Get Mystery Box with random crypto!

✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

የቴሌግራም ቻናል አርማ itsmetsiyearsemalj — ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘
የቴሌግራም ቻናል አርማ itsmetsiyearsemalj — ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘
የሰርጥ አድራሻ: @itsmetsiyearsemalj
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.69K
የሰርጥ መግለጫ

በቤቴ ሲታደሙ ከጥበብ ማዕድ ይቋደሳሉ
በኔና በሌሎች የተፃፉ
🌹ግጥሞች🌸
🌹ወጎች 🌸
🌹ልቦለዶች 🌸
ሌሎችም...
━━━━━━━━ ✦
ለማንኛውም አስተያየት
@Tsiyon_awit and
@itsmetsita
ይጠቀሙ።
Join us
@itsmetsiyearsemalj

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-09 19:35:02 ጉብኝቴ አጠናቅቄ መጨረሻ አካባቢ አንድ ተቀፍሮ ለነገ የተዘጋጀ ብረት ብቻ የታሰረበት Footing ጋር ደረስኩ…..ስመለከተው አሰራሩ የተወታተፈና ሴንተሩን ያልጠበቀ ሆኖ ታየኝ፡፡በርቀት ላይ ስራ ሲሰሩ የነበሩትን ጋሽ አህመድንና በሪሁንን ጠራዋቸው….ቦታውን በደንብ ለማየት ጨለም ስላለኝ እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም…
‹‹ማነሽ እህት…ማን ነበር ስምሽ.እስኪ ባትሪው ይዘሺልኝ ነይ››
‹‹የትኛውን?›
‹‹አንዱን… ደህና የሚያበራውን››
‹‹እሺ›› ብላ ቆርቆሮ በቆርቆሮ ወደ ተሰራው እስቶር ሮጣ ሄደች...በፍጥነት በግራዋ አንድ ባትሪ በቀኞ ሌላ ባትሪ ይዛ መጣች፡
ሁለቱንም ተራ በተራ እየሞከረች ‹‹የትኛውን ልስጥህ ››አለቺኝ…..በዚህን ጊዜ በሪሁንና ጋሽ አህመድ መጥተው ስድስት ሜትር የሚረዝመው ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ነበር…አይዳ ደግሞ ከልጅቷ ጎን ልክ እንደጋርድ ተገትራ ቆማለች፡፡እኔ የጉድጎዱ ከንፈር ላይ ቆሜ አንዱን ባትሪ ከልጅቷ ተቀበልኩና እታች ላሉት ለማቀበል ሞክር ጀመር… እሷም እንደእኔው የጉድጓዱ ከንፈር ጋር ቆማ ሁላችንም እንዲታየን ወደታች ማብራት ጀመረች፡፡
አያችሁ እዛ ጋር ያለው ኦቨርላፕ ትክክል አይመስለኝም..እስቲ ቼክ አድርጉት …››ላስረዳቸው ገና ስጀምር ….የቆምንበት አፈር የመንሸራተት ስሜት አሳየ.. እርስ በርስ ተያይተን ሌላ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የማሰቢያ ጊዜ ከማግኘታን በፊት ከእኛ ውጭ ያለ ከጥልቁ ሲኦል የተላከላ የሚመስል ኃይል ጎትቶ እንደጨመረን አይነት እግራችን ከዳንና ወደጉድጎዱ ተስፈንጥረን ገባን…
እንግዲህ የጉድጎዱ ጥልቀት ስድስት ሜትር ከሰላሳ ነው…. የሚቀበለን እንደአልጋ የተረበረበ ባለ 32 ዲያሜትር የአርማታ ብረት ንጣፍ እና ብረቱን ዙሪያውን አቅፎ የያዘው ወፍራም ፎርምወርክ (ጣውላ )ነው….ወይንም እድለኖች ከሆን ከታች ጉድጓድ ውስጥ ስራ ላይ በሚገኙትን ጋሽ አህመድ ና በሪሁን ጭንቅላት ላይ እናርፋለን…..እኛ ከከባድ ጉዳት እንተርፋለን…እነሱ ደግሞ ምን አልባት አንገታቸው ይቀነጠሳል፡፡
ስንት ሜትር ላይ እንደሆነ አናውቅም አዲሷን እስቶርን ኪፐር በአንድ እጄ በሌላ እጄ ደግሞ የአይዳን ቀሚስ ጨምድጄ ይዤ ነበር … ..በዛ ጭንቅ ላይ ሆኜ ‹‹አሁን እንዲሀ አንድ የተከበርኩ እና የተፈራው ፕሮጅት ኢንጂነር በሁለት ሴቶች መካከል ተጣብቄ ያየኝ ሰው ምን ይላል…?›› እያልኩ አስባለው ፡፡
…አዲሶ ልጅ . ኢየሱስ ድረስልኝ….ኢየሱስ ድረስልኘ.. እያለች ትጮኸለች
ከበታቻችን‹‹ አላዋክበር …አላዋክበር….››የሚል ድምፅ ይሰማኛል…….ጋሽ አህመድ መሰለኝ
.በጉጉት ወደሚሄድበት ሽርሽር ቦታ ለመድረስ እንደጎጎ ህፃን<<ቆይ አንደርስም እንዴ?..››ስትል ጠየቀች አይዳ ነች….ምንም የመለሰላት የለም
በእውነት ግን አንደርስም እንዴ ?ስል በውስጤ እራሴን ጠየቅኩ….ስድስት ሜትር ይሄን የህል እሩቅ ነው….?ነው ወይስ የቆሪጥ መንፈስ ወደ ጥልቁ የቢሾፍቱ ሀይቅ እየጎተተን ይሆን…?ምንድነው ጉዱ ?ቢሾፍቱ ሀይቅ አፋፍ ላይም የቤርሙዳ ትርያንግልን አይነት ታአምራዊ ማጅክ አለ እንዴ…?››በውስጤ ያሰብኩት ጭንቀት ወለድ ሀሳብ ነው፡፡
ከረጅምምምም የእድሜ ልክ ያህል ከሚረዝሙ ደቂቃዎች ቡኃላ መሬት ስናርፈ እኔ በሁለቱ ሴቶች መካከል እንደተጣበቅኩ ነበር.. እርስ በርስ ተያየን….
‹‹ወይኔ እማዬ ድረሽ…ቂጤ ተጨፈለቀ…››ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማውት የአይዳ ንግግር ነው፡፡
‹‹ቂጥሽ መጨፍለቁ ምንም አይደል ነፍሽ ግን አለ?››
‹‹ቂጤ ከሌለ ነፍሴ ምን ያደርግልኛል?››የእሷ መልስ ነበር ፡፡
.ዙሪያችንን ስናይ እንደእስፖንጅ የሚያነጥር ቄጤማ የተነጠፈበት መሬት ላይ ነው ያረፍነው ….በሁለታችንም በእጃችን ያለው ባትሪ እየበራ ነው፡፡ያለንበት 2.5×2.5 ስፋት የተቆፈረ የfoothing ጉድጓድ ሳይሆን አንድ መለስተኛ ሳሎን ስፋት ያለው ግዙፍ ዋሻ መሳይ ክፍል ነው፡፡ ከእኛ ወደኣራት ሜትር እርቀት ላይ ጋሽ አህመድና በሪሁን ጎን ለጎን ተዘርረው እርስ በርስ በድንጋጤና በገረሜታ እየተያዩ ነው፡፡ምንድነው እየሆነ ያለው..?ለ foothing የተቀመጠው ብርት ከእኛ በአንድ ሜትር ርቀት ዘፍ ብሎ ቁጭ ብሎል፡፡ጣውላዎቹና መቀሰቻ እንጨቶቹ ተበታነው ወለሉን ሞልተውታል፡፡አይኔን ወደላይ አቀናው ትልቅ አለት ድንጋይ በመጣንበት አቅጣጫ ተቀርቅሮ አፈርና ብስባሽ ነገሮች ደፍነውታል፡፡አዎ ጉድጎዱ ተደርምሶል፡፡
በአስፈሪው የቢሾፍቱ ገደል ሀይቁ ጠርዝ ስር..ምን አልባትም ከሀይቁ ወላል በታችም ሊሆን ይችላል የአንድ ድርጅት ሰራተኞች የሆን ሁለት ሴት እና ሶስት ወንዶች በድምሩ አምስት ሰዎች የተፈጠሮ ታጋቾች ሆነናል…ከነነፍሳችን ተቀብረናል…ምን አልባትም አልቆልን ሊሆን ይችላል፡፡

