Get Mystery Box with random crypto!

✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

የቴሌግራም ቻናል አርማ itsmetsiyearsemalj — ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘
የቴሌግራም ቻናል አርማ itsmetsiyearsemalj — ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘
የሰርጥ አድራሻ: @itsmetsiyearsemalj
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.69K
የሰርጥ መግለጫ

በቤቴ ሲታደሙ ከጥበብ ማዕድ ይቋደሳሉ
በኔና በሌሎች የተፃፉ
🌹ግጥሞች🌸
🌹ወጎች 🌸
🌹ልቦለዶች 🌸
ሌሎችም...
━━━━━━━━ ✦
ለማንኛውም አስተያየት
@Tsiyon_awit and
@itsmetsita
ይጠቀሙ።
Join us
@itsmetsiyearsemalj

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-26 19:46:00 ሀንፃውን ቀና ብሎ አየው ፤ በፍቅር፤ በፈገግታ ። እና ከቁጥጥር ውጭ ሊባል በሚችል ሁኔታ በልቡ ያሰበው ነገር ከአፉ ሲወጣ ድምፅ ሆኖ ተሰማው « ሃይ ፣ ታዲያስ !» አለ። ባለፉት ዓመታት ይህን ሺህ ጊዜ ደጋግሞ ብሎታል ። እዚህ ቤት ፤ ታዲያስ !»ይልና ከፍቶ ይገባል ። ያኔ ያያታል ፤እሸራ መወጠሪያ አትሮኑስዋ አጠገብ ቆማ ፤ ቀለም ተፈናጥቆባት ። እጅዋ ላይ እክንዷ ድረስ ፤ አንዳንዴም ፊቷ ሳይቀር በቀለም ተላብሶ ያያታል አንዳንዴ ስራዋ ላይ እያለች ከሆነ ሲገባም አትሰማ ። እንግዲህ አንደኛው ቁልፍ እሱ ዘንድ ነበር የሚቀመጠው። ስለዚህ ለመግባት ማንኳኳት የለበትም። ይህን እያሰበ በቀስታ ደረጃውን ወጣ ። በጣም ደክሞት ነበር። ሆኖም ለማረፍ አልከጀለም ። ሊያየው የፈለገው ነገር እየገፋ እያንሳፈፈ ሽቅብ ነዳው ።እዎ ማረፍ የለበትም፤፣መድረስ እለበት ። ከደረሰ በኋላ ሄዶ ፤ ከእስዋ ጋር … ከእሷ አጠገብ የእሷ ከሆኑ እቃዎች ፤ ከእሷ ንብረቶች አጠገብ መቀመጥ ብቻ ነው እሚፈልገው ። ያ ፍላጐት ነው ሽቅብ የሚነዳው፡፡ በስተውጭ ሁሉ ነገር እንደነበረ ነበር ። የቀለሙ ሽታ ሳይቀር ሸተተው ። ውሀ ሲቀዳ ይሰማዋል ። የሕፃናት ድምፅ ፤ የድመት ጩኸት ... ሁሉ ነገር ይሰማዋል። ያው ነው፣የተለወጠ ነገር አልነበረም ። ቆይቶ የጣልያንኛ ዘፈን ተሰማው…. ሬዲዮኑን አልዘጋችውም ማለት ነው? አለ በሃሳቡ ። ቁልፉን ከኪሱ እወጣና በሩን ለመክፈት ተዘጋጀ ። ይኸኔ እውነት ብቅ አለች ። ናንሲ የለችም! አላገኛትም አለ በሃሳቡ ። ናንሲ ሞታለች አለ በሃሳቡ ። አዎ ሞታለች ። ይህን መርዶ ከሰማበት ጊዜ ጀምሮ ድምፁን ከፍ አድርጐ «ሞታሉች» ለማለት ደጋግሞ ሞክሮ ነበር ። ግን አልቻለም። ይህን የሞከረው ደግሞ በከንቱ አልነበረም ። ማይክል ሐቁን እየሸሹ ደግ ደጉን በማሰብ በተስፋ በውሸት ተስፋ ለመኖር እንደሚሞክሩ አንዳንድ ሰዎች መሆን አይፈልግም ። ስለዚህ እውነቱን ለመጋፈጥ ደጋግሞ ሞከረ ፤ ሞታለች ብሎ ለራሱ ሊነግር። ራሱን ሊያፅናና ግን አልቻለም ። ይህን ደካማነቱን ብታውቅበት እንዴት ትንቀው !ይኸ ሁሉ በሃሳቡ ነበር ። ግን ይረሳል ። ሞቷን ይረሳል ፤ ላይቀርለት ። ለቅጽበትም ያህል ቢሆን እውነቱ አካል ያወጣ ያህል ብቅ እያለ በጥፊ ማጠናገሩን ላይተው ። ልክ በዚህ ቅጽበት በሩን ሊከፍት ሲሰናዳ እንዳጮለው ሁሉ በየሰዓቱ ማጮሉን ላይተወው እውነቱን ይሸሻል።

ሰረገላውን ቁልፍ ካዞረና ከከፈተው በኋላ ቆም ብሎ ጠበቀ ምናልባት አንድ ሰው ከበስተውስጥ ይከፍትልኝ ይሆናል ብሎ ተስፋ ያደረገ ይመስል ጠበቀ ። ግን ማንም አልከፈተለትም ማንም ብቅ አላለም ። በሩን ገፋ አደረገው ። ወደ ውስጥ ተመለከተ ። እንደገና ከእውነቱ ራቀ። እና የተመሰጠች ፤ በስራዋ የተዋጠች ናንሲን ሊያይ ፈለገ ግን ያጋጠመው ሌላ ነበር፡፡ አንድ የሚያስደነግጥ ድምፅ ከትንፋሹ ጋር አስወጣ ። አስደንጋጭ የድንጋጤ ድምፅ።
«ኦ! አምላኬ. ! የታለ ? ወዴት ?» ሁሉም ነገር ባዶ ነበር። ሁሉም ነገር ። ጠረጴዛ የለ ፤ወንበር፤ ቀለም የለ ብሩሽ ፤ የሸራ መወጠሪያ አትሮኑስ የለ ቀለም ማደባለቂያ ፤ ቤት ውስጥ የበቀሉ አበቦች የሉ ፤ ምንጣፍ...አንድም ነገር አልቀረም ። ቤቱ ባዶ ...ወና ሆኗል ።
«የክርስቶስ ያለህ ! ናንሲ !» አለ አጠገቡ ያለች ይመስል፤ የት አደረስሽው ? ሊላት የፈለገ ይመስል ። የሌሎቹን ክፍሎች በር እየከፈተ ተራወጠ ፣ እንባው በፊቱ ላይ እንደ ጐርፍ እየወረደ ። ጨዉ ፊቱን ሲያቃጥሊው ተሰማው፡፡ አይኑን ሲቆጠቁጠው ተሰማው ። እንዲህ ሆኖ ነው ማልቀሱን እንኳ የተገነዘበው እንጂ እንባውስ ዝም ብሎ ነበር የወረደው፤ ፊቱን ያጠበው ።

የትም የት ምንም እቃ አልነበረም ። ባለበት ደንዝዞ ቀረ። ሃሳቡ ሁሉ ሙልጭ ብሎ ከአእምሮው ወጣ። ድንገት በሩን በርግዶ ወጣና ወደታች መውረድ ጀመረ።ሁለቱን ደረጃ ባንዴ እየተራመዶ ምድር ቤት የሚገኘውን የሕንፃውን ዋና አስተዳዳሪ ቢሮ ሲያይ ወደዚያው ሄደ። በቡጢ ይነርተው ጀመር ። ደቃቃው አስተዳዳሪ ደንግጦ በሩን ቀስ ብሎ ከፈተው ፤ በሩን የሚመታው ሰው አደገኛ መስሎ ከታየው መልሶ ለመዝጋት በመጠንቀቅ ። ግን ወዲያው አወቀው ። ማይክልን አወቀው ። ስለዚህም በሩን በደንብ ከፈተው ። ሆኖም የገመተው ማይክል ሳይሆን ቀረ። አንገቱን በሸሚዙ ሲያንቀው ደነገጠ ። ማይክል ሰውየውን አንቆ ይዞ እያርገፈገፈ
«የታለ ! . . እቃዋ ሁሉ የታለ !? እቃዋ ሁሉ የታለ ካውሰኪ ? የት ወሰድከው? የት ከተትከው?» አለ።
«የምን . . የምን እቃ? . .ኦ ! አምላኬ ! ገባኝ ። የለም ፤ የለም እኔ አይደለሁም ። አንዲት ስንጥር ነገር አልነካሁም ። ከአስራ አምስት ቀን በፊት . . አካባቢ... መጥተው ወሰዱት ። እና ደግሞ እንዲህ ብለው … » ሰውየው መንቀጥቀጥ ጀምሮ ነበር።
‹‹ማናቸው ? እነማን ናቸው እነሱ ?»
«አላወኩም። . . ብቻ ጠሩኝና ነገሩኝ ። ሚስ ማክአሊስትር...» ይህን እያለ ማይክልን ቀና ብሎ አየው ። ፊቱ በሐዘን ተውጦአል፡፡ አይኖቹ በእንባ ዳምነዋል ። ስለዚህም ሊናገረው የነበረውን ቃል ዋጠው።
«ያው ታውቃለህ አይደል ! በኋላ ነገሩኝ ። ከጥቂት ቀናት በኋላ እቃውን እናወጣለን አሉኝ ። እንዳሉትም ሁለት ነርሶች መጥተው አንዳንድ እቃዎችን ወሰዱ ። በማግስቱ የጉድዊል ጭነት መኪና መጣ። ሌላውን እቃ ሙልጭ አድርጐ ወሰደው። እኔ ...እኔ ምንም እቃ አልነካሁም ። አላደርገውም ። ያችን የመሰለች ልጅ…»
«ሰዎች ያልካቸው እነማን እንደሆኑ አታውቅም? ማለት ከየት እንደመጡ።
«ምንም አላወቅኩም ። ነጭ ልብስ ለብሰዋል ። ለዚህ ነው ነርስ የመሰሉኝ ። እነሱ የልብስ ሻንጣዋንና ስእሎቿን ብቻ ነው የወሰዱት ። ሌላው እቃ ወደ ጉድዊል ነው የተጫነው ። እኔ… እኔ አንድም ነገር አልነካሁም ። በፍጹም እኔስ ነገ ... ››

