዚህ ተቆጥቶ በጉን ላሙን ርግቡን ከምኩራብ አስወጥቶ ሸቀጣቸውንና መደርደሪያቸውን እንዲሁም ወርቅና ብራቸውን በነፋስ በተነባቸው ይላል።

በዚህ ሁኔታ ከቤተ መቅደስ አስወጥቶ "ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች እናንተ ግን የሽፍቶችና የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት" በማለት ወቅሷቸዋል። “አሰስሉ ወአውፅኡ ዘንተ እምዝየ ወኢትረስዩ ቤተ አቡየ ቤተ ምሥያጥ” እንዲል ዮሐ. 2፥16፤ ማቴ. 21፥13። ይህን ተአምር በማሳየት ቤተ ጸሎት የተቀደሰ ከገበያ የተለየ መሆኑን አስተምሮበታል።

በሰንበተ ምኩራብ ጌታ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለዋጮችን ማስወጣቱ ወርቅና ብሩን በነፋስ መበተኑ ላሞችን በጎችን በጅራፍ መግረፉ ቤተ መቅደሱን ማንጻቱ ወዘተ ይነገራል።

(የዚህም በዓል ታሪክ ዝርዝር ሁኔታው ማቴዎስ 21፥12-13 ላይ ተጠቅሷል፡፡)

#የቅዳሴ_ምንባባት፦

ቆላስ. 2፥16-23
«እንግዲህ በመብል ወይ በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፣ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው፡፡ .......፡፡»

ያዕ. 2፥14-26
«ወንድሞቼ ሆይ፣ እምነት አለኝ የሚል፣ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን ......፡፡»

ሐዋ. 1ዐ፥1-9
«በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነው ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበር፡፡ እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ፡፡ ....፡፡"

#ምስባክ- መዝ 68፥9
እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡

(የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና
ነፍሴን በጾም አስመረርኋት፡፡)

#ወንጌል፡- ዮሐ 2፥12-25
«ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፣ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ፡፡ የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡ ወደ መቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፣ .....፡፡»

(ከመድብለ ታሪክ እና ግጻዌ የተወሰደ)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.1K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 08:29:11 ጊዮርጊስ ሆይ ከእኛ ወገን ነህን?

ወደ አድዋ ከዘመተው ሕዝብ አብዛኛው ባዶ እግሩን ነበር:: ዳዊት ጎልያድን ሊዋጋ ሲወጣ ከያዛት በትር በቀር አብዛኛው ሰው መሣሪያ አልታጠቀም:: አብዛኛው ዘማች ባዶ እጁን የዘመተው ሁለት ነገር አስቦ ነው:: መሣሪያ ባይኖረውም በውጊያው መካከል ከጠላት ጦር መሣሪያ ነጥቄ እዋጋለሁ አለዚያም ከሚወድቁት ላይ መሣሪያ አንሥቼ እዋጋለሁ ብሎ ነበር:: በውጊያው ታንክ በጎራዴ እስከመማረክ ያደረሳቸውም ይህ ቆራጥነታቸው ነበር::

ለመንፈሳዊ ጥንካሬያቸው ደግሞ ምሥጢሩ አብራ የዘመተችው የቤተ ክርስቲያን ጸሎት እና ንጉሡ በድንግል ማርያም ስም ምለው የሠጡት አደራ ነበር:: ለተገፉ የሚቆመው ሰማዕቱ ጊዮርጊስም በግፍ ባሕር አቁዋርጠው በደሃ ሕዝብ ላይ እሳት ከሚያዘንቡት ከአባቱ ዘመዶች ከሮማዊያን ጋር ሳይሆን እንደ ዳዊት በትር ይዘው በእግዚአብሔር ስም ከወጡት ባለማተቦች ጋር በምልጃው ተሰልፎ ዋለ::
በዚያች ዕለት አንድ ጣሊያናዊ ቅዱስ ጊዮርጊስን አግኝቶ ኢያሱ ቅዱስ ሚካኤልን እንደጠየቀው "ከእኛ ወገን ነህ ወይንስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? " ብሎ ቢጠይቀው ኖሮ "እኔ አሁን ከእግዚአብሔር ተልኬ መጥቻለሁ ይልቅስ የቆምክባት መሬት ኢትዮጵያ የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ" ባለው ነበር::

የዐድዋ ዘማቾች ጾመኞች ነበሩ:: እንግሊዝም ጣሊያንም ሰይጣን ይመስል ኢትዮጵያን የተዋጉአት በዐቢይ ጾም ነበር:: "ወድቀህ ብትሰግድልኝ መንገድና ፎቅ እሰራልሃለሁ" ያለንን ጣሊያን አባቶቻችን "ሒድ አንተ ጣሊያን የራስህን እንጂ የእኔን አታስብምና" ብለው ድል ነሡት::

ዘማቾቹ የምግብ እጥረት ቢኖርም እንኩዋን ጾሙን ትተን ካልበላን አላሉም:: ድንገት መሞቴ አይቀር ብበላ ይሻለኛል ሳይሉ ተዋግተው ድል ተቀዳጁ:: እኛ በሰላም ጊዜ የምንተወውን ጾም እነርሱ በጦርነት ላይም ሆነው አልተዉትም:: በዚያ ድል  ሀገሪቱ ለዐርባ ዓመት ከጦርነት ስታርፍ ለዕድሜ ዘመንዋ ደግሞ ከቅኝ ግዛት ዐረፈች::

ቅኝ ግዛት ብንገዛ ኖሮ ደሃ አንሆንም ነበር የሚል ሰው አይጠፋም:: ይህንን አሳብ የብዙ አፍሪካውያን ሀገራት ጆሮ አይስማው:: ዛሬ ነጻ ከወጡም በኁዋላ በባርነት ሕሊና የሚሰቃዩ ብዙ ናቸው::