ይቀጥላል .....


ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
654 viewsTsi B, 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 19:35:02 በህይወት መንገድ ላይ……
( ታጋቾቹ)
ምዕራፍ-አንድ
(በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)
///
እኛ የዘላለም ተጓዦች ነን…..ለዘላለም በሁለንተና ውስጥ ቅርፃችንን እየቀያርን ከአንዱ አፅናፍ ወደ ሌላ አፅናፍ እየተላጋን የምንኖር ተንከራታች እና ተቅበዝባዥ ፍጡሮች፡፡ይህ ታርክ ግን ስለዘላለም አይደለም የሚተርከው… ስለቅፅበት ነው፡፡ሰው ተብለን ከተፈጠርንበት ሬሳ ተብለን እስከምንሸኝበት ስላለችው ቅፅበት አንድ ነጠላ ታሪክ ነው…..ከዛ በፊትም ሆነ ከዛ ቡኃላ ስላለው ብዙም እውቀቱ ስለሌለን ብንናገርም መቀባጠር ብቻ ነው የሚሆንብን፡፡
ተወልደን ወደሞታችን እየተጎዝን ነው፡፡በእያንዳንዱ ቀን ተኝተን ስንነቃ ከበላያችን የተሰቀለውን የሞት ቅርንጫፍ ዘንጥለን ወደገደሉ ለመሽቀንጠር እየተንጠራራን…. በተንጠራራንበት ቅፅበት ሁሉ የሆነች መጠን ወደቅርንጫፉ እየቀረብን ነው፡፡ግን ይህን ለማሰብ ዳተኞች ነን፡፡ስለዚህም የዘላለማዊነትን ምኞት በጭንቅላታችን ጠቅጥቀን ትርምሱ ውስጥ ገብተን እንንቦራጨቃለን….ማግበስበስ ውስጥ እንዳክራለን…..ትንፋሽ እስኪያጥረን ብኩንና ተቀበዝባዥ እንሆናለን፡፡በዛም የተነሳ መንገዳችንን ለመመርመርና ለማጣጣም እድል አይኖረንም….ጉዞችን የእውር ድንብር እይታችንም በደመነፍስ ነው፡፡እኔም ያው ሰው ነኝና እንደዚሁ ነበር ጉዞዬ…

እድሜዬ ሰላሳ ስድስት ሆኖታል፡፡ይህን ያወቁት እንግዲህ ከልደት ሰርተፍኬታ ላይ መነሻውን በመውሰድ እስከአሁን ያለውን ዓመት ቆጥሬ ነው፡፡..የፀሀይ መውጣት እና መጥለቅ ከሰው ልጅ መወለድና መሞት ጋር ይመሳሰልብኛል፡፡የፀሀይ መውጣት ከመወለድ ጋር የፀሀይ መጥለቅ ደግሞ ከመሞት ጋር፡፡