ግን ማይክል አይሰማውም ነበር ። አስተዳዳሪውን ትቶ ወደውጭ መውጣት ቀጠለ ። ሰውየውም እየውና በሀዘኔታ አንገቱን ነቀነቀ ። እና ድንገት
«ስማኝ ልጄ….» ሲል ተጣራ ። ማይክል መለስ ብሎ አየው ።
« ስለሆነው ሁሉ እዝናለሁ ፤በርታ » አለው።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
1.1K viewsTsiyon Beyene, 16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 19:46:00 #ቃል
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አስር (10)


የአንቡላንሱን በር ቦግ አድርገው ከፈቱና ወሳንሳውን በጥንቃቄ ተሸክመው ወደ ሆቴሉ ገቡ ። የሆቴሉ ማኔጀር እውጭ ደረጃውን ወርዶ ነበር የተቀበላቸው ። ወደተዘጋጀላቸው ክፍል እየመራ ወሰዳቸው ። በሆቴሉ ውስጥ የሚገኝ የአንድ ቪላ ያህል ምቾትና ስፋት ያለው ክፍልና ዙሪያ ገባው በጠቅላላ ለእነሱ ሲባል ተለቆ ነበር ። ሁለት ወይም ሶስት ቀን ያህል እዚህ ሊቆዩ አስበዋል ። ይህ የሆነው ደግሞ በሁለት ምክንያት ነው። አንደኛ ማሪዮን ሂልያርድ ቦስተን ከተማ ውስጥ አንድ ስብሰባ ላይ መገኘት ነበረባትና ወደኒውዮርክ ለመመለስ አትችልም ነበር። ሁለተኛ ማይክል ወደ እናቱ መኖሪያ ቤት ከመሔዱ በፊት ከሆስፒታል ወጥቶ ለትወሰነ ጊዜ ሆቴል ውስጥ ለመቆየት እንደሚፈልግ ተናግሮ ነበር። እርግጥ ነው የማሪዮን ስብሰባ ቢኖርም ማይክል ግን ወደ ቤት ሄዶ እዚያው ኒውዮርክ ሊጠብቃት እንደሚችል ታውቃለች ። ግን ደግሞ ሆቴል መቆየት እፈልጋለሁ ካለ ይህን ፍላጎቱን ማሟላት አለባት። ምንም እንኳ ፍላጐቱ የልጅ ቢመስልም ማሪዮን የጠየቀውን ሁሉ ልታሟላለት በልቧ ዝግጁ ነበረችና ይሁን ብላ ተቀበለችው ።

የአንቡላንስ ሠራትኞች ከናወሳንሳው አውርደው እንደሚሰበር ዕቃ ተጠንቅቀው አልጋው … ሲያስተኙት «ማሚ ፤ በክርስቶስ ይዤሻለሁ ፤ይህን ያህል ጥንቃቄ አያስፈልገኝም ። ሀኪሞቹን ሰምትሻቸው የለም? ደህና ነው፤ምንም አልሆነም ፤ ነበርኮ ያሉሽ » አለ ማይክል ።
«ቢሆንም ፤ ቢሆንም ችላ ማለት ደግ አይደለም» እለች ማሪዮን።
«ችላ ማለት ? » እለ ማይክል ። ይህን ብሎ ክፍሉን እየቃኘ ትንሽ አጉረመረመ ። ማሪዮን ዝም ብላ ለእምቡላንሱ ሠራተኞች ጉርሻ ትሰጥ ነበር ።

ክፍሉ በተለያዩ የእበባ ዓይነቶች ተሞልቷል ። አልጋው አጠገብ በሚገኝ ጠረጴዛ ላይም አንድ ችልቅ ቅርጫት በፍራፍሬ ተሞልቶ ተቀምጧል ። ዝግጅቱ ማይክልን እምብዛም አላስደነቀውሙም ። ምክንያቱም ሆቴሉ የማሪዮን ሂልያርድ ንብረት ነው ባሊፈው ዓሙት እንደ ገዛችው ያስታውሳል
« አሁን ዘና በላ የኔ መኳንንት ስለምንም ነገር ማሰብ መጨንቅ አያሻህም ። በነገራችን ላይ የሚበላ ነገር ምን ይምጣልህ ? » አለች ነገራት።
«ምን ዓይነት የምግብ አመራረጥ ነው የኔ ሸጋ ? » አለች። እውነቱን ለመናገር ግን ምርጫው ተስማሚ ይሁን አይሁን አላወቀችም ። ምክንያቱም አልሰማችውም። እሱ ምግብ ሲዘረዝር የሷ ሀሳብ እቀጠሮዋ ላይ ስለነበር ሰዓቷን በማየት ላይ ነበረች። ስለዚህም «እንግዲህ እንደፍላጎትህ አድርግ ። ማለት የሚያስፈልግሀን ነገር ራስህ ማዘዝ ትችላለህ ። በበኩሌ ፤ ጆርጅ እንደመጣ መሄድ አለብኝ ወደ ስብሰባው›› አለች ። ይህን እንዳለች ደወሉ ተንጫረረ ። በሩ ሲከፈት ጆረጀ ኮሎዌ ነበር ።
« እሺ ፤ አሁንስ እንዴት ነው ? ተሻልህ ፤ ማይክል ?»
«ደህና ነኝ ። ብቻ ሁለት ላምንት ሙሉ እሆስፒታል ውስጥ ያላንዳች ስራ ተጋድሜ ሰንብቼ ስለወጣሁ በሁኔታው እፍረት ቢጤ እየተሰማኝ ነው»

ማይክ የልቡን በልቡ ይዞ በአፉ ይህን ይበል እንጂ በገፅታው ላይ ግን የተሰበረ ስሜት ጉልህ ሆኖ ይታይ ነበር ። እናቱም ያንን ገፅታውን እይታለች ። ግን ድካም ነው ፤ ድንጋጤ ነው ፤ ሌላ ምንም አይደለም ብላ ራሷን አስተማምና ተፅናንታለች፡፡ ስለናንሲ ያስባል ፤ የናንሲን «ሞት» በመስማቱ ነው ይህ ሁኔታ የሚታይበት ለማለት አልደፈረችም ። ከዚህ ሀሳብ አጥብቃ ትሸሻለች ። ማይክል ሆስፒታል ውስጥ በቆየበት ጊዜም ስለአደጋው ፈፅሞ እያነሱም ነበር ፤እናትና ልጅ። የሚወያዪት ስለ ድርጅቱ እድገት፣ በተለይም በሳንፍራንሲስኮ ስለሚሰራው የሕክምና ማእከል ኮንትራት እና ስለሚገኘው ትርፍ ነበር ።
« ዛሬ ጧት ከኒውዮርክ ከመነሳቴ በፊት አዲሱን ቢሮህን ተዘዋውሬ አየሁት ። መቼም ድንቅ ቢሮ ነው» አለ ጆርጅ በግርጌ በኩል አልጋው ላይ እየተቀመጠ።
«ገና ሲጀመር ታውቆኛል።ድንቅ ቢሮ ነው ፤ አይደል ? » አለ ማይክል ።ልብሷን ቀይራ የምትመለሰውን እናቱን እየተመለከተ «ማሚ ጥሩ ነገር የማቀድና የመምረጥ ችሎታ ስላላት ቢያምር አያስደንቅም »
«እሱ ላይ ልክ ብለሀል» አለና ጆርጅ ሞቅ ባለ ፈገግታ ማሪዮንን ተመለከታት ። ይህን ጊዜ ማሪዮን በእጅዋ ባዶውን አየር ቁልቁል ወደኋላ እየገፋች «የአፍ ሹም ሽረቱን ተዉት ። ይልቅ ሳይረፍድ አልቀረምና ቶሎ ተነሳ እንሂድ ፤ ጆርጅ » አለች « በነገራችን ላይ ጆርጅ ለመሆኑ አስፈላጊ የሆኑ መዘክሮችን አጠናቀህ ይዘሀል? »
« በሚገባ »
‹‹እንግዲያስ እንሂድ» ብላ ወደ አልጋው ሂዳ ግንባሩን እየሳመችው «ማይክል የኔ ቆንጆ ምንም ማሰብ አያስፈልግም በደንብ እረፍ። ነገ ቀጥ ብለህ መስራት ልትጀምር ነው ። በነግራችን ላይ ምሳህን እንዳትረሳ» አለችው ።
«አልረሳም። ደህና ዋሉ መልካም ስብሰባ። መልካም እድል››
« እድል አልክኝ ?» አለች ሳቅ ብላ « እድልና ስራ በምንም በምን ግንኙነት የላቸውም›› ይህን ስትል ማይክልና ጀርጅ ሳቁ ። ማሪዮንና ጆርጅ ተሰናብተውት ወጡ ማይክልን ።

ልክ ሲወጡለት ከተጋደመበት ተነስቶ አልጋው ላይ ተቀመጠና ማሰብ ጀመረ። የሚያደርገውን ነገር በሚገባ አጥንቶታል፡። ሁለት ሳምንት ሙሉ ምን እንደሚያደርግ አውጠንጥኖ ጨርሷል አሁን ጊዜው ደረሰ ። ባቀደው መሠረት መፈጸም ብቻ ነው ያለበት፡፡ በእቅዱ መሠረት አንደኛው ተፈፅሟል ። ቦስተን ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ መቆየት እፈልጋለሁ የሚለውን ሀሳብ ያቀረበው ለዚህ ነበር።ይህን ምክንያት ቢያቅርብላት ኋላ ይደርሳል ወይም እኔ እንዲፈጸም አደርጋለሁ ትለው ነበር ። ስለዚህ የቅብጥብጥ ልጅ አጉል ፍላጐት የመሰለ ምክንያት ሰጣት ። የፈለገውን በደስታ አደረገችለት ። በዚያ ላይ ብቻውን የሚሆንበት ጊዜ ያስፈልገው ነበር። በስብሰባው ላይ እንድትገኝ ገፋፋት። ጆርጅና አንድ ሌላ ሰው ሊገኙ ይችሉ ነበር ። ግን ለስራው አንቺ ትሻያለሽ ምንም ቢሆን እያለ አሳመናት ።

ድንገት ቢመለሱ በማለት ከወጡ በኋላ ለግማሽ ሰዓት ያህል ከአልጋው ላይ አልወረደም ። ባለበት ቁጭ እለ። ያን ያህል ጊዜ ካለፈ በኋላ ርግጠኛ ሆነ። ከዚያም ልብሱን ይለባብስ ጀመር። ሰውነቱ ያሰበውን ያክል አልጠነከረም። ልብሱ ራሱ አዲስ ሆነበት ፤ ቆሞ መሄድም እንግዳ ነገር።

