Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxtewahedo
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 47.96K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ።
‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ››
ት.ኢሳ 58÷3
https://youtu.be/csxxAMGtC4I
ለመቀላቀል
http://t.me/ortodoxtewahedo

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-10 08:38:30 #የሊባኖሷ_ሙሽራ

በመጀመርያ በክንፍ ላይ ስሎ ለመላእክት ሲገልጣት የጠባቂነት መዓረግን መስጠቱ ነበርና ከማኅፀን ጀምሮ እንዲጠብቃት አደራ በተሰጠው መልአክ በኩል እንደተናገረው በዘመድ በኩል ቢሆንም ቅሉ ለምትወለደዋ ሕፃን ዘመዶቿ የሰማይ መላእክት  ነበሩና በእነርሱ ተከባ ወደ ምትወልድበት ስፍራ እንዲሄዱ ተነገራቸው ።

እራሷ ከዓለም አይደለችምና በመወለዷ በቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች ዓለማዊ ተድላ ደስታን እንዳያደርጉ በመንፈሳዊያን ዘመዶቾ በመላእክት ታጅባ ከቤት ወጣች ። ከቤቱ ወጥቶ ሕገ እግዚአብሔርን ስቶ የነበረ አዳምን የሚፈልግ ጌታ እናቱ ናትና ከቤት ወጥታ ቀድሞ አባቶቿ ነብያት እርሷን በራዕይ ወደ ተመለከቱበት ታላቅ  ስፍ ወደ ሊባኖስ ተራራ ተጓዘች ። በሊባኖስ ተራራ ጉያ ስር በእንበሶች ጉድጓድ እንደምትወለድ ትንቢት የተነገረላት የሊባኖስ ሙሽራ እርሷ ናትና ።

ከጉሩማኑ አናብስት ከነዳዊት ከነሰሎሞን ፤ ከተላላቁ ተራሮች ከነ አብርሃም ፣ ይስሐቅ ፣ ያዕቆብ አብራክ የተገኘችው እመቤታችን ሰው በማይኖርበት ስፍራ ልትወለድ ተወሰነ። በዚያም ሳሉ ክብሯ ከአድባራት ሁሉ በላይ የሆነ ከቀደሙትም ከኋለኞቹም በላይ ስሟ የገነነ ፣ ከፀሐይ ይልቅ የምትደምቅ እመቤታችን በግንቦት አንድ ቀን ተወለደች ።

እሷ የሁሉ ፍጥረት ናት እንጅ የሐናና የኢያቄብ ብቻ ባለመሆኗ በአንድ ሰው ቤት ውስጥ እንዳትወለድ መንፈስ ቅዱስ ከለከለ ።

     ( ሕይወተ ማርያም ገጽ 85-87 ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ )

አማላጅነቷ የእናትነት ፍቅሯ ይጠብቀን ።

http://t.me/ortodoxtewahedo
6.2K viewsedited  05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 21:04:26
(፩)ልደታ ለማርያም እናቴ
#ድንግል ሆይ
የነብያት-ትንቢታቸው
የሐዋርያት-ሞገሳቸው
የሰማዕታት-አክሊላቸው
የመላእክት-እህታቸው
የምንዱባን-እናታቸው
የነዳያን - ምግባቸው
የደካሞች-ምርኩዛቸው
የደናግል-መመኪያቸው
አንቺ ነሽ
እመቤቴ ሆይ ልደትሽ ልደታችን ነው እንኳን አደረሳችሁ
ልደታ ለማርያም
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ለዕውራን ብርሃናቸው ለተጠሙትም የወይን ምንጫቸው ሆይ፤ ወደኔ ፈጥነሽ ነይ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ኦ ወዮ ትተይኝ ይሆን? ኦ ወዮ ትንቂኝ ይሆን? እንግዲያ የልቤን ኅዘን ለማን እነግረው ይሆን፡፡

መልክአ ኤዶም

የቃል ኪዳኗ እመቤት ምልጃዋ አይለየን ።

http://t.me/ortodoxtewahedo
6.6K views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 21:03:27
5.2K views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 21:03:12 #እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" #ልደታ ለማርያም ድንግል "*+

#ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ:
ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ::

" ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን:
ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) "

=>የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኩዋ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን::

+ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል::

+እመቤታችን ከአዳም ስሕተት በሁዋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: (ኢሳ. 1:9)

+ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ቀን: በሊባኖስ ተራራ ከ2,022 ዓመታት በፊት ተወልዳለች::

"ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ" (መኃልይ. 4:8)

=>ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች ልጅ የላችሁም በሚል ይናቁ ነበር::

+ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ::
እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም::

+የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች::

+ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን 2ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ::

+እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::

+በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::

+እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች::
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . .
ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም)

+"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ."
"ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9)

+እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች::

=>የእመቤታችን የዘር ሐረግ:-
*አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ=
*በእናቷ:-
-ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና::
*በአባቷ በኩል:-
-ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል::

+ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,026 ዓመታት በፊት ተወልዳለች::

=>የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን::

=>ግንቦት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (ልደታ)
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቴክታና በጥሪቃ
4.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

http://t.me/ortodoxtewahedo
6.3K viewsedited  18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-07 11:40:43 #ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

✞ ሰኞ-
ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

✞ ማክሰኞ-
ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

✞ ረቡዕ-
አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

✞ ሐሙስ-
አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

✞ አርብ-
ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

✞ ቅዳሜ-
ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

✞ እሁድ-
ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

http://t.me/ortodoxtewahedo
7.9K views08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-05 04:21:47 ትንሳኤ
                         
Size 6.7MB
Length 19:00

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

http://t.meortodoxtewahedo
8.5K viewsedited  01:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-04 19:38:38 ሁሉም ተፈጸመ//ተፈጸመ ኩሉ
                                              
Size:- 31.5MB
Length:-1:30:32
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

http://t.meortodoxtewahedo
8.3K viewsedited  16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 20:43:15
በፀሎት ሁላችንም ተግተን ወደ ፈጣሪያችን እንፀልይ በውጭም በሀገር ውስጥም ያላቹ አባቶች :ምዕመናን :አጠቃላይ የቤተክርስቲያን ልጆች የቤተክርስቲያን አንድነት የሚሰብክ ነገር እንድታስተላልፍ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ምክንያቱም አንዳንድ መልዕክቶች ይበልጥ ቤተክርስቲያን የሚከፋፍሉ አሉና ጥሩን ነገር ብቻ እንድታስተላልፍ ጥሪ እናቀርባለን ::

ብፁዕ አብነ አብርሃም

የቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላይ ስራ አስኪያጅ


@ortodoxtewahedo
1.5K viewsedited  17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 17:44:48
http://t.me/ortodoxtewahedo
1.9K views14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 17:44:42 በትግራይ በተከናወነው የሕገ ወጥ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለሐምሌ 25/2015 ዓ.ም ምልዐተ ጉባኤ ጠራ።

1. በክልል ትግራይ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙት አህጉረ ስብከት ጋር ተቋርጦ የነበረውን መዋቅራዊ ግንኙነት ችግር በውይይት እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪና ልዑካኑን በአካል ልኮ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ተብለው በሚጠሩበት በማዕከላዊ ትግራይ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 15 እና 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከናወነ ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት መፈጸሙን በመገናኛ ብዙኃን ለማወቅ ችለናል፡፡ በመሆኑም በዚህ የዶግማና የቀኖና ጥሰት ተግባር የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በእጅጉ አዝኗል፡፡

2. በመሆኑም የተከሰተው የዶግማ፣ የቀኖና እና አስተዳደራዊ ጥሰት አስመልክቶ ተወያይቶ ተገቢውን ለመወሰን ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ ተላልፏል፡፡

3. የስብሰባው ቀን ሊራዘም የቻለው በውጭው ክፍለ ዓለማት ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት መገኘት ስላለባቸው የጉዞ ቀኑ እንዳያጥር እና በሀገር ውስጥ የሚገኙትም ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት ለአገልግሎት ወደ አህጉረ ስብከታቸው የሄዱ በመሆኑ ለመመለሻ የሚያስፈልገውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡

4. በየደረጃ ያሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሥራ ኃላፊዎች እና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ምዕመናን ከአሁን ቀደም በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በደረሰው ፈተና በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን በመቆም ላሳያችሁት ጽናት እያመሰገንን አሁንም በደረሰው ፈተና እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን ጸንታችሁ እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

5. በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ በትግዕስት እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡

6. ምንም እንኳን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ ጥሪው በደብዳቤ የተላለፈ ቢሆንም የመልእክቱ በፍጥነት መድረስ ካለው ስጋት አንጻር የችግሩን ተደጋጋሚነትና አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ክፍለ ዓለማት የምትገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ተጠቃላችሁ ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ እንድትመጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡


7. ሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን ሚዲያዎችና ሌሎች መገናኛ ብዙኃን ይህን መልዕክት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን መልእክቱን በማስተላለፍ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እንጠይቃለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም.

ምንጭ: ኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

http://t.me/ortodoxtewahedo
1.5K viewsedited  14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