ፀሐይ ወጣች ስንል ተፈጠረች ማለታችን ሳይሆን ለእኛ እይታ ተከሰተች ብርሀኗ እና ሙቀቷ ምድራችን ጎበኛት ማለታችን ነው እንጄ ከመውጣቷ በፊተ ባለው ለሊት የለችም ማለት አይደለም በትክክልም አለች፡፡አንድ ሰውም ተወለደ ስንል ከመወለዱ በፊት የለም ማለት አይደለም በሌላ ዓለም በሌላ ቅርጽ ወይም በማንገምተው ህልውና ነበር..(ምክንያቱም እግዚያብሄር የሰውን ልጅ አንድ ቀን አንድ ላይ ነው የፈጠረው..)ሲወለደ በዚህ ምድር ተከሰተ ማለታችን ነው እንጂ ስለመፈጠር ማውራታችን አይደለም፡፡ፀሀይ የቀን ውሎዋን አጠናቃ ስትጠልቅም ከሰመች ጠፋች ማለታችን አይደለም….ከጠለቀችም ቡኃላ ከነምሉዕነቷ መኖሯን እንደምትቀጥል እናምናለን እናውቃለንም ፡፡ ሰውም ሞተ ስንል ነፍሱ ከምድር ህልውና ተነጠለች፤ ጊዜያዊ ቆይታዋንም አጠናቀቀች ማለታችን እንጄ ጭሩሹኑ ወደአለመኖር ተሸጋገረች ከሰመች ማለታችን አይደለም፡፡

ያው እንደነገርኮችሁ እድሜዬ 36 ነው ፡፡ግን ደግሞ እድሜ እንደዛ አልነበረም መቆጠር ያለበት….በህይወታችን እርባነቢስ ሆነው ዝም ብለው የሚያልፉ ትርጉመቢስ የሆኑ ቀናቶች፤ ሳምንታቶች እና አመታቶች አሉ..አሁን እነሱ ከእድሜያችን ተደምረው እንደኖርንባቸው መቆጠር ነበረባቸው?፡፡ደግሞ አንዳንድ ጊዚያቶች አሉ አንፀባራቂና ወርቃማ የሆኑ…ማንነታችንን የሰራንባቸው፤ ለነፍሳችን መዝናኛ በአበባ ያጌጠ አፅድ ፤ በፍራፍሬ የተሞላ ጋርደን ማዘጋጀት የቻልንባቸው፤ ጥቂት ግን ደግሞ በተደራራቢ ድርጊት የተሞሉ..በመከራና አሰቃቂ ድርጊቶች የታጠሩ…ተስፋ በማስቆረጥ እና መልሰው ደግሞ ብጣቂ ተስፋ በመስጠት በህይወት ዥዋዝዌ እያላጉ እያፈረሱ መልሰው የሚሰሩን …ለዘመናት የገነባነውን መኮፈሳችንን የሚቦረቡሩ….ኩራታችንን ከአመድ ሚደባልቁ….የማናውቀውን እራሳችንን የሚያስተዋውቁን…በስቃይ እሾህ የታጠሩ ግን ደግሞ ፍሬያማ ጊዜያቶች…እና እነሱ ከእድሜያችን ጋ ሲደመሩ በሁለት ሶስት እጥፍ መባዘት አልነበረባቸውም….?
እና ለዚህ ነው እድሜዬን ሲጠይቁኝ ስንት ማለት እንዳለብኝ ግራ የሚገባኝ፡፡ለማንኛውም አሁን ስለነዛ በልኬት ጥቂት ግን ደግሞ በተደራራቢ ትንፋሽ አስቆራጭ ድርጊት የታጨቀ ኩነቶች ነው የማወራችሁ..ከዘልዛላው ህይወቴ ላይ ተቦጭቀው በጉልህ ስለሚነበቡ አይረሴ ቀናቶች ፡፡
እለቱ አርብ ነው፡፡ሰዓቱ ደግሞ 12.30 ….ስራ ላይ ነኝ…የስራ ቦታዬ በተፈጥሮ ውበት በደመቀችው የመዲናይቱ አዲስ አበባ ኮረዳ ጎረቤት በሆነችው ቢሾፍቱ ከተማ ነው፡፡
በትክክል ከቢሾፍቱ ከተማ እንብርቶ በሆነው ቢሾፍቱ ሀይቅ ጠርዝ ላይ ነው ያለውት ፡፡ይዚህን ሀይቅ ጠርዝ ታከን እዚህ አስቸጋሪ ገደልና ኮረብታማ ቦታ ላይ አስደማሚ ሪዞልት እየገነባን ነው፡፡በዚህ የሪዞልት ግንባታ ላይ ፕሮጀክት ኢንጂነር ሆኜ በመስራት ላይ እገኛለው፡፡ ስራ ከጀመርኩ አመት ከስድስት ወር ሆኖኛል፡፡ፕሮጀክቱ በሁለት ፌዝ የሚገነባ ሲሆን አሁን አንደኛውን ፌዝ ገንብተን ጨረሰን ፊኒሽንግ ላይ ስንሆን አንደኛውን ደግሞ ገና ቁፋሮ ጨረሰን ፋውንዴሽን እየሞላን ነው፡፡አንደኛውን ፌዝ ሰርተን ለማጠናቀቅ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሚባል መስዋዕትነት ከፍለናል፡፡አንድ ሰው ሞቶብናል.ከአራት በላይ ሰዎች በስራ ላይ እያሉ አደጋ ደርሶባቸው አካለጎደሎ ሆነዋል፡፡ሁለተኛውን ፌሰዝ ግን ከመጀመሪያው ያገኘነው ልምድ ቀላል የሚበል ስላልሆነ በዛ መጠን እንደማንፈተን እርግጠኞች ነኝ፡፡
ሪዞርቱ የሚያሰርፍበት ቦታ እጅግ ሳቢና አስደማሚ መልካአምድር ያለበት ቢሆንም ለግንባታ ግን በጣም አስፈሪና ፈታኘ ነው፡፡አሁን የቆምኩበት አለት ላይ ሆኜ ቁልቁል የግዙፍ እስትዲዬም ሜደ የመሰለውን ክቡ ሀይቅ ከነውበቱና አስፈሪነቱ ይታየኛል፡፡፡፡በዚህ ሰዓት ሰራተኛ ሁሉ ወጥተው ሄደዋል…እኔ ፤ የሳይቱ ፎርማኑ ጋሽ አህመድ ፤ዋናው ፌራዩ(የብረት ሰራተኛ) በሪሁን እና ከአመት ቆይታ ቡኃላ ሰሞኑን ከስራ ልትሰናበት በርክክብ ላይ ያለችው እስቶር ኪፐሯ አይዳ እና እሷን ተክታ ሰሞኑን የተቀጠረች አንድ ለጊዜው ስሞን የማላውቃት ልጅ ነን በሳይቱ ውስጥ ያለነው፡፡ ፡፡ሰራተኛ ከወጣ ቡኃላ ወደኃላ ቀርቶ በእለቱ የተሰራውን ስራ ማየት የዘወትር ልምዴ ነው፡፡ሳይቱ ከግርግር ነፃ ከወጠ ቡኃላ በስክነት የእለቱን ስራ ማየት..በእለቱ የተሰራውን መልካም ስራና የጠፋና የተበላሸም ካለ ግልፅ ሆኖ ስለሚተይ የሚቀጥለውን ቀን ፐሮግራም ለመከለስ ከፍተኛ እገዛ ያደርግልኝል፡፡
ነገ ኮንክሪት ለመሙላት የተዘጋጁ አስር የሚሆኑ footing ስላሉ ዛሬውኑ የብረት ስራቸው በትክክል በዲዛይኑ መሰረት መቀመጣቸውን እያረጋገጥን ነው፡፡
አና እንደተለመደው ከአንዱ ኮረነር ወደሌላወ ኮርነር እየተዘዋወርኩ በመመልከት ላይ ሳለው ከኃለዬ ድምፅ ሰማው
‹‹…አንጂነር የምትፈልገው ነገር አለ..?ልወጣ ነበር ››አለችኝ..አዲሶ እስቶር ኪፐር
‹‹ቆይ ትንሽ ጠብቂንና መኪና ስለያዝኩ እሸኝሻለው….እነበሪሁንም አሉ አንድ ላይ እንሄዳለን…. አንድ 10 ደቂቃ ጠብቂን…እሷ ግን መሄድ ትችላለች››አልኳት..አይዳን ማለቴ እንደሆነ ሁለቱም ገብቶቸዋል፡፡እሷ.እንድትቆይ የፈለኩት ምን አልባት ከስቶር የምንፍልገው እቃ ይኖራል የሚል ግምት ስለወሰድኩ ነው፡፡
‹‹እሺ …እጠበቅሀለው››አለቺኝ
‹‹እኔም እሷን እጠብቃለው…..ሆሆይ ከስራ ሰዓት ውጭ እህቴን ሶስት ወንዶች መካከል ትቻት አልሄድም…..ምን ይታወቃል››አለች አይዳ..እንግዲህ ነገር እየፈለገች መሆኑ ነው……ከስራ የለቀቀችው እሷ ፈልጋ ሳይሆን እኔ አባርሬያት ነው….ለምን የሚለውን ሌላ ጊዜ ነግራችሆነው..እሷም ታዲያ አሁን በዚህን ሰዓት እዚህ ሳይት ላይ የተገኘችው ከአስራአምስት ቀን በፊት ስለተዋወቀቻት ሴት ደህንነት ተጨንቃ ሳይሆን እኔን ምቾት ለመንሳትና ለማበሳጨት ነው…አዎ አይዳ እንዲህ ነች፡፡የተናረችውን እንዳልሰማው ሆኜ ትኩረቴን ወደስራዬ መለስኩ፡፡
742 viewsTsi B, 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 07:56:26 Watch " ያበደው ፍቅሬ ድንቅ ተከታታይ ልብ ወለድ ትረካ. ፀሀፊና ተራኪ ፅዮን በየነ / Yabedew fkre @Tsion tube" on YouTube