ወጣ ድካም ሲሰማው እየተቀመጠ ሲያልፍለት እየተነሳ ጉዞ እየቀጠለ። ከሆቴሉ ወጥቶ ታክሲ መጠበቅ ጀመረ ታክሲውን አገኘ። የሚሄድበትን አድራሻ ነገረውና ወደዚያው ተጓዘ፡፡ ታክሲው ራሱ ዳተኛ የሆነ መሰለው። በጣም ቸኮለ። ለረጂም ጊዜ የተለያት ሲሆን ዛሬ ግን በስጋ የቀጠራትን ያህል ሆኖ ተሰማው። እዚያ እስኪደርስ በጣም ቸኮለ። ቆማ የምትጠብቀው እሷም ቀጠሮ እንዳላቸው የምታውቅ እንደሚመጣ የምታውቅ ይመስል ጊዜም መኪናም ተንቆራሰሱበት ።

እቦታው ላይ ሲደርስ በደስታ ፈገግ እለ ፣ ለብቻው ። ክዚያም ሾፌሩን እያዬ ፈገግ አለ ። ጠቀም ያለ ገንዘብ ሰጠው። ጉርሻው ከክፍያው የላቀ ነበር ። እና ዞሮም ሳያየው ፤ ጠብቀኝ ትመልሰኛለህም ሳይለው ጉዞውን ቀጠለ ። ማንም ሰው እንዲጠብቀው አልፈለገም ምክንያቱም የፈለገውን ያህል ጊዜ እዚያ ሊቆይ ይፈልጋል ። እንዲያውም ሀሳቡን አውጥቶ አውርዶ ጨርሶታል። ኪራዩን ሊከፍል ፤ በናፈቀ ጊዜ ወይም በከፋው ጊዜ እዚያ ቤት እየመጣ ሊቀመጥ ፤የተወሰነ ሰዓት ሊያሳልፍ እንደሚችል አውጠንጥኖ በልቡ ተስማምቷል ። ምናለው ? ከኒውዮርክ ቦስተን የአንድ ሰዓት ጉዞ ነው ። ያች አፓርታማ ለሱ ልዪ ነገር ናት፤የናንሲ መኖሪያ ። የናንሲና የማይክል መኖሪያ። የነሱ መኖሪያ ነበረች…ናት ።
1.0K viewsTsiyon Beyene, 16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 19:35:07 እንዲህ እያለ በቀላሉ የረጅም ጊዜ ትውውቅ ያላቸው እስኪመስላት ራሱን አላመዳት ። ባንዴ ። ይህን ሁሉ የሚላት ለመቀራረብ ብቻም አልነበረም። በረጂም ጉዞ ላይ ስለነበረች ለጥቂት ጊዜ ያላንዳች እንቅስቃሴና ሀሳብ ስታርፍ ሰውነቷ በቀላሉ ዘና እንደሚል ስላወቀም ነበር ። ነርሶቹም ደስ አላቸው ። እነሱም ከጉዞ ጣመናቸው ማረፍ ያስፈልጋቸው ነበርና ካንቡላንስ ነጂው ጋር እያወጉ ይዝናኑ ነበር። ወደናንሲ አይናቸውን ጣል ሲያደርጉ ዶክተር ግሬግሰን ናንሲን ሲያጫውታት ስላዩ ስውየው ደስ ብሏቸዋል ።
«እኔ ? እኔ እንኳ ያደኩት ኒው ሃምፕሻዬር ነው ። እናትም አባትም አልነበረኝምና እዚያው ባለ የእጓለማውታን ማሳደጊደያ ውስጥ አደኩ ። ወደ ቦተስን የመጣሁት አስራ ስምንት አመት ከሞላኝ በኋላ ነው»
«ይኸማ ልብ የሚሰቅል ታሪክ ነው። ወይስ ማሳደጊያ ቤቱ በቻርልስ ልቦለዶች ውስጥ እንዳሉት ያለ በጭካኔ የተሞላ ነበር» አለ ፒተር ። ናንሲ በፒተር አጠያየቅ ፤ በተለይም ሁሉን ነገር ቀላል አድርጐ በመቀበል ችሎታው ተገረመች የዲክንስ የእጓለማውታ ማሳደጊያዎችን ማሰቡ አሳቃት ።
«ዲክንስ ውስጥ ? በፍጹም ! ያሳደጉኝ መነኩሲቶች በጣም ዶጋጐች ነበሩ ። ደስ የሚሉ። በዚህ የተነሳ እንዲያውም እኔም እራሴ ለመመንኮስ ሀሳብ አድሮብኝ ነበር ። እንደነሱ ለመሆን አለች ናንሲ ።
«አረ የስላሴ ያለህ ! ጆሮ አይሰማው የለ ! ስሚ የኔ እህት» አለ ፒተር ፤ናንሲ ሳቀች ።
«የኔ እህት ልክ ህክምናውን እንደጨረስሽ በቀጥታ ወደ ፊልሙ ከተማ ወደ ሆሊውድ!... ገባሽ?... ነገር ግን... ይህን አይሆንም ብለሽ ቁንጅናሽን ይዘሽ ገዳም ብትገቢ አያድርገውና !... ገዳም ብትገቢ እኔ ምን የማደርግ . . . እኔ ሌላ ምንም አላደርግም ። ወደወደብ ሄጄ፤ አንዱ ቋጥኝ ላይ ወጥቼ፤ ከዚያ ላይ ተወርውሬ ስምጥ ። በቃ ። የለም የለም ፤ እንዲሀ በቀላሉ አንላቀቅም ። እንዲያውም ህክምናዬን ከጨረስኩ በኋላ ቁንጅናዬን አንድ ገዳም ወስጄ ላልደብቅ ለፒተር ግሬግሰን ቃል እገባለሁ ስትይ ማይልኝ፡፡ ይህ ቀልድ ነው ። ሆኖም እንደዘበትም ቢሆን ቃል መገባት ደግ አይደለም ። ይህን ታውቃለች ። ትወቅ እንጂ ቃል ለመግባት ደግሞ አይከብዳትም ። ምክንያቱም እካሏ ይመለሰን እንጂ ወደየት እንደምትሔድ ታውቃለች ። ማይክል አለላት ። በዚያ ላይ ሞግዚቷና እናቷ እንደነበሩት እማሆይ ሜሪ የመሆን ፍላጐቷም አስቀድሞ ጠፍቶ ነበር ። ይህ ሁሉም ሆኖ ትንሽ ጫወታ አይጎዳም በማለት ፣ «እንዲያ ከሆነ እሺ›› አለች
«ምንድነው እሺ ? ቃል ገባሁ ማለችሽ ነው? ቃል በቃል ልትናገሪ ይገባል። ቃል ገብቻለሁ በይ »
«እሺም ቃል ኪዳን ነው። ስለዚህም ቃል ገግብቻለሁ
«ቃል ገብቻለሁ ! ብሎ ነገር ምን ለመሆን ነው ቃል የገባሽው ?»
«መነኩሴ ላለመሆን››
«እፉፉዎዬ ! አሁን ቀለል እለኝ » አለ ፒትር ።

እስካሁን ሰውነቷ ዘና እንደሚል ገባው ። ስለዚሀም ነርሶቹ እንዲወጡ በጥቅሻ ጠራቸው ። በወሬ ብዙ ማድከሙም ደግ እይደለም። ይበቃታል ፤ ሲል እያሰበ ። ሁለቱ ነርሶች ሲመጡ
«ከጌደኞችሽ ጋር ለምን አላስተዋወቅሽኝም ? » አላት ።
«ደግ » አለችና ናንሲ ፤ «ባለሰቀዝቃዛ እጅዋ ሊሊ ትባላለች ። ባለሞቃት እጅዋ ደግሞ ግሬችን ትባላለች» አራቱም በዚህ ንግግር ሳቁ ።
«አመሰግናለሁ ናንሲ » ሊሊ የናንሲን እጅ በማበረታታት መንገድ ጨበጥ አደረገች ። ናንሲ በድንገት ደስ አላት ። እኒህ ሶስት ጓደኞቿ ምንም እንኳ እንግዳ ቢሆኑ የልብን የሚነግሯቸው የሚተማመኑባቸው ጓደኞቿ እንደሆኑ ተገነዘበች ። እነሱ እያሉ ምንም ችግር ይኖራል የሚል ሥጋት አልነበረባትምና ስለአስታማሚና ስለመሳሰሉት ያላትን ሀሳብ አራገፈች ። ይህን አራግፋ ፤ድና ስትወጣ ለማይክል ምን መስላ እንደምትታየው ታሰላስል ጀመር። ፒትር ግሬግሰንን አሰበችው ። የሚቀበሉት ፤ የሚወዱት ሰው ሆኖ አግኝታው ነበርና በህክምናው ተማመነችበት ። ውብ መልክ እንደሚሰጣት ገባት ምክንያቱም ለሰው ፍቅር አለው ። ስለዚህም ይጠነቀቃል ፤ ይጨነቃል ።"

«ወደ ሳንፍራንሲሰኮ እንኳን ደህና መጣሽ ብጥሌ!›› አለ ፒተር ግሬግሰን ። የሊሊ ሚጢጢ እጅ ናንሲን ለቅቋት የፒትር ሰፊ እጅ ያዛት ። ማረፊያቸው እስኪደርሱ ድረስ ማለትም በመንገድ ላይ አምቡላንሰ ውስጥ እጅዋ በእጁ ውስጥ ነበር ። በሚያስገርም አኳኋን ስሜቷን ሁሉ ቀየረው ። እናም የመጣችው ወደማታውቀው ሰፍራ ሳይሆን ወደ ቤቷ፤ ወደትወለደችበት ሀገር እንደሆነ አድርጋ ገመተች......

