Get Mystery Box with random crypto!

Addis Ababa Education Bureau

የሰርጥ አድራሻ: @wwwaddisababaeducationbureau
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 108.10K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-06-16 22:07:02
በአረፋ በዓል ምክንያት በቀን 9/10/2016 ዓ.ም ሳይሰጥ የዋለው የሬሜዲያል ፈተና ሰኞ (በ10/10/2016 ዓ.ም) በፊዚክስ እና ማክሰኞ (በ11/10/2016 ዓ.ም) በኬሚስትሪ ፈተና እንደሚቀጥል እናሳውቃለን፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

(ሰኔ 9/2016 ዓ.ም)

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
9.6K viewsAbebe Chernet, 19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-16 09:43:35 መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
12.1K viewsAbebe Chernet, 06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-16 09:43:29
የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የ2015 ዓ.ም አመታዊ የትምህርት መጽሔትን አስገመገመ።

(ሰኔ 9/2016 ዓ.ም) መጽሔቱ ጉዳዩ በሚመለከታቸው የቢሮውና ክፍለ ከተማ ባለሙያዎች የተገመገመ ሲሆን የግምገማው ተሳታፊዎች በቡድን እና በጋራ በመሆን ከትምህርት ቤት ጀምሮ በወረዳና ክፍለ ከተማ ደረጃ ተጠናቅረው በአመታዊ መጽሄቱ የተካተቱ አጠቃላይ የትምህርት መረጃዎችን የማጥራትና የመገምገም ስራ ሰርተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ደስታ አብረሀም ቢሮው ከሚያከናውናቸው ቁልፍ ተግባራት መካከል አንዱ አመታዊ የትምህርት መጽሔት በማሳተም ለተገልጋዩ የሚፈለገውን መረጃ ተደራሽ በማድረግ ለመማር ማስተማር ስራው ውጤታማነት አስተዋጽኦ ማበርከት መሆኑን አስታውቀዋል።

ቡድን መሪው አክለውም በአመታዊ መጽሔቱ የተካተቱ የተማሪዎችና የመምህራን አጠቃላይ መረጃዎች፣የትምህርት ተቋማት መረጃዎች እንዲሁም አራቱ የትምህርት አመላካቾችን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎች በአግባቡ መካተታቸው በባለሙያዎቹ መገምገሙን ጠቁመው በቀጣይ በግምገማ ሂደቱ የተሰጡ የማስተካከያ ሀሳቦች ተካተው መጽሔቱን ወደ ማ ሳተም ሂደት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመርሀ ግብሩ የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ባለሙያው አቶ አለምነህ መላኩ በአመታዊ መጽሔቱ የተካተቱ መረጃዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።
11.4K viewsAbebe Chernet, 06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-12 16:38:34 መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
8.5K viewsAbebe Chernet, 13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-12 16:38:28
ከተማ አቀፉ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ።

(ሰኔ 5/2016 ዓ.ም) ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 182 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለሁለት ቀን ተ ሰጥቶ በሰላም መጠናቀቁን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ በከተማ አስተዳደሩ የ2016ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል ከአቅም በላይ በሆነ ችግር እና ከሀገር ውጭ በመሆናቸው ፈተናውን መውሰድ ካልቻሉ ጥቂት ተማሪዎች በስተቀር 99% የሚሆኑት መፈተናቸውን ጠቁመው ፈተናው በአማርኛ ስርአተ ትምህርት ለተማሩ ተማሪዎች በስድስት የትምህርት አይነት እንዲሁም ለአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ተማሪዎች ደግሞ በስምንት የትምህርት አይነቶች መሰጠቱን አስታውቀዋል።

አቶ ዲናኦል አክለውም በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች የተመደቡ የጸጥታ አካላትና የፈተና አስፈጻሚዎች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣታቸው ምስጋና አቅርበው ከሰኔ 12 እስከ 14/2016ዓ.ም የሚሰጠው ከተማ አቀፉ የ2016ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መጠናቀቃቸውንም አስገንዝበዋል።
8.3K viewsAbebe Chernet, 13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-12 14:41:39
"መውለዴና ትምህርቴን አያስቆመኝም ከዓላማዩም አያደናቅፈኝም" ተማሪ ሀና ደሳለኝ

(ሰኔ 5/2016ዓ.ም) ተማሪ ሀና ደሳለኝ በመሪ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በማታው መርሃ ግብር ከባለቤቷ ጋር በመሆን ትምህርቷን በመከታተል ላይ ስትሆን በዘንድሮው ዓመት የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል አንዷ ናት፡፡

ተማሪ ሀና 22 ዓመታ እንዲሁም ባለትዳር ስትሆን የመጀመሪውን ቀን ፈተና በሰላም ከተፈተነች በኋላ ትላንትና ማታ በድንገት ምጧ ይመጣና በወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ተወስዳ ወንድ ልጅ በሰላም ለመገላገል በቅታለች፡፡