1.0K viewsTsi B, 04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 19:58:18 ‹‹ይቅር ስላልሺኝ በጣም አመሰግናለው..እርግጠኛ ሁኚ በቀሪው ህይወታችን እክስሻለው….ምርጥ ባል ነው የምሆንልሽ››
‹‹ምርጥ ባል እንድትሆንልኝ አይደለም የምፈልገው ምርጥ ልጅ እንድትሆንለኝ ነው የምፈልገው.እናትህ መሆን ነው የምፈልገው.የእንጀራ እናትህ››
‹‹እያሾፍሽብኝ ነው እንዴ?›
‹‹አይ እውነቴን ነው …ታውቃለህ በጣም የማፈቅረውን ሰው በሞት ተነጥቄያለው.እሱን መመለስ አልችልም…ግን ደግሞ በህይወት ያሉት አባትህን አፈቅራቸዋለው ….እሳቸውን ማግባት ነው የምፈልገው››
‹‹እየተበቀልሺኝ ነው?››
‹‹እሱን እንደፈለክ ተርጉመው..ግን ይቅር ተባብለናል ያልነው የእውነታ ከልባችን ከሆነ ስለበቀል ማውራት ከእኛ የሚጠበቅ አይደለም››
‹‹እና አባትህን ላግባ ማለት ሌላ ምን ትርጉም ልስጠው እችላለው?ለመሆኑ እኔ እሺ ብልሽ አባዬ በዚህ እብድ ሀሳብሽ የሚስማማ ይመስልሻል.?ነው ወይስ እናቴን እንደምትመስይ ደጋግሞ ሲነግርሽ ተምታታብሽ››
‹‹አንተ እንዲስማማ ታደርገዋለህ ››
‹‹ጭራሽ እኔው..?››
‹አዎ አንተው.አባትህን ትሄድና እኔና አንተ ያለንን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ በስምምነት እንዳቋረጥን ..እና እስከአሁንም ቃል ከመገባባት በዘለለ ምንም የፈፀምነው ፃታዊ ትስስር እንደሌላ ታስረዳቸዋለህ.፡፡በተጨማሪም አኔ እሳቸውን ማግባት እንደምፈልግ ትነግራቸዋለህ…..እናም ለአንተ ሲሉ እንደያደርጉት እሺ እስኪሉህ ድረስ እግራቸው ስር ወድቀህም ቢሆን ትማፀናቸዋለህ፡
‹‹ማይሆነውን?››
ስልኳን አወጣች…ጎረጎረችና የሆነ ነገር ላከችለት
‹‹ምርጫ የለህም…የላኩልህን ነገር እየው…ይሄ እኔ ጋር ብቻ ሳይሆን ጠበቃዬ ጋርና በጣም የማምናቸው ሌሎቸ ሰዎች ጋር በተጠበቀ የሚስጥር እቃ ተቀምጧል..እኔ አንድ ነገር ብሆን ወይም አንተ በዚህ ሀሳቤ የማትስማማ ከሆነ ወዲያውኑ ፍርድ ቤት ይቀርባል….ከዛ የሚሆነውን መገመት ቀላል ነው፡፡›
ተስገብግቦ ሞባይሉን አወጣና የላከችለትን ፎልደር ከፈተው….ወዲያው ደንግጦ ዘጋው..መልሶ ከፈተው..ወደ .ጆሮው ለጥፎ አዳመጠው.ይህ ቀጥታ ለእድሜ ልክ ዘብጥያ የሚያስወረውረው መረጃ ነው፡፡
‹‹ከየት አገኘሽው?›
‹‹እሱ ምን ደያደርግልሀል…አንተም ብቻ አይደለህም እኮ እስማርት…››
‹‹አሁን መሄዴ ነው››
‹‹አንድ ሳምንት ሰጥቼሀለው››
ምንም አልመለሰላትም በተቀመጠችበት ጥሏት አንገቱን እንዳቀረቀረ በተሰበረ ቅስም….ሆቴሉን ለቆ ወጣ፡፡