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
1.3K viewsTsiyon Beyene, 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 19:35:07 #ቃል
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ዘጠኝ (9)

የአውሮፕላኑ መስገሪያ ጎማ ከሆዱ ውስጥ ጉጉ ግርር ብሎ ሲወጣ ለናንሲ በደንብ ተሰማት ። እጅዋን ስትዘረጋ ከቦስተን ወደ ሳንፍራንሲስኮ ባደረገችው በዚህ ጉዞ ላይ ያዝ እያደረጉ መቶ ጊዜ ያህል ካፅናኗት ሁለት የተለያዩ እጆች አንዱ ያዝ አደረጋት ። ከሁለቱ ነርሶች አንደኛዋ ነበረች እጅዋን ያዝ አድርጋ ያጽናናቻት ። የነርሷ እጅ እጅዋን ሲቀበል መንፈሷ ተረጋጋ። የትኛዋ ነርስ እንደሆነች ስታውቅ ደስ አላት ። በአያያዛቸው መለየት ጀምራ ነበር ። የአንደኛዋ ነርስ እጅ ቀጭን ሲሆን ልስልስ ያለ ነበር ። የዚች ነርስ እጅ ቀዝቃዛ ቢሆንም አጨባባጧ ግን ጠንካራ በመሆኑ ይህችኛዋ ሴት ስትጨብጣት ፍርሃት ፤ ፍርሃት የሚላት ይተዋትና ልቧ መድፈር ይጀምራል። የሁለተኛዋ ነርስ እጅ ወፍራምና ቡትቡት ያለ ሲሆን ገና ያዝ ስታደርጋት ክብካቤና ፍቅር ያልተለያት እንደሆነ ይሰማታል ። የዚች ነርስ ሞቃት እጅ ፍቅርን ይገልጽላታል ። ያዝ አድርጋ እትከሻዋ አካባቢ እጅዋ መባቀያ ላይ መታ መታ ስታደርጋት የፍቅሯን ጥልቀት ይገልጽላታል ፤ ለናንሲ ። ህመሙ ጠንከር ሲልባት ሁለት ጊዜ መርፌ የወጋቻት ይህችው ነርስ ነበረች ።

ድምጿም የሚያረጋጋ ሀይል አለው። ልስልስ ያለ ነው። ቀጭን እጅ ያላት ሴትዮ ስትናገር ትንሽ ያዝ ያደርጋታል ። ናንሲ ሁለቱንም ሴቶች እየወደደቻቸው ስትሄድ ተሰማት ።

«አሁን ደርሰናል የኔመቤት ። ማረፊያው እየታየኝ ነው» አለች ጠንከር ያለ አያያዝ ያላት ነርስ እጅዋን እንደያዘች ።

ነገሩ እንደተባለው ነበር ። የቀራቸው ሃያ ደቂቃ ያህል ሲሆን፤ ፒተር ግሬግሰን ሰዓቱን በማየት አረጋገጠ ። ፒተር ግሬግሰን በቀጠሮው መሠረት በጥቁሩ አውቶሞቢል ወደ አውሮፕላን ማረፊያው ሲነጉድ ይህን ተገንዝቧል። አምቡላንሱ እዚያው ይጠብቀዋል ። ፒተር ሕክምናውን ከሚያደርግላት ልጅና ከነርሶቹ ጋር በአምቡላንሱ ሊመለስ ወስኗል።ምክንያቱም የልጅቷ ሁኔታና የሚያደርግላት ሕክምና አጓጉቶታል ። አዲስ ፊት መስራት ! አዲስ ውበት መፍጠር ! ይህ 'ቀላል ነገር አይደለም ። በዚያ ላይ ምን አይነት ፊት እንደሚፈጥር ያውቃል ። ፒተር በዚህ ሁኔታ ሀሳቡን ሊቀጥል አልፈለገም ። ስለዚሀም ስለናንሲ ማንነት ማሰብ ቀጠለ ። አራት መቶ ሺህ ዶላር እጅግ በጣም ብዙ ገንዘብ ነው። ልጅቷ ይህን የሚከፍልላት ሰው ማግኘቷ መታደል ነው። ለማሪዮን ሂልያርድ ምኗ ትሆን! ማሪዮን በጣም የምትወዳት ወይም የምታስብላት ሰው መሆን አለባት-። ያለዚያ ይህን ያህል ገንዘብ አታወጣም ነበር። ይህን ያህል አትጨነቅላትም ነበር ።። አራት መቶ ሺህ ዶላር ! ከዚህ ውስጥ ሦስት መቶ ሺህ ዶላር የሱ የአገልግሎት ዋጋ ነው ። ወጭውንና የመሳሰለውን ችሎ ። መቶው ሺህ ዶላር ግን የተከፈለው ለታካሚዋ ነው ። ሕክምናዋን እስክትጨርስ ለመኖር የሚያስፈልጋትን ነገር ለማሟላት የምትጠቀምበት ። በዚህ ገንዘብ የፈለገችውን ሁሉ ለማሟላት ወደ ኋላ አልልም አለ ፒተር ግሬግሰን በሀሳቡ ።

እንደገናም አመት ከመንፈቅ ሙሉ በአይኑ ላይ ውል ሲለው የኖረ ፊት ትዝ አለው ። ያ ፊት ናንሲን አዲስ ሴት ያደርጋታል ። ለአስራ ስምንት ወራት ያረገዘውን ፊት ናንሲ አድርጎ ይወልደዋል ። የናንሲና የእሱን የወደፊት ግንኙነት ሲያስበወ ሲቃ ያዘው። ናንሲ የሙያውን ረቂቅነት የሚያይባት ብቻ አትሆንም ። የእሷና የሱ ግንኙነት ከሐኪምና ታካሚ ግንኙነት ያልፋል ። ከመዋደድም ያልፋል ። ደፋርና በራሷ የምትተማመን ሴት የምትሆንበትን መንገድ ሁሉ ያደርጋል ። ደግሞም ትሆናለች። ይህን ነገር ሲያስብ የሆነ ያህል ሆኖ ተሰማው። በደስታ ሰክረ። ሙያውን ይወደዋል ። አንድ ነገር ሰርቶ ውጤቱ ሲያምር ሁልጊዜም ይደሰታል ። ስለዚህም ምንም እንኳ ነገሩ ግራ ቢመስል ፤ገና ካሁኑ ከናንሲ ጋር ፍቅር ያዘው። ገና ወደፊት ከሚፈጥራት ናንሲ ጋር፤ ካላያት ናንሲ ጋር።

ሰዓቱን እንደገና አየት አደረገ ጊዜው እየታቀረበ ነው። ቤንዚን መስጫውን ተጫነው። መኪናው ተፈተለከ ። የቀጠሮው ሰዓት በመድረሱ ብቻ ሳይሆን ፒተር ግሬግሰን በፍጥነት መንዳት በጣም ከሚያስደስታቸው ሰዎች አንዱ ነው። ይህም ብቻ አይደለም። ፒተር የግል አውሮፕላንም አለው። ያን አውሮፕላን አስነስቶ በጣም ከፍ ብሎ ማብረር ወይም አውሮፕላኑን በፍጥነት ሽቅብ ነድቶ አቅጣጫ ለውጦ ዘቅዝቆ ቁልቁል ማብረር በጣም ያስደስተዋል። ጉራ ወይም ሌላ ነገር አይደለም፣ፒተር አስቸጋሪ ነው የሚባለውን ነገር ሁሉ ማድረግ ይወዳል። አደገኛ ነው ሲሉት ተራራ መውጣት... የመሳሰሉትን ሁሉ በሚገባ እስኪካናቸው ድረስ ያደርጋቸዋል። ፒተር አናቱ ድረስ ያልወጣበት የአውሮፓ ተራራ አይገኝም። ይህ ሁሉ ታዲያ እላይ እንደተገለፀው ካስቸጋሪው ጋር መጋፈጥን በመውደዱ ነው። በዚህ ጠባዩ ነው ይህን የቆዳና የአካል ቅርፅ መፍጠር ቀዶ ሕክምና ሙያው ያደረገው። አስቸጋሪና ብዙ ጥንቃቄ ያሻዋል። ያ ስለሆነ እንዲያውም ሰዎች አንዳንድ ጊዜ እግዜር ልትሆን ትሻለህ? በሚል ተረብ ገረፍ ያዶርጉታል። እሱ ግን ይህ እንዳልሆነ ያውቃል። ይህን አይነት ሕክምና እንዲያደርግ እሱን የሚገፋፋው እልህ ነው ፤አይቻልም ያሉትን ነገር እንዲቻል የማድረግ እልህ። እና አድርጎ ማሳየት ። ፒተር ይኸው ነው። እስከዛሬ ድረስ ያከማቸውን ሰዎች አስታወሰ ። ተሳክቶለታል ። ፒተር ሁልጊዜም ይሳካለታል ። የፈለጋት ሴት እምቢ አትለውም ። ተራሮች ተረትተውለታል። ሰማይን ተጫውቶበታል። ምን ጊዜም አሁንም ይሳካለታል። ናንሲና እሱ ተረዳድተው ሕክምናው ባሰበው መንገድ ይፈጸማል። ዛሬ የአርባ ሰባት አመት እድሜ ያለው ሰው ነው። በዚህ ባሳለፈው እድሜ ሁሉ ተሸንፎ አያውቅም ። ዛሬም አይሸነፍም