የደከምኩበትንና የወደፊት ህልሜን የማሳከበትን ትምህርት ምንም እንኳን በችግር ውስጥ ብሆንም ሳልፈተን አላቋርጥም በማለት የምጥ ድካሟ ገና በአግባቡ ሳይሽር ፈተናዋን በፈተና ጣቢያ አሰተባባሪዎች እገዛ በመስራት ላይ ትገኛለች ፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
9.2K viewsAbebe Chernet, 11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-12 13:48:30
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የ2016 ዓ.ም 8ኛ ክፍል ከተማ ዓቀፍ ፈተና ሂደት ምልከታ ተደረገ፡፡

(ሰኔ 5/2016ዓ.ም) በዛሬው እለት ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የ2016 ዓ.ም 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በክፍለ ከተማው በ22 የመፈተኛ ጣቢያዎች 13 ሺ 7 መቶ 79 ተማሪዎች እየተሰጠ ይገኛል ይህንን አስመልክቶ የአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል፣ የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ተወካይና ሌሎች ኃላፊዎች በክፍለ ከተማው የእለቱን ፈተና በማስጀመር በመፈተኛ ጣቢያዎች ተዘዋውረው የፈተና ሂደቱ ሰላማዊ መሆኑን የተመለከቱ ሲሆን ተፈታኞችንም አበረታተዋል፡፡

ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና በዛሬው እለት ይጠናቀቃል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
8.0K viewsAbebe Chernet, 10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-12 11:03:04
የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለሁተኛ ቀን እየተሰጠ ይገኛል።

(ሰኔ 5/2016ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከቢሮው አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ እና ከክፍለከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከአቶ በለው ተስፋ ጋር በመሆን በክፍለ ከተማው በሚገኙ የተወሰኑ የፈተና ጣቢያዎች ተገኝተው የሁለተኛውን ቀን የፈተና ሂደት በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል።

አመራሮቹ ምልከታ ያደረጉት ሽመልስ ሀብቴ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ጠመንጃ ያዥ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ፈለገ ዮርዳኖስ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሲሆን በሶስቱም ጣቢያ ተማሪዎች ፈተናውን በአግባቡ በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ በምልከታቸው አረጋግጠዋል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 4,230 ተማሪዎች በ17 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናቸውን በመውሰድ ላይ መሆናቸውን የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በለው ተስፋ ገልጸው በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች በቂ የጸጥታ አካላትን ጨምሮ የፈተና አስፈጻሚዎች ተመድበው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
8.9K viewsAbebe Chernet, 08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-08 15:58:09 መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
7.5K viewsAbebe Chernet, 12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-08 15:57:59
በሚኒ ሚዲያ ክበባት ውስጥ ለሚሰሩ መምህራን እና ተማሪዎች የስፖርት ጋዜጠኝነት ስልጠና ተሰጠ።

(ቀን ሰኔ 1/2016) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከትምህርት ቢሮ ጋር በመተባባር በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በሚኒ ሚዲያ ክበባት ውስጥ ለሚሰሩ መምህራን እና ተማሪዎች በስፖርት ጋዜጠኝነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

በስልጠናው ክፈቻ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ ኮሚሸር ተስፋዬ ኦሜጋ ትምህርት ቤቶቸ የተተኪ ስፖርተኞች መፍለቂያ አንደመሆናቸው መጠን በትምህርት ተቋማት የሚከናወኑ ስፖርታዊ ሁነቶችን የሚዘግቡ ተማሪዎች አና መመህራንን አቅም ለመገንባት ታሰቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል።

ስልጠናውን የሰጡት የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዘዳንት ጋዜጠኛ ነዋይ ይመር ሲሆን ሰለ ሰፖርት ጋዜጠኝነት ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ መረጃ አሰባሰብ አና አቀራረብ ላይ ሰፊ ሰልጠና ሰጥተዋል።

ስልጠናውን የወሰዱ መምህራን እና ተማሪዎች ስልጠናው ሰለስፖርት ጋዜጠኝነት አና አዘጋገብ ያላቸውን እውቀት አንደጨመረላቸው እና በትምህርት ቤታቸው የሚከወኑ ስፖርታዊ ሁነቶችን ተከታትሎ ለመዘገብ የሚያሰችል እውቀት አንደጨበጡበት ተናግረዋል። እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው የጠየቁት መምህራን እና ተማሪዎች ለከተማዋ ብሎም ለሀገር የስፖርት አድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦም እንደሚወጡም ተናግረዋል።

የሰፖርት ጋዜጠኝነት ስልጠናን ለወሰዱ መምህራነ እና ተማሪዎች በፀረ አበረታች ቅመሞች ዙሪያ አጭር ገለፃ ከኢትዮጵያ ፀረ አበረታች በለስልጣን በመጡ ባለሙያዎችም ተደርጎላቸዋል።
7.6K viewsAbebe Chernet, 12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