ተፈፀመ


ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
1.7K viewsTsi B, 16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 19:58:18 //
6 ሰዓት ሁለቱም በተቃጠሩት ሆቴል ፊት ለፊት ተቀምጠዎል።እሷ አሁንም ጥቁር በጥቁር እንደለበሰች ነው።ቢሆንም ከሰሞኑ ጉስቁልናዎ ቀስ በቀስ እያገገመች መሆኑን ጠቅላላ ሁኔታዎን አይቶ መገመት አይከብድም...እሳቸው ነጭ በነጭ የባህል ልብስ ለብሰው በቀኝ እጃቸው ነጭ ጭራ ይዘው በሌላ እጃቸው የተንዠረገገ ነጭ ፂማቸውን እያፍተለተሉ ላያቸው የሆነ የመላዕክትን ገፀ_ባህሪ ለመጫወት ዝግጅ የሆነ ባለግርማ ሞገስ ተዎናይ ነው የሚመስሉት።
"ናፍቀሺኝ ነበር...ማለቴ በጣም"
"እኔ ደግሞ ሳዬት ነው ናፍቀውኝ እንደነበር ያወቅኩት"
"ያንን በመስማቴ ደስ ብሎኛል"
"ደግሞም አምሮቦታል "አስባበት ሳይሆን ምላሶን አዳልጧት የተናገረችው ነው።
"ለአንቺ ያለኝን ክብር እንዲያስረዳኝ ነው እንዲህ መዘነጤ ...ለመሆኑ አንቺስ እንዴት ነሽ?*

‹‹ሰላም ለመሆን እየመኮርኩ ነው..ግን ደግሞ በጣም እየናፈቀኝ ነው።"

"አውቃለው… ንግስቴ ጥላኝ ከሄደች ብኃላ እኔሞ በጣም ትናፍቀኝ ነበር።አዎ ናፍቆቱ ስቃይ አለው...ቢሆንም እንድረሳት ስለማልፈልግ ህመሙን እችለዎለው።እንደውም ከቆይታ ብኃላ በናፍቆቱ ምክንያት ልብሽ ላይ የሚሰማሽ ስቃይ ሱስ ይሆንብሻል።..ነገሩ እኔ ካንቺ በተሻለ እድለኛ ነበርኩ››

"እንዴት ጋሼ?"
‹‹ብቻዬን ጥላኝ አልነበረም የሄደችው...ሁለት ልጇቾን ጥላልኝ ነበር የሄደችው ..እነሱም አንድ መፅናኛዎቼ ነበሩ
"ጋሼ"
"አቤት ንግስቴ"
‹‹ለአባቴም ገና ያልነገርኩትን አንድ ዜና ልንገሮት"

"ልስመዎ"