«ሄሎ ናንሲ ፤እንኳን ደህና መጣሽ ጉዞው እንዴት ነበር! አለ ፒተር ግሬግሰን ካውሮፕላኑ እንደወረደች ። ሁለቱን ነርሶች እንዳያቸው ተስማሚ እንደሆኑ ገምቷል ። ለነሱ በጥቅሻ ሰላምታ ሰጠ። ፤ድምጹን ስትሰማ ደስ አላት ።
«ጥሩ ነበር፤ ዶክተር ግሬግሰን » አለች ናንሲ ።ድምጺ እንደደከማት በ.ያመለክትም ስልቸታ ግን አልነበረበትም ።
«ዶክተሬ ነህ-»
«ነኝ። ግን ካሁን ጀምሮ አብረን መሥራታችን እይደለም? ስለዚህ ሚስ ማክኦሊስተር ፤ዶክተር ግሬግሰን ከመባባል ፤ እኔም ናንሲ ብል አንችም ፒተር ብትይ ይበልጥ የሚያቀራርበን ይመስለኛል» አለ ፒተር ። አቀራረቡ ደስ አላት ።
«ልትቀበለኝ ነው እዚህ ድረስ የመጣኸው » አለች።
«አንቺ ብትሆኝ እዚህ ድረስ መጥተሽ አትቀበይኝም ነበር ማለት ነው?» ሲል ጠየቃት ።
«እቀበልህ ነበር እንጂ» አለች ይህን ስትል በሚገርም ሀኔታ ነገሩ እውነት መሰላት። ይህን ያህል ከሰው ጋር ባጭር ጊዜ መግባባት መቻሏ ገረማት «አመሰግናለሁ» አለች ።
«እኔ የመጣሁት ለራሴ ደስ ስለሚለኝ ነበር ። ሆኖም አንችንም ደስ ሲልሽ አየሁ ። ይህ ደሞ ደስታዬን እጥፍ አደረገው እንኳን መጣሁ አሰኘኝ» አለ ።« በማከታተልም «ናንሲ» አለ
«አቤት »
«ናንሲ ከዚህ በፊት ሳንፍራንሲስኮ መጥተሽ ታውቂያለሽ?»
«አላውቅም»
‹‹ደስ እምትል ከተማ ናት ። ፍሬስኮን እንደምትወጃት እተማመናለሁ። ምርጥ የሆነ አፓርታማ እንፈልግልሻለን ። አለቀ ። ብዙ ሰዎች ሳንፍራሲስኮን ከረገጡ በኋላ የተወለዱበትን ፤ የኖሩብትን ቦታ ይረሳሉ። እዚሁ ቅልጥ ብለው ነው የሚቀሩት ። ለምሳሌ የእኔን ነገር ማንሳት እንችላለን ። የዛሬ አሥራ እምስት አመት አካባቢ ከሺካጐ መጣሁ። መጣሁ ቀረሁ። ዛሬ የፈለገው ነገር ቢመጣ ከዚች ከተማ ንቅንቅ አልልም ። አንች የት ነው የነበርሽው?››
‹‹ቦስተን »
1.2K viewsTsiyon Beyene, 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:08:52 እግሯ እየተብረከረከ ቀስ ብላ ወደ አልጋው ሄዶች :: ጎንበከ ብላ ፊቱን ዳበስ ፤ ዳበስ አደረገችው ። «ሄይ ማም» አለ አይኑን ገለጥ አድርጐ ማይክ በዚች ዓለም ላይ ለማሪዮን የእነዚያን ቃላት ያህል ውብ ነገር አልነበረም ። የደስታ እንባ አፈሰሰች ፤እየሳቀች ።
«ማይክ በጣም እወድሀለሁ » አለች ።
«እኔም እወድሻለሁ እናት አለም» አላት ። ይህን ሲያይ በሕክምና ዓለም የኖረውና ብዙ ክፉና ደግ ብዙ ሞት ሽረት ያየው ዶክተር ዊክፊልድ ሳይቀር አይኑን እንባ ቆጠቆጠው። ይህን ለጋ ለግላጋ ወጣትና ይህችን ያህል ጊዜ እንቅልፍ ሳያሸንፋት ፤ እህል ሳያምራት የልጀዋን መታመም ስታብሰለስል ከጎኑ ሳትለየው ለመቆየት የቻለች እናት ሲያይ ሐኪሙ እንኳ አላስችል ብሎት እንባው መጣበት ። ስለዚህም ቀሳ ብሎ ትቷቸው ወጣ ። መውጣቱን ሁለቱም አላዩም ።

እቅፍ አድርጋ ይዛው ብዙ ሰዓት ቆየች ። እሱም ጸጉሯን በእጁ እያረሰ «በጣም አትሸበሪ ፤ ማሚ። አሁን ሁሉም ነገር ተስተካክሏል።የክርስቶስ ያለህ ! እንዴት አድርጎ ነው የራበኝ እባካችሁ» አለ ድምፁን ስትሰማ፤ ነፍሱ ተመልሳ «ራበኝ» ሲል ዳነልኝ በቃ የኔ ነው ፣ማንም አይወስድብኝም ፤ ማንም አይቀማኝም ስትል አሰበች ። ደስ አላት ፤ ሳቀች ። «ዊክን እንጠይቀውና ይሁን ካለ በዓለም ላይ ካሉት ቁርሶች ሁሉ የላቀውንና የጣፈጠውን ቁርስ እናቀርብልሃለን » አለች ።
«ዊክ ቢፈልግ ገደል ይግባ ። እኔ በራብ መሞቴ ነው› አለ ማይክል ።
«ማይክል ምናልክ ! » አለች ። ግን ቁጣ ሊሆንላት አልቻለም አትችልምም ። ልትወደው ብቻ ነው እምትችለው ። ቁጣዋ ያሳደረበትን ስሜት ለማየት ፊቱን ስታጤን ልውጥ ሲል ታያት። ቅር ተሰኝቶ አይደለም አልነበረም ። ድንገት አንድ ነገር ያስታወሰ መሆኑ በግልፅ ታይቷታል። ለምን ሆስፒታል ውስጥ እንዳለ የገባው መሆኑ ገብቷታል። የመጀመሪያው አነሳሱ ሌላ ነበር ። በልጅነቱ ቶንሲል አሞት ሰንብቶ ከእንቅልፉ ሲነቃ እንደተሻለው ሲገነዘብ የሚሰማው አይነት ስሜት ነበር ። አይስ ከሬምና እናቱን ብቻ የፈለገው ለዚያ ነበር ። አሁን ግን ፊቱ ላይ ብዙ ነገር አነበበች ። ተነስቶ ሊቀመጥ ሞከረ። ምን እንደሚፈልግ ግራ ገባው እንጂ የሆነ ነገር ሊጠይቅ ፈልጐ ነበር፡፡ ከፊቱ አንድ ነገር ለመረዳት የፈለገ ይመስላል ። ትኩር ብሎ አያት። እስዋም አየችው። እጁን ጭብጥ አድርጋ ይዛ
«የኔ ውድ በቃ ፣፤ ቻለው» አለችው።
«እማዬ . . . ያንለት ሌለት . . ሌሎቹስ! አሁን ትዝ አለኝ» አለ ።
«ቤን ወደ ቦስተን ተወስዷል። ተገጫጭቷል ። ቢሆንም ደህና ነው። ካንተ ይሻላል» አለችው። ይህን ብላ በረጂሙ ተነፈሰች ፤ በጣም ማዘኗን ለመግለፅ ። እና እጁን ጥብቅ አድርጋ ያዘችው ። ቀጥሎ የሚመጣውን ጥያቄ አስቀድማ አውቃዋለች ።መልሱን አስቀድማ ስላዘጋጀች አልተጨነቀችም ።
«ናንሲስ ? » አለ ።«ናንሲ የት አለች ማሚ !?»
ፊታ መልሱን ነገረው ።እንባው ዱብ ዱብ አለ። አጠገቡ ተቀምጣ እጁን ቀስ ብላ እያሻሸች ፤
«በጣም ተጎድታ ነበር ስለዚህ አልተቻለም ። ሕይወቷን ማትረፍ አልተቻለም» አለች ። ቀጥላም… «ሀኪሞች ያልሞከሩት አልነበረም ። አልቻሉም » አለችና ንግግሯን አቋረጠች ። «ዛሬ ጠዋት አረፈች » አለችው ቀጥላ ።
«አየሻት? ሄደሽ አየሻት ?» አለ ፊቷን ትኩር ብሎ ስትዋሽ ውሸቷን ለማንበብ የሚሞክር መስሎ ።
«ትናንት ሌሊት. . . ለጥቂት ጊዜ... አጠገቧ ሄጄ ቁጭ ብዬ ነበር ። »
«ምንው አምላኬ ! ምነው … ናንሲ!ወይኔ ! የኔ ናንሲ» አለ ። ትራሱ ሳይ ተደፍቶ እንደልጅ አለቀሰ ። ማሪዮን ከጀርባው ላይ እጅዋን ጣል አድርጋ ተወችው ። ስሟን እየደጋገመ እያነሳ አለቀሰ ። እስኪደክመውና ድምጹ ተዘግቶ ማልቀስ እስኪ ሳነው። ቀና ብሎ እናቱን አያት ። በዚህ ጊዜም ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው አዲስ ስሜት እፊቱ ላይ አየች ። የናንሲን ስም እየደጋገመ ሲጠራና ሲያለቅስላት ልክ ከውስጡ አንድ ነገር የጠፋ ያህል ነበር ያን ነገር አየችው ። ከውስጡ አንድ ነገር ጐድሎ የእሱ የአካል ክፍል ተነጥሎ እንደሞተ ታያት....

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
1.4K viewsTsiyon Beyene, 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:08:43 #ቃል
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ስምንት (8)


ናንሲን አምቡላንስ ላይ ሲያሳፍሯት ፤ ማረዮን ሂልያርድ ጥቁር የሱፍ ቀሚስና መደረቢያውን ለብሳ ሆስፒታሉ ሕንፃ በር ላይ ቆማ ትመለከት ነበር። ጊዜው ከጥዋቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ሲሆን ፤ ቀኑ ከናንሲ ጋር ከላይ የተገለጸውን ስምምነት ባደረጉ ማግሥት ነው ። ከናንሲ ጋር እዚያ ስምምነት ከደረሱ በኋላ ማሪዮን ዳግም ወደ ናንሲ ክፍል ዞር አላለችም ። ዳግም አላነጋገረቻትም ። ብቻ እስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ጉዳዩን ለዶክተር ሮበርት ዊክፊልድ አነሳችለትና በፍጥነት ከዶክተር ፒተር ግሬግሰን ጋር እንዲዋዋል ጠየቀችው ። ዶክተር ዊክፊልድ ይህን ሲሰማ በደስታ ሰክሮ ማሪዮንን ጉንጩን ሳማት ። ግሬግሰንን አንጋገረው ። ግሬግሰንም ተሰማማ በቃ ። ፒተር ግሬግሰን ናንሲን ሳይውል ሳያድር ወደ ሳንፍራንሲስኮ እንድትልክለት ስለጠየቀ ማሪዮን ደስ ተሰኘች ። ሁለት ነርሶች ቀጥራ በአንደኛ ማዕረግ የጄት ጉዞ ነርሶቹ ይዘዋት ወደ ሳንፍራንሲስኮ እንዲንዙ ሁሉን ነገር ባንድ ቀን አዘጋጀች። ማሪዮን ስለወጪው ቅር አልተሰኘችም።