ብዙ በፈረንሳይ የተገዙ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ዛሬም ድረስ በአደራ አስተዳደር በፈረንሳይ በእጅ አዙር ይተዳደራሉ:: በተባበሩት መንግሥታት ሳይቀር ቅኝ ገዢዎቻቸውን ተወካይ ሁነኝ ብለው የሚልኩ ሀገራት አሉ::
ዛሬም ድረስ በአንዳንድ አፍሪካ ሀገራት ጥቁሮች ሊስተናገዱ በተሰለፉበት ሱፐር ማርኬት አንድ ነጭ ከመጣ ሰልፍ ሳይይዝ ቅድሚያ ይስተናገዳል:: (በዓይኔ ያየሁት ነው)

ዛሬም ድረስ ብዙ አፍሪካዊያን ጥቁር በአስተሳሰብ ከነጭ በታች ነው ብለው ያምናሉ:: በዜኖ ፎቢያ የገዛ ወንድሞቻቸው አፍሪካውያንን የሚያሰቃዩ ደቡብ አፍሪካውያን ነጭ ሰፈር ግን ዝር አይሉም:: ሂሳብ ስታሰላ ሲያዩህ እንኩዋን አንተ ጥቁር ሆነህ እንዴት ያለ ካልኩሌተር መደመር ቻልክ የሚሉ ሰዎች ተፈጥረዋል::

በአውሮፓ በአሜሪካ ተወልደው አድገው ስኬታማ የሆኑት ጥቁሮች እንኩዋን የቤተሰብ ስማቸው ላይ አያቶቻቸውን በባርነት የገዛው ነጭ ገዥ ስም አብሮ ስለሚለጠፍ የዕድሜ ልክ የበታችነት ይሰማቸዋል:: አባቶቻችን ከብዙ ጣጣ አድነውናል አሁን ራሳችን የምንፈጥረውን ችግር ቢያዩ ለማመን የሚቸገሩ የሚሆኑትም ዘር ሳይለዩ አብረው የተዋደቁት ጀግኖች ናቸው:: ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬም ቤሩታዊት ኢትዮጵያን ከዘረኝነትና ጥላቻ ደራጎን ይታደጋት ዘንድ የምንማጸንበት ጊዜ ነው::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.8K views05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 14:30:57 ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የነፍስ ምግብ እንጅ

አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት ጾም የሥጋ ሥቃይ ሰማዕትነት ወይም መስቀል አይደለም ሥጋ ከነፍስ ጋር የሚተባበርበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከፍ ከፍ የሚልበት እንጂ። ስንጾም የመጾማችን ዕቅድ ሥጋችንን ለማንገላታት አይደለም ጠባዩን ለመግራት እንጂ። ይህ በመሆኑም አንድ የሚጾም ሰው መንፈሳዊ እንጂ ሥጋዊ ሰው አይሆንም ማለት ነው ።

ጾም መናኝ ነፍስ ስለሆነ በምናኔ ውስጥ ያለ ባልንጀራ ሥጋውን ይዞ ይጓዛል እንጂ ብቻውን አይጓዝም። ጾም ማለት የተራበ ሥጋ ማለት አይደለም የመነነ ሥጋ እንጂ። ጾም የሥጋ ረሀብ አይደለም የሥጋ ልዕልና እና ንጽህና እንጂ ለመብላት የሚናፍቅ የሚራብ ሰውነት ያለበት ሁኔታ ማለትም አይደለም፤ መብላት ዋጋውን የሚያጣበትና ሰውነት ለመብላት ካለው ፍላጎት ራሱን የሚያላቅቅበት ሁኔታ እንጂ።

ጾም ነፍስ ከፍ ብላ ሥጋን ከእርስዋ ጋር ከፍ የምታደርግበት ጊዜ ነው። ይህ ጊዜ ሥጋ ጓዙንና ሸክሙን የሚያራግፍበት ጊዜ ስለሆነ እግዚአብሔር ያለ ምንም እገዳ ለመንፈሳዊ ዘላለማዊነት ደስታ የሚሠራበት ጊዜ ይሆናል። ጾም ማለት ነፍስና ሥጋ በኀብረት መንፈሳዊ ተግባር ለማከናውን የሚጠቀሙበት ጊዜ ነው። በጾም ወቅት ነፍስና ሥጋ የነፍስን ሥራ ለመሥራት ይተባበራሉ። ይህም ማለት ለጸሎት ለተመስጦ ለክብርና ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሕይወትን ለመጋራት ይተባበራሉ ማለት ነው።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሳልሳዊ

የዐቢይ ጾም ዜማዎች

የዐቢይ ጾም ምዕዛል
ዘሰሉስ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
@abenet_tmhert ✥            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.4K views11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 12:00:26
ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን መቀሌ ገብተዋል

ፎቶዎች ፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት #በብፁዕ_አቡነ_ዮሐንስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ትግራይ ፣ መቐለ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
5.7K viewsedited  09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 09:55:04 የዐቢይ ጾም ዜማዎች

የዐቢይ ጾም ምዕዛል
ዘቀዳሚት

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
     •✥• @z_tewodros •✥•
@abenet_tmhert ✥            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.5K views06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 09:40:10
ቅዱስ ፓትርያርኩ በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ሽኝት ላይ ለመገኘት ወደ መቐለ አቀኑ!

የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ወደ መቐለ አቀኑ።

ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና ሊቃውንትን አስከትለው በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ወደ መቐለ ሲጓዙ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ሽኝት አድርገውላቸዋል።

ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
1.7K views06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 21:17:07
ዜና ዕረፍት
ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመቀሌ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
7.8K viewsedited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