Get Mystery Box with random crypto!

ከተማ አቀፉ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ። (ሰኔ 5/ | Addis Ababa Education Bureau

ከተማ አቀፉ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ።

(ሰኔ 5/2016 ዓ.ም) ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 182 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለሁለት ቀን ተ ሰጥቶ በሰላም መጠናቀቁን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ በከተማ አስተዳደሩ የ2016ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል ከአቅም በላይ በሆነ ችግር እና ከሀገር ውጭ በመሆናቸው ፈተናውን መውሰድ ካልቻሉ ጥቂት ተማሪዎች በስተቀር 99% የሚሆኑት መፈተናቸውን ጠቁመው ፈተናው በአማርኛ ስርአተ ትምህርት ለተማሩ ተማሪዎች በስድስት የትምህርት አይነት እንዲሁም ለአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ተማሪዎች ደግሞ በስምንት የትምህርት አይነቶች መሰጠቱን አስታውቀዋል።

አቶ ዲናኦል አክለውም በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች የተመደቡ የጸጥታ አካላትና የፈተና አስፈጻሚዎች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣታቸው ምስጋና አቅርበው ከሰኔ 12 እስከ 14/2016ዓ.ም የሚሰጠው ከተማ አቀፉ የ2016ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መጠናቀቃቸውንም አስገንዝበዋል።