« መቼም የታደለች ልጅ ናት ማሪዮን » አለ ዶክተር ዊክፊልድ ማሪዮንን በአድናቆት እየተመለከተ ።
«ይመስለኛል » አለች ማሪዮን ። «አንድ ነገር . . . ይህን ጉዳይ ማይክል እንዲሰማ አልፈልግም ። ሰምተኸኛል ዊክ ?»
«አልገባኝም » አለ ዶክተር ዊክፊልድ ግራ እየተጋባ ።
«ለምን አይሰማም ? ለሚወዳት ልጅ እናቱ ያደረገችላትን ችሮታ የመስማት መብቱን መነፈግ አለበት እንዴ ?››
‹‹የለም የለም የለም ፣ መስማት የስበትም ። እንዲያውም ከሰማ ውሉን እሰርዛለሁ… የማሳከሙን ውል»
« አልገባኝም. . .»
«ይህ ጉዳይ ሚስጥር ሆኖ እንዲጠበቅ እፈልጋለሁ ። ከሁለታችን ማለፍ የለበትም። ማለትም ካራታችን ፣ ካንተ ፣ ከኔ ከሷና ከግሬግሰን ። ማይክል ይህን ነገር መስማት አይኖርበትም ። አያስፈልገውም ። ነፍሱን እንዳወቀ ፈጽሞ ስለናንሲ ማንሳት የለብህም እንዲረበሽ አልፈልግም ። »

በሀሳቧ፣ ቢሻለውና ነፍሱ መለስ ብትል ነው ያውም…አለች ሌሊቱን ሙሉ አጠገቡ ቁጭ ብላ ነው ያደረችው ። ከናንሲ ጋር ከተደራደረች በኋላ ነፍሷ በጣም ስለተደሰተች እንቅልፏም አልመጣባት ። ድካምም አልተሰማት ። ያደረገችው ነገር ትክክል እንደሆነ አምና ነበርና ። ደጋግማ አስባበት ፤ አምናበት ነበር። ለሁለቱም ሕይወታቸው የደስታ እንዲሆን ነው ያደረግሁት ። እሱም ነፃ ወጣ ። እሷም ትድናለች ። እያለች ደጋግማ ስታስብ አደረች ። « እንግዲህ አንዲት ቃል ላንናገር ተስማምተናል ። አይደለም እንዴ ሮበርት ? » አለች ማሪዮን ። ሮበርት ብላ ጠርታው አታውቅም ነበር ።
«መነገር የለበትም ካልሽ እኔ የምናገርበት ምንም ምክን ያት የለም »
«ደግ እንደሱ ነው»

የአምቡላንሱ በር ተዘጋ ፤ ሁለቱ ነርሶችና ናንሲ ከገቡ በኋላ ። ናንሲ ሕክምናዋን በምታካሂድበት ጊዜ ነርሶቹ ቋሚ አስታማሚ ሆነው ስድስት ወር ሙሉ አብረዋት ሊቆዩ ተቀጥረዋል ። ከስድስት ወር በኋላ ግን ነርሶቹ እንደማያስፈልጉ ግሬግሰን ገልፆላቸዋል ። ከስድስት ወር ፤ ጨመርም ቢል እስከ ሰባት ወር ድረስ… የፊት አጥንቷን ሽፋሽፍቶቿንና ሽፋሎቿን እንዲሁም አፍንጫዋን ማስተካከልና መትከል ስላለበት አይኖቿ በፋሻ መታሰራቸው አይቀርም ። በዚያ ጊዜ ሰው ያስፈልጋታል" ነርሶች ማለት ነው ። ግሬግሰን እንዳለዉ ፊቷ እንደገና እንደ አዲስ ነው የሚታነጸው ። ስለዚህ ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ወጭው ብዙ ነው። ለምሳሌ አንድ የአእምሮ ሀኪምም ያስፈልጋታል ። በየጊዜው ሊያነጋግራትና በአዲሱ ሰብእናዋ እንድታምን ሊያደርጋት ይገባል ። ለዚያም መክፈል ያለ ነው ። ግሬግሰን ይህን ሲያስረዳ…
«አዲስ ሰው መሆኗ አይቀርም ። ምክንያቱም ያጣችውን ነገር ሁሉ ፤ማለት በመንፈስ ያጣችውን… ለመመለስ አዳጋች ነው። አዲስ ሰብእናዋን እንድትቀበል ማድረግ ይኖርብናል » ብሏ.ል ። ይህ ደሞ ማሪዮንን በጣም ነበር ያስደሰታት ። ምክንያቱም ይህ ከሆነ ናንሲ ከማይክል ጋር ያላትን ግንኙነት ልትቀጥል አትደፍርም ማለት ነው ብላ ስለገመተች ነበር ። ማን ያውቃል ? ድንገት ሊገናኙ ይችላሉ ። አውሮፕላን ማረፈያ ላይ ሰው ይገናኛል ። ወይም ሆቴል ውስጥ ወይም ድንገት እመንገድ ላይ . . . ድንገት ። ይህ ደግሞ ለማሪዮን ደግ ነገር ሆኖ ሊታያት አይችልም ።

ግሬግሰን በጣም ግልፅና ሥራውን አጠናቆ የሚያውቅ ባለሙያ ሲሆን እድሜውም በአርባና በሃምሳ ዓመት መካከል ነው። ዝናው በመላው ዓለም ታውቋል ። እንዲህ ያለ የፕላስቲክ ሰርጀሪ ( የአካል መልሶ መተካት ቀዶ ህክምና ) ሙያ ያለው ሰው ነበር ናንሲን ያጋጠማት ። የታደለች ልጅ ነች አለች ማሪዮን በሀሳቧ ። በውሉ ላይ የናንሲ ምቾት የሚጠበቅበት ሁኔታ ሁሉ አብሮ ገብቷል ። የሚመች መኖሪያ መከራየት አለባት ። ከላይ ያልናቸውን ወጪዎች ጨምሮ ጠቅላላ የተከፈለው አራት መቶ ሺ ዶላር ነበር ። ውሉ ሲታተም ማሪዮን አላንገራገረችም ። ገንዘቧን ለምታ ስቀምጥበት ባንክ ደውላ የተባለውን ያህል ገንዘብ ወደሚፈልገው ባንክ በስሙ እንዲዛወርለት የምታደርግ መሆኑን ወዲያውኑ ገለፀች ።
«ነገ ጠዋት በሶስት ሰእት ሄደህ ብትጠይቅ ገንዘቡን በስ ምህ ገቢ ሆኖ ታገኘዋለህ» አለች ማሪዮን ፒተር ግሬግሰን አልተጠራጠረም። ማሪዮን ሂልያርድ ማን እንደሆነች አሳምሮ ያውቃል ። ለመሆኑ ማሪዮንን የማያውቅ ማን አለ!

«ለምን አትመጪና ቁርስ አትቀምሽም ማሪዮን» አለ ዶክተር ዊክፊልድ ከሀሳቧ እየቀሰቀሳት ። ግራ ተጋብቷል ። ጆርጅ ኮሎዌይን ነበር የተማመነው ። እሱም እስከ ነገ ጠዋት ከኒውዮርክ መውጣት እንደማይችል ገልጾለታል ። ዶክተር ዊክፊልድ አላወቀም እንጂ እንዳይመጣ የከለከለችው ማሪዮን ነበረች።
«የምፈጽመው ጉዳይ ስላለ ብቻየን መሆን እፈልጋለሁ ። ስለዚህ መምጣት አያስፈልግህም » ብላ ። ሁሉም ነገር እንዳሰበችው ተሳካላት ። አሁን ደስ ብሏታል ።
« ማሪዮን »
‹‹እህ»
«ቁርስ እንዴት ነው ?»
«በኋላ ይሻለኛል ፤ ዊክ በኋላ ። አሁን ልግባና ማይክልን ልየው »
«እኔ አይቸው እመጣለሁ »
ዶክተር ዊክፊልድ ወደ ፎቅ ሲወጣ እሷ ወደ መጸዳጃ ቤት ጎራ አለች ።

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ማይክል ወደተኛበት ክፍል ስትገባ ሁሉም ነገር ፀጥ ብሎ ነበር፡፡ ዶክተር ዊክፊልድ ዝም ብሎ አልጋ አልጋዉን ይመለከታል፡፡ ነርሷም የለች….
የጥዋት ጸሐይ በመስኮት ገብታ አልጋው ላይ አርፋለአች ከየት እንደሆነ እንጃ የተበላሸ ቧንቧ ይመስላል ውሀ ያለማቋረፍ ጠብ ጠብ ሲል ይሰማል ። ጸጥታው ታይቶ ፤ ተሰምቶ የማይታወቀውን ያህል ነበር ። ድንገት ልቧ ዘለለ ። ልቧ ዘልሎ ባፏ ሊወጣ ደረሰ… ልክ እንደያኔው ፤ ልክ ፍሬዲሪክ ሲሞት እንደሆነው ምነው አምላኬ!ምነው!እጅዋን ወደ ደረቷ ላከችው፣ልቧን ለመያገ ልቧን ይዛ እበሩ ላይ እንደቆመች የጨው አምድ መስላ ቀረች አይኗን ከዶክተር ዊክፊልድ ወደ አልጋው ፤ካልጋው ወደ ዶክተር ዊክፊልድ እያንከራተተች ባለችበት ድርቅ ብላ ቀረች እና አየችው ልጅዋን ማይክን። የለም እንደያኔው አይደለም።እንደ ፍሬዴሪክ አደለም ። እንባ ተናነቃት ።
1.2K viewsTsiyon Beyene, 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 19:31:16 አሁን የንግድና የድርጅት ባለቤት የሆነችው ማሪዮን ሂልያርድ ሙሉ በሙሉ ብቅ አለች ። ልጅዋ ይህን ሁሉ ስትል ቢሰማ ልግደልሸ ሳይላት አይቀርም ነበር ። «ናንሲ ፤ እስኪ ስለአዲሱ ገፅታሽ አስቢ ። ስለአዲሱ ህይወትሽ አስቢ። ስለ አዲሲቷ ናንሲ አስቢ። ስለነዚህ ነገሮች አስቢ አሁን ካለሽበት ሁኔታ ወጥተሽ ስለምታገኝው እዲስ ህይወት አስቢና አመዛዝኝ ፣ ናንሲ ። « በሌላ በኩል እንዲህ እንዳለሽ ብትኖሪ የሚመጣብሽን ደግሞ አስቢው ። እንዲህ ማስፈራሪያ መስለሽ ምን ሆነሽ ልትኖሪ ትችያለሽ? ሱቅ ብትገቢ ፤ ሰዎች ለማየት ይፀየፉሻል። በመንገድ ላይ ድንገት ያዩሽ ሰዎች ይበረግጋሉ ። ህፃናት አይተውሽ አሪ ብለው ያለቅሣሉ ይህን ደሞ አስቢው ። እንዲሀ ሆኖ መኖር የሚቻል ይመስልሻል ? ግን እንዲህ ያለመሆን አማራጭ አለሽ»
«ምንም አማራጭ የለኝም›› እለች ናንሲ ።
«አለሽ ናንሲ… አለሽ ። አዲሱ ህይወት በእጅሽ ነው ፤ ካወቅሽበት ማለቴ ነው» ማሪዮን ከመቀመጫዋ ተነሳች ። እና ቀጠለች «ቀላል ነው ከባድም ሊሆን ይችላል ። ግን አማራጭ ነው» መምረጥ አለብሽ ናንሲ።