ቀኝ እጇን አነሳችና ሆዶ ላይ አስቀመጠች..አሻሸችው።አይናቸው ተበለጠጠ..‹‹.ምን እያልሺኝ ነው..?
"አዎ ለእኔም ትቶልኝ ነው የሄደው..አርግዤያለው"
‹‹እኔ አላምንም..››ከመቀመጫቸው ተነሱ .ጠረጳዛውን ዞሩና ወደእሷ በመቅረብ አገላብጠው ሳሟት…እሷ እርሷ ማርገዞን የሰማች ቀን በእሳቸው መጠን የፈነጠዘች መሆኗን አታስታውስም፡፡.ወደመቀመጫቸው ተመልሰው ተቀመጡና፡፡
‹‹..እና እግዚያብሄር በፀጋው ዳብሶሻል ማለት ነው?››
‹‹እንግዲህ መሆኑ ነዋ››
‹‹ነው እንጂ…በጣም እድለኛ ነሽ.፡፡በይ አሁን ወደቀልብሽ ተመለሺ፤ የውስጥሽንም ሀዘን ለመቆጣጠር ሞክሪ ፡፡.በማህፀንሽ ለተሸከምሽው በረከት ስትይ…በዛ ላይ የእሱም መንፈስ በቅርብ ሆኖ ያይሻል
‹‹እውነቷትን ነው››
‹‹አዎ ጨክነው ጥለውንማ አይሄዱም…..ልክ እንደከዚህ ቀደሙ ተመልሰው እስኪመጡ ድረስ መንፈሳቸው ይጎበኛናል፡፡
‹‹ለሶስተኛ ጊዜ ተመልሶ የሚመጣ ይስሎታል?፡፡››
‹‹ለሁለተኛ ጊዜ ተመልሶ መምጣቱን አምነሻል ማለት ነው?››
‹‹እኔ እንጃ አርሶ ስላሉኝ ነው…እርሶን ደግሞ አምኖታለው››
‹‹እንግዲያው አዎ አንቺና እሱ የተመቻቸ ዘመን በተመቻቸ ሁኔታ ላይ ተፈጥራችሁ በስርእት መጋባትና በፍቅር አብሮ መኖረ እስክትችሉ ድረስ በተለያየ ትውልድ ደጋግማችሁ ትፈጠራላችሁ...ይህ ነው የእኔ እምነት››
‹‹እኔም እንደዛ ማመን እፈልጋለው›አለች…እውነቷን በውስጧ የሚሰማትን ነው የተናገረችው..አንድ በጣም በነፍስ እንጥፍጣፊ ጭምር የሚያፈቅሩትን ሰው እስከወዲያኛው ለዘለለሙ ነው ያጣውት ቡሎ ማሰብ በጣም ተስፋ አስቆራጭና ጨለማ ሀሳብ ነው..በሆነ ተአምር ዳግም ስጋ ለብሶ በዚህ ምድር ይከሰታል እኔም እንደዛው አደርጋለው...እናም መልሶ በእይታው ለመደንገጥ.. በአይኑ ጥቅሻ ለመቅለጥ..ከዛም በሙቀቱ ለመቃተት እና በፍቅሩ ለመስከር እድል ይኖረኛል ብሎ ማለም ..እጅግ በውስጣችን ብርሀንን የሚረጭ ፋንታሲ ነው፡፡እና እንደዛ ለማመን መንገድ ላይ መሆኗ ተመችቷታል…ምን አልባት ከእሳቸው በላይ የዚህ እምነት ዋና አቀንቃኝ እንደምትሆን ከአሁኑ እየታወቃት ነው፡፡
‹‹ንግስቴ››
‹‹አቤት ጋሼ››
‹‹የዚህ ልጅ የጡት አባት ወይም የክርስትና አባት መሆን እፈልጋለው..ቀሪ ዘመኔን ልንከባከበው እፈልጋለው፡፡የእሷን ልጅ ተንከባክቤ እንዳሳደኩ ሁሉ የአንቺን ልጅ ድንቅ ድንቅ ተረቶች እየነገርኩ ጭንቅላቱን በፍቅር እያሻሸው ማሳደግ እፈልጋለው፡፡አውቃለው ባል ታገቢያለሽ..ባልሽ እንደልጁ ሊንከባከው ይችላል….ብዙ ሞግዚቶች ልትቀጥሪለትና እነሱ ሊንከባከቡት ይችላሉ፡፡.ግን እመኚኝ የእኔን ያህል ልምድ አይኖራቸውም.፡፡በዛ ላይ እንደዛ ማድረጌ እድሜዬን ያረዝምልኛል… አዎ ለራሴ ብዬ ነው››
‹‹ጋሼ…ወንድ ነው እንዴ? ››
‹‹ማ ?››
‹‹ልጁ..በሆዴ ያለው?››
‹‹እኔ እንጃ …ወንድም ሆነ ሴት ምን ለውጥ አለው…ዝም ብዬ አፌ ላይ ለምዶብኝ ነው››
‹‹ገባኝ››
‹‹እና ያልኩሽን ምን አልሺኝ..የጡት አባት ወይስ የክርስትና አባት..የትኛው?››
‹‹አይ እኔ የልጄ ብቻ ሳይሆን የሁለታችንም ጠባቂ አባት እንዲሆኑ ነው የምፈልገው…የእኔም የልጄም.››
‹አግኝቼ ነው..ሄኖክን ልተገቢው ነው እንዴ?ያው እሱን ካገበሽ ለሚወለደው ልጅ አያት ላንቺ ደግሞ አማች ስለምሆን ያው ጠባቂያችሁ ሆንኩ ማለት ነው››
ኮስተር አለች‹አይ በፍፅም እሱን አላገባም››
‹‹ታዲያ እንዴት ለሁለታችሁም ጠባቂ መሆን እችላለው?››ግራ በመጋባት ጠየቋት፡፡
‹‹ምነው እርሶ አያገቡኝም?...ማለቴ ..በፈለግሺው ጊዜ መሸሸጊያሽ እሆናላሁ ብለውኝ አልነበር ?››
‹‹አዎ ብዬሻለው ...ግን እንዴት ነው የሚሆነው?ግራ ገብቶኝ እኮ ነው››
‹‹ልክ ቅዱስ ዮሴፍ ለድንግል ማርያም እንደሆነት አይነት….ልክ እየሱስንም እናቲቱንም በፍጽም ንፅህና እና ቅንነት እንደጠበቀው አይነት…››
‹‹ተአምረኛ ልጅ ነሽ…ከቤተሰቦችሽና ከማህበረሰቡ የሚደርስብሽኝ ጫና የሚሸከም ጫንቃ ካለሽ እኔ ከዚህ በፊት እንደነገርኩሽ ሁሌም ያንቺው ነኝ፡፡›አሏት በፈግታ ተሞልተው፡፡
‹‹እንግዲያው እኔ ቤት ነው የምንኖረው…ከፈለጉ ሰርግ መደገስ እንችላለን፡፡››
‹ሁሉም አንቺ እንደፈለግሽ ይሆናል .. እኔ ካንቺ ጎን ከመኖር ውጭ ምንም ሌላ ፍላጎት የለኝም…የእኔ አንድ ጭንቀት በዚህ ጉዳይ ልጄን ማሳመን እንዴት እንደምችል ብቻ ነው….አባት የልጁን ፍቅረኛ ነጥቆ አገባ ሲባል ለሰሚው ከባድ ነው…›
‹‹ጋሼ የሄኖክነ ነገር ምንም አይጨነቁ ..የማናግረው እኔ ነኝ….››
‹‹እንደዘ ይሻላል?››
‹አዎ .ስለእሱ ምንም አይጨነቁ….እርሷን ሳይቀየም ፍቃደኛ ይሆናል፡፡››
‹‹እሺ እንዳልሽ….ግን ከዚህ ቡኃላም ጋሼ እንዳልሺኝ ነው የምትቀጥይው›
ፈገግ አለች…‹‹እስኪ በሂደት እንዴት ማስተካከል እንደምንችል እናስብበታለን፡፡››
‹‹ልቀልድ ብዬ ነው እንደፈለግሽ››
///
አሁን ልክ ከቀኑ 11 ሆኗል ፡፡እናም ሲፈን ሶስተኛው ቀጠሮዋ ላይ ተገኝታለች.፡፡ሄኖክም ከፊት ለፊቷ ተቀምጧል፡፡ይሄኛወ ቀጠሮዋ ከአጀማመሩም ውጥረት ያለበት ነው፡፡
‹‹ሲፈን እንድንገናኝ ስለፈቀድሽ በጣም ደስ ብልኛል››
‹‹የግድ ስለሆነ ነው የተገናኘነው››መለሰችለት፡፡
‹አዎ…የግድ ነው…በጣም ብዙ ጠብቄያለው…በመራራቃችን በመከከላችን ብዙ ብዙ ችግሮች ተፈጥረዋል…አሁን ግን ያን ሁሉ ከኃላችን ጥለን ቁስለታችንን በማከም ወደፊት መቀጠል ነው ያለብን፡፡››አለ ምን ትመልስልኝ ይሆን በመሚል ፍራቻ ፈራ ተባ እያለ..
‹‹ትክክል ብለሀል…አሁን በትክክል አድምጠኝ ፤እኔ ላለፈው ጥፋትህ ማለቴ በእኔ ላይ ለሰረሀው በደል ሁሉ ይቅር ብዬሀለው .አንተም ያስቀየምኩህ ነገር ካለ ይቅር እንድትለኝ እፈልጋለው፡፡››
1.4K viewsTsi B, 16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 19:58:18 ነፍስ ስታፈቅር
ምዕራፍ -24

ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ


///

የቢላል ህይወት ካለፈ 15ቀን ቢያልፈውም ሲፈን ግን ዛሬም ወደቤቷ አልተመለሠችም።ወላጆቾ ቤት እዛው ክፍሏ ነው ያለችው።ይህ የሆነው ከደረሰበት የሀዘን ስብራት አባቷ እንዲያፅናናት ወይም እናቷ ጉያቸው ሸጉጣ ተስፋ እንዲሰጧት ፈልጋ አይደለም።እዛ ቤት የመሸገችበት ብቸኛው ምክንያት ክፍሏን ፈልጋ ነው ።እዛች ክፍል ውስጥ ቢላል ከ20ቀን በላይ ኖሯል...በሰፊው አልጋ ላይ ከዳር እስከዳር ተንከባሎበታል..እያንዳንድን የክፍል ወለል እየደጋገመ ረግጦታል ፤በሻወር ቤቱ ደጋግሞ ተጠቅሞል....የጠጣባቸው ብርጭቆዎች፤ የተመገበባቸው ሳሀኖች ፤እዛ ክፍል ይገኛሉ።እያንዳንድንን ቢጃማዎን ፤ሠፋፊ ቀሚሶቾን :ቲሸርቶቾን እየቀያየረ ለብሶቸዎል..።አሁንም ሙሉ ክፍሉ..እጅ ያረፈባቸው እቃዎች በጠቅላላ የእሱን ጠረንና ትዝታ አዝለዎል..እና የእሷ እዛ ክፍል በራሷ ላይ ጠርቅማ ስትተክዝና ስታልም መዎል ምክንያቱ ይሄ ነው።

ይሁን እንጂ ጉዳዩ ቤተሠቦቾን በተለይ አባትዬውን ክፍኛ አሳስቧቸዎል።እና ዛሬ ሊያናግሯት ወስነው ክፍሎ ድረስ መጥተዎል።

"ልጄ...አይበቃም...እስከመቼ እራስሽ ላይ ዘግተሽ?"
‹‹አባ አንድ ክፍል ውስጥ ታፍኖ መቀመጥን አንተ እኮ ነህ ያስጀመርከኝ..."
"ለአንቺው አስቤ እኮ ነበር ...ይገድላታል ብሎ ሄኖክ ሲያስፈራራኝ ምን ማድረግ ነበረብኝ...?"
"ቢሆንም የእኔንም ፍላጎት ከግምት ልታስገባ ይገባ ነበረ....ከማታውቀው ሰው ምክር ከመቀበል ይልቅ እኔ ልጅህን ብትማከር ይሻል ነበረ"

‹‹"እሱስ እውነትሽን ነው ...እንደዛ አድርጌ እራሱ መች አዳንኩሽ...እንደው ልጅ እግዚያብሄር ይባርከውና እንደተባለው አድርጎ ቢሆን ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር...?እኔ ያቆምኮቸውን ወጠምሾች አልፎ ክፍልሽ ገብቷል..ከመግባትም ለቀናት ኖሯል....እና እዛው በገዛ ክፍልሽ አንቆሽ ቢሆን ኖሮ...አረ በስመአብ.."ግሽግሽ አሉ፡፡

" ....ግን አላደረገውም...በጣም ስለሚያፈቅረኝ ምን አልባት በበሽታው ተፅዕኖ አንድ ቀን እንዳይገድለኝ በመፍራት ብቻ ቀድሞ እራሱን አጠፋ...ከራሱ ሊጠብቀኝ እራሱን ገደለ ፤ይሄንን ሰው ነበር ሁለታችሁም ስታሳድዱት የከረማችሁት››

"አዎ ልጄ ትክክል ነሽ አጥፍተናለ..ብቻ ነፋሱ በአፀደ ገነት ትረፋ.."