ናንሲ አዲሱ ህይወት በእጅሽ ነው የተክፈለውን ያህል እክፍላለሁ ፡፡ ግን አንች ደግሞ ውል ትገቢያለሽ ፤ ከማይክል ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ላለማድረግ ። ይህን ካደረግሽ አዲሱ ግፅታ የግልሽ ነው። ማይክልን ግን ዞር ብለሽ ማየት የለብሽም ነገር ግን ይህን ስጦታ አልቀበልም ብትይ ዞሮ ዞሮ ያው ነው። ማይክል ያንቺ አይሆንም ። ስለዚህ ህይወትሽን በሙሉ ለምን ማስፈራሪያ መስለሽ ትኖሪያለሽ አማራጭ እያለሽ ? ለኔ አይታየኝም!»
«እኔስ እሺ ልበል። ግን ማይክል ይህን ውል ባይቀበልስ? እኔ ልሽሽ ልደበቅ ፤ ግን እሱ ቢመጣስ? ቢፈልግና ቢያገኘኝስ›› «በዚያ አንች መጨነቅ የለብሽም ። አንች ያለብሽ የራስሽን ቃል ማክበር ብቻ ነው። ማይክል የፈለገውን ቢያደርግ ያ የራሱ ጉዳይ ነው»
«ይህን ቃልሽን ትጠብቂያለሽ ? ማለት እሱ ፈልጐኝ ከመጣ ያ የራሱ ጉዳይ ነው ብለሽ ትተይዋለሽ?»
«ቃል፣ ቃል ነው»

ይህን ስትሰማ ናንሲ ደስ አላት ። በዚህ ድርድር ማሪዮን ሂልያርድን እንደተጫወተችባት ገመተች። ምክንያቱም በማይክል ላይ እምነቷ የጠነከረ ነበርና ነው ። ማይክል መኖሯን ካወቀ እናቱ የፈለገችውን ያህል ብትለፋ ናንሲን ሊፈልግ መምጣቱ እይቀርም ። ናንሲ ይህን ስለምታወቅ ኮራች ፤ደስ አላት
«ተስማማን ወይስ..? መልስሽን አልነገርሽኝም ናንሲ አለች ማሪዮን ። በዛባት መቆየት አትችልም ፤ከዚህ በላይ።
« ተስማምተናል » አለች ናንሲ ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
1.4K viewsTsiyon Beyene, 16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 19:31:15 #ቃል
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰባት (7)


በሩ ላይ ቆማ ለረጂም ጊዜ ፍዝዝ ብላ ቆየች ። ልግባና. . . ላድርገው? ... ግራ ገባት ። ለማይክል ነው። ለማይክል ስል ነው። ማይክልን ነፃ ማውጣት አለብኝ አለች ራሷን ለማበረታታት ። ቀስ እያለች እግሮቿን እየጐተተች ወደ ክፍሉ ውስጥ ገባች።

ክፍሉ ጨለማ ነበር። ምንም ብርሃን እንዳይገባ የተከለከለ ይመስላል። መብራቱም አልበራም ። ሻተሮቹም ተዘግተዋል ። አሁንም የለቅሶው የማንተግ ድምፅ ይሰማታል ። ቀስ ብላ ተጠጋች። አልጋው እንደ ጥላ ሆኖ ይታያል ። የልቅሶው ድምፅ ጐላ እያለ ይሰማ ጀመር። «ሰውነው... ማነው? » አለች ናንሲ ። ማሪዮን ተጠጋች። የናንሲ ራሷ ፊቷ በጠቅላላ በፋሻ ተጠቅልሏል ። ድምጺም የታፈነና እንግዳ ነገር ሆኖ ተሰማት ለናንሲ ለራሷ።
«ማነው... ሰው አለ?» አለች ናንሲ ። እና ታለቅስ ጀመር ። «አይኔ አያይም ... ሰው አለ?... አይኔ ፈፅሞ አያይም» አለችና ሳግ አከታትሎ ይነትጋት ጀመረ ። « አይንሽ ምንም አልሆነም ። ሁለቱም አይኖችሽ ደህና ናቸው፤ እንዳታይ የሚከላከልሽ የተሸፈንሽበት ፋሻ ነው» አለች ማሪዮን፡፡ ናንሲ ይህን ብትሰማም ለቅሶዋ ጨመረ ።
«ለምንድን ነው እንቅልፍ ያልወሰደሽ?» አለች ማሪዮን ድርቅ ባለና ስሜቱ በተሟጠጠ ድምፅ «የሚያስተኛ መድሀኒት አልሰጡሽም ?» ማሪዮን ራሷ በህልሟ የምትነጋገር መስሎ ተሰማት። .... መርፌ ወግተውኝ ነበር። ግን መድሀኒቱ ሊሰራ አልቻለም። እንቅልፍ ባይኔ አልዞር አለ» አለች ናንሲ። «ይጠዘጥዝሻል...ወይም ውጋት የመሳሰለ ህመም አለው «ምንም አይሰማኝም ። አካሌ በጠቅላላ ደንዝዟል ። ማን... አንቺ ማን ነሽ?» ስሟን ልትነግራት አልደፈረችም ። በዚያ ፋንታ አልጋው አጠገብ ወንበር ስላየች ሂዳ እዚያ ላይ ቁጭ እለች ። የልጅቷን እጅ አየች። ሁለቱም እጆቿ እንዲሁ በፋሻ ተጠቅልለዋል አይንቀሳቀሱም ። ትዝ አላት ዶክተር ዊክፊልድ የነገራት ። ፊቷ እንዳይጐዳ በእጅዋ መከላከሏ ያለ ነው ። ስለዚህ ሁለቱም እጆቿ በጣም ተጐድተዋል። ለወደፊቱ በሰዓሊነት ሀይወቷን ለመቀጠል ተስፋ የላትም ስትል አሰበች ።

‹‹ናንሲ» አለች ማሪዮን ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን ስም እየጠራች። ግድ የለም ይሁን ለማይክል ስል... ‹‹ናንሲ ....» ድምጺ ለስለስ ያለ ነበር ። «ፊትሽ ምን ያህል እንደተጐዳ ሀኪሞቹ ነገሩሽ » .. በክፍሉ ፀጥታ ነገሰ። ዘለአለም አለም ያህል ጊዜ ሁለቱም ጸጥ ብለው ቆዩ። ድንገት የለቅሶ ሳግ ፀጥታውን አደፈረሰው «በፊትሽ ላይ የደረሰው አደጋ መጠን ከምን እስከምን እንደሆን ነገሩሽ ? አሰቃቂ እንደሆነ አውቀሽዋል ?» አለች ማሪዮን አሰቃቂ የሚለውን ቃል ስትናገር ልቧ ሊከዳት ምንም አልቀራትም። ሁሉ ነገር አስጠላት ። ሆዷ ተገላበጠ ። አንጀቷ ተላወሰ ወዲያው የለም፣ መዳከም አያስፈልግም አለች ማይክልን እያሰበች። «ናንሰ. ፤ የቀድሞ መልክሽን መመለስ ይትርና ትንሽ እንኳ ለማስተካክል በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ እንደተበላሸሽ ነግረውሻል?» አለች ማሪዮን ። የናንሲ ለቅሶ ቁጣ የተቀላቀለበትና ስቃይ የተሞላበት ሆነ።
«አልነገሩኝም ዋሽተውኛል እነሱ ያሉኝ...»
«ናንሲ ፤፡ ሀክምናውን ሊያደርግልሽ የሚችል በሀገሪቱ ውስጥ ያለ አንድ ሃኪም ብቻ ነው ። እሱን ለማግኘትም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዶላሮች ያስፈልጋሉ ። ይህን ያህል ገንዘብም አንች የለሽም ማይክልም አያገኝም »
«ቢኖረውም ያን ያህል ገንዘብ ከፍሎ እንዲያሳክመኝ አልፈቅድም «» የሚያነጋግራት ድምፅም ኑሮና እድልዋም አናደደዷት፤ «አልፈቅ. .. ቅድለትም » አለች ሳግ ኢያቋረጣት ።
«ያሰብሽው ነገር አለ?» አለች ማሪዮን ።
«ምንም ያሰብኩት ነገር የለም!»
«ይህን መስለሽ የማይክልን ፊት ማየት ትደፍሪያለሽ ? እሱስ የሚችል ይመስልሻል ? ርግጥ መቼም በይሉኝታ ትንሽ ሊሞክር ይችላል ። ታማኝ ለመሆን መሞከሩ አይቶርም ። ግን ያን ሁሉ የሚያደርገው ወዶሽ ሳይሆን አዝኖልሽ እንደሆነ እያወቅሽ ደስታ ልታገኝ የምትችይ ይመስልሻል !? » ከዚያ በኋላ ማሪዮን እነገሩ ውስጥ ዝፍቅ ብላ ገባችበት ።
«ናንሲ … ሃኪሞቹን አነጋግሬ ነበር ከድሮው ገፅታሽ አንድም ያልተለወጠ ነገር የለም ። ፊትሽ ፈፅሞ ሌላ ሆኗል ። ስለዚህም የነበረሽ ነገር ሁሉ የለሽም ። ካሁን በኋላ ... ከዚህ በፊት ከኖርሽው ነገር ላንቺ የሚሆን እንደሌለ መገንዘብ አለብሽ ለተወሰነ ጊዜ ሁለቱም ፀጥ አእሉ። ማሪዮን ቀጠለች ። «ከማይክል ጋር ለመኖር ብትሞክሪ ከላይ እንደነገርኩሽ ላንቺም ለሱም ስቃይ እንጂ ሌላ ትርፍ የለውም ። ስለዚህ ቁረጪ ናንሲ። ተለያይታችኋል በቃ ።ማለት ከወደድሽው ይ…ገባሻል። ለሚወዱት ሰው ስቃይ መሆን ደስ አይልም ። አንቺም:..አንቺም ቢሆን መሰቃየት የለብሽም ። አንቺም አዲስ ህይወት ሀ ብለሽ ልትመሰርቺ የምትችይበት መንገድ አለ ናንሲ » ማሪዮን ናንሲ ትናገር እንደሆነ ጠበቀች ናንሲን ግን ሳግ ሲነትጋት ይሰማ እንጂ ምንም ቃል አልተነፈሰችም ። «ይህ ቢሆን አዲስ ህይወት ፤ አዲስ አለም ልታገኝ የምትችይበት መንገድ ይኖራል » አለች ማሪዮን ። አሁንም መልስ የለም ። «አዲስ ፊት ፤ አዲስ ገፅታ ፣ አዲስ ኑሮ!» አለች ማሪዮን ሳጉ ቆመ ።
«ከየት ? እንዴት ›› አለች ናንሲ ።
«እኔ እማውቀው ሰው አለ ። ሳንፍራንሲስኮ ውስጥ የሚኖር። ይህ ሰው እንደገና ቆንጆ ሴት ሊያደርግሽ ይችላል ። ይህ ሰው የስእል ስራሽን እንድትቀጥይ ሊያደርግ ይችላል ። ይህን ለማድረግ በርግጥ ረጂም ጊዜና በርካታ ገንዘብም ይወስዳል ። ሆኖም ገንዘብም ቢጠፋ ፤ ጊዜም ቢወስድ ከሚገኘው ጥቅም ጋር ሲነፃፀር ኢምንት ይሆናል ። አይመስልሽም ናንሲ?›› አሁን ማሪዮን በነገሩ ገባችበት ። ውል መዋዋል ነው የንግድ ውል ። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚተረፍበት ውል። ያ ደግሞ ሥራዋ ነው።

«ታዲያ ያን ያህል ገንዘብ እኛ ከየት እናመጣለን!›› አለች ናንሲ። «እኛ» የሚለውን ቃል ስትሰማ ማሪዮን ሂልያርድ ሽምቅቅ አለች ። « እኛ›› ያለችው እሷን ከማይክል ጋር ደብላ መሆኑ ነው ስትል አሰበች። ተናደደች። ቢሆንም ለጊዜው መቻል አለባት። ይህን የጀመረችውን ነገር በትእግስት ከዳር ማድረስ አለባት፡፡
«ልክ ነሽ ናንሲ ። በቀላሉ የሚቻል አይደለም ። ግን እችላለሁ ። ማን እንደሆንኩ እስካሁን ሳታውቂ አልቀረሽም፤ አይደለም ?››
« አውቄአለሁ»
«እንዳልኩሽ ማይክል ከእንግዲህ ያንች ሊሆን እንደማይችል ገብቶሻል ፤ አይደለም ? በተለይ እንዲህ ሆነሽ ቢያይሽ እሱንም ፀፀቱ ሊገለው እንደሚችል ይገባሻል ፤ አይደለም
«ይገባኛል »
«ስለዚህ ታማኝነትህን አሳየኝ ማለት ያውም ቢተርፍ ማለቴ ነው፤ መፈታተን ፤ በጣም ከፍተኛ የሆነ ክፋት እንደሆነ ትረጃለሽ፤ አይደለም ናንሲ ? ይህን አእትረጂም ?›»
«እረዳለሁ » አለች ድክም ባለ ድምፅ ።
«ስለዚህ የቀረ ነገር ቀርቷል ።። የጠፋ ነገር ጠፍቷል ፤ አይደለም?»
«አዎ»
«ናንሲ ፤፡ አንድ ሃሳብ ላቀርብልሽ እፈልጋለሁ ። ድርድር ነው፡።፡ እንደምንስማማ ተስፋ እለኝ፡፡
1.2K viewsTsiyon Beyene, 16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 12:59:46 #ከማበድህ_በፊት_5_ነገሮችን_አስታውስ!

#የስኬት_አቡጊዳ_መጽሐፍ

#1_ዛሬ_ለራስህ_እረፍት_ስጠው፡፡ ስላስጠቁህ እና ተስፋ እንድትቆርጥ ስላደረጉህ ሰዎች እያሰብክ ከመዋለል ይልቅ ያበረታቱህን ሰዎች በምታደንቅበት እና በምታመስግንበት ጉልበትህ ላይ ትኩረትህን ዳግም አድርግ፡፡ አስታውስ አንዳንድ ሰዎች የሚፈጽሙብህን ክብረ ቢስ ተግባር እና ንግግር መቆጣጠር አትችል ይሆናል፤ ነገር ግን ዛሬ በእነርሱ ላለመረበሽ መወሰን ትችላለህ፡፡

#2_በጫጫታ_ውስጥ_ገብተህ_አትጥፋ
አንዳንድ ጊዜ ልብህ ቀድሞ ያወቀውን ነገር አእምሮህ ለመቀበል ጊዜ ይወስድበታል፡፡ ተንፍስ፡፡ ምስክር እንጂ ዳኛ አትሁን፡፡ የራስህን ድምጽ - የራስህን ነፍስ ለማዳመጥ ለራስህ ቦታ ስጥ፡፡ ብዙ ሰዎች በዓለም ውስጥ ያለውን ጫጫታ በመስማት በሁካታው መሀል ገብተው ይጠፋሉ፡፡

#3_ደግ_ሁን_ግን_እምቢ_ማለትንም_ተማር! ሁልጊዜ በሁሉም ነገር የሚስማማ ሰው ልትሆን አትችልም፡፡ የዚህ አይነት ሰው ከሆንክ የሰዎች መጠቀሚያ ትሆናለህ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወሰን ማስመር አለብህ፡፡ አንዳንድ ጊዜ “አይሆንም” ወይም “እምቢ” ማለት አስፈላጊው የራስ እንክብካቤ ነው፡፡

#4_ሕይወት_ስሜታዊ_ሽክርክሪት_አትሁንብህ
ሕይወት ስሜታዊ ሽክርክሪት ስትሆንብህ ቀለል ያሉ ልማዶችን በመገንባት ራስህን አረጋጋ፡፡ አልጋህን አንጥፍ፡፡ አትክልቶችህን ውኃ አጠጣ፡፡ የራስህን ሳህንና ማንኪያ እጠብ፡፡ ቀላልነት እርጋታን እና ጥበብን ይስባል፡፡

#5_ተይዘህ_አትቅር
ምንም አድርግ ምን ዛሬ ስሜትህን ባበላሸው ትንሽ ነገር ውስጥ ብቻ ተቀርቅረህ ወይም ተይዘህ አትቅር፡፡ ተንፍስ፤ ከፊትህ ላለው ነገርም ምስጋና አድርስ፡፡ አንዳንዶቹ በረከት ናቸው፤ ምንም ነገር ደግሞ ለዘላለም አይቆይም፡፡ ሕይወትን በየእለቱ በሚገጥሙ አሉታዊ ገጠመኞች ላይ ለማባከን በጣም አጭር ናት...

#አዎን_የተሻለ_ማሰብ_ትችላለህ ይህም ማለት ውሎ አድሮ የተሻለ መኖር እንድትችል ሊያደርግህ የሚችለውን ውስጣዊ ጥንካሬህን መክፈት ትችላለህ ማለት ነው፡፡

#የስኬት_አቡጊዳ_መጽሐፍ


ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
1.2K viewsTsi , edited  09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 12:54:11
የመዝጊያ መልዕክት ከ #እረኛየ!!!

ይገርማል ሁሌም ድክም ብሎኝ ስቀር ምርኩዝ ይልክልኛል፤ አንቺም የበቃልዬ ምርቃት ይድረስሽ ሲል ምርኩዝ አርጎ አመጣሽ። በቃልዬ አብነትን የመረቃትን ሰምተሻል? "እውቀት እንደ ምንጭ ይፍለቅብሽ፣ እንደጅረት ወርዶ ለዓለም ሁሉ ይድረስ ብሎ ነው የመረቃት" ። ለአንቺም ከምርቃቱ ይድረስሽ። አሜን፤ ጎሽ ልጄ አዎ፤

እማማ እንመለስ? ደከመዎት?
አየ ልጄ መመለስማ የለም፤ ወደኋላ ዞሬ መመልከቴ ከመነሻየ ምን ያህል ርቀት ተጉዤ እንደመጣሁ ለማወቅ፣ ወደፊት ለመጓዝ ተስፋ እንዲሆነኝ ነው፤ መመለስማ የለም።

ብዙ መከራ አይቻለሁ፣ ብዙ መከራና ስቃይ ፈትኖኛል ልጄ፤ ያኔ ከአበባየ መርገፍ በኋላ ጉልበት ተስኖኝ እቤት ቀርቼ ነበር።

ሰው የጭረት ጠባሳውን እየገለጠ፣ የሌላውን ቁስል እየወጋ፣ በቂም መከፋፈሉን አይታ፣ መቁሰሌ ሌላውን ሰው ወደ ሞት የሚወስድ አይሁን፣ ለእርቅና ለይቅርታ ይሁን ብላ የመንደሩን ሰው በአደራ መራችው። ወደኋላ መመለስ የለም ብላ ሁሉን በአንድነት አስተሳስራ የኔ ልጅ ወደፊት መራችው። ለወደደችው፣ ላመነችበት ዋጋ ከፈለች፤ ዋጋ ከፈለች እኔ ግን እሷ የከፈለችውን ዋጋ ከንቱ ለማስቀረት እቤቴ ቁጭ አልኩ፣ እቤት ቀረሁ፤ ግን ትውልድ አይጥፋ፣ ተስፋ አይጥፋ ይሄው አንቺ መጣሽልኝ እና ምርኩዝ ሆነሽ ይዘሽኝ ወጣሽ።

ዛሬ እግሬ እንዲቀጥልና እንድበረታ ያጸናኝ ተስፋ ነው።

የኔ ልጅ በዚህ እድሜሽ የደረሰብሽን እናትሽን ማጣትሽን ሰምቻለሁ ልጄ ግን ወደኋላ መመልከቱ ምን ያህል ትተሽው እንደመጣሽ ለማወቅ እንጂ ወደኋላ ለመመለስ አይሁን፤ አይሁን ልጄ።

ከመጣንበት ይልቅ ገና የምንሄድበት ብዙ ነው።

አሁን ምንድን ነው የሚመረቀው?
ዛሬ ሸክላ በመስራት ነው የሚያስመርቁት ብለዋል።
ጎሽ ጥሩ አድርገዋል የሰው ልጅስ ከመነሻው እንዲሁ አይደል እንደሸክላ ከአፈር
1.1K viewsTsi , 09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