ረጂም ዝምታ.....
"ልጄ"
"አቤት አባዬ"
"አንድ ሌላ ነገር ልነግርሽ እፈልጋለው..."አሉና እጃቸውን ወደጃኬት ኪሳቸው በመስደድ አንድ ወረቀት አወጡ....
"ይሄ ያንቺን ጋብቻ በተመለከተ ተዋውለን የነበረ ውል ነው...ቀነ ገደብ ሊገባደድ አንድ ወር ብቻ ነው የቀረው.."

ፊቷን በንዴት አጨማደደች"አባዬ አሁን ስለዚህ ጉዳይ ለማውራት አቅሙ የለኝም"

"አውቃለው ልጄ "ብለው ሁለት ቦታ ከዛም አጥፈው አራት ቦታ ቀዳደዱና ወለሉ ላይ በተኑት...ሲፈን በጣም ደነገጠች
"እንዴ አባዬ!! ምን እየሰራህ ነው?"

"ልጄ ሀሳቤን ሁሉ ሰርዤዎለው...በፈለግሽ ሰዓት የፈለግሽውን ማግባት ካለበለዚያም አለማግባት ትቺያለሽ...እኔ ልጄ ደስተኛና ጤነኛ ብቻ እንድትሆን ነው የምፈልገው....ካንቺ የሚበልጥብኝ ምንም ነገር የለም"አሉና ከመቀመጫቸው በመነሳት ግንባሯን በመሳም ወደ ውጭ መራመድ ጀመሩ።

"አባዬ..በጣም ነው የማመሠግነው..ደግሞ ቃል ገባልሀለው…በጣም በቅርብ አስደሳች ዜና አሰማሀለው"አለች ሆዷን በቀኝ እጇ በስሱ እየዳበሰች።
"ይሁን ልጄ..ይሁን...በእኔ በኩል ምንም ብታደርጊ ቅሬታ የለኝም ...ለሁሉም ነገር ከልቤ መርቄሻለው... ደህና ሁኚልኝ..."ወጥተው ሄድ።
///
በማግስቱ…..
በጥዎት ነው ከእንቅልፏ የተነሳችው፡፡ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ቀለል ብሏታል።አዎ በሀዘን የጎበጠ ትከሻዎ ቀና ማለት ፤የደፈረሱ ዓይኗቾ መጥራት፤ የተሠነጣጠቀ ልቧ ክፍተቱን ማጥበብ ጀምሮል ...ለዚህ ደግሞ የሄኖክ አባት ድርሻ ቀላል አልነበረም....ቢላል ከሞተ ብኃላ በራሷ ፍላጎት ስልክ አንስታ በመደወል የምታዋራቸው ብቸኛ ሰው ናቸው።እና በደወለችላቸው ጊዜ ሁሉ ከልስልስ አንደበታቸው እየሾለኩ በጆሮዎ የሚሰርጉ የምክር እና የማፅናናት ቃላት በትክክል ልቧ ላይ እያረፉ ሲቀልጡና ከሰውነቷ ሲዎሀድ ይታወቃት ነበር...በዛ ላይ በየሰዓቱ ልዩነት በሚሴጅ የሚልኩላት አጫጭር መልዕክቶች ለተሠበረ መንፈሶ መታሻ ቅባቶች ሆነውላታል።

ዛሬ ግን ከእሷቸው ጋር የምሳ ቀጠሮ አላቸው።ከሁለት ወር ብኃላ ነው በአካል የሚገናኙት።ከዛ በፊት ግን ቀርስ ላይ ከፕሮፌሰሯ ጋር ለመገናኘት ወደ ቤቷ ትሄዳለች..ስለልጅ ልጇ ማውራት ፈልጋለች.በዛ ላይ አራት ሰዓት አብረው ሀኪም ቤት ይሄዳሉ የፅንሱን ጤንነት ለማወቅ.፡፡..የዛሬዎ ቀጠሮ በዚህ አያበቃም 11ሰዓት ደግሞ ከሄኖክ ጋር ትገናኛለች።ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ፊት ለፊት አግኝታው ስለወደፊታቸው እልባት ለመስጠት ስለፈለገች ነው ላግኝህ ያለችው፡፡እሱም በደስታ እየፈነጠዘ ነበር ቀጠሮውን የተቀበለው፡፡

ብቻ ዛሬ ህይወቷን አዲስ አቅጣጫ የምታሲዝበት ቀን ነው።ለዚህ ደግሞ በዙሪያዋ በአውንታም ሆነ በአሉታ ተፅዕኖ ያላቸውን ሰዎች የምታናግረውን አናግራ የምታማከረውን አማክራ የመጨረሻ የመፍሰሻ አቅጣጫዎን ትወስናለች።
///
ወደኘሮፌሰሯ ቤት እየሄደች ሳለ ቤቷ ጋር ስትደርስ መኪናዋን አቆመችና ክላክሱን አንጫረረች…ተዘራ በራፉን ከፈተና ዱላውን እየወዛወዘ ወደእሷ ቀረበ…

"እንዴ እትይ ..እንደው ለመሆኑ ሰላም ነሽ.?.ስልኪቱን ብደውልም እኮ አታነሺም››
‹‹ምነው ችግር ነበረ እንዴ?››አለቸው በመስኮት አንገቷን አውጥታ እጇን ወደእሱ በመሰንዘር እየጨበጠችው፡፡
‹‹ኸረ እዚስ ሰላም ነው...ግን እትይ የአንቺ ነገር በጣም አሳስቦኝ ነው?"
‹‹እኔ ሰላም ነኝ...ከሳምንት ብኃላ ሙሉ በሙሉ ወደቤቴ እመለሳለው"
"ውይ እትዬ እባክሽ ተመለሽ...እባክሽ...መሽቶ ከልነጋ አለኝ እኮ...እንደው እትዬ አትታዘቢኝና በራፍ ከፍቼልሽ ስትገቢና ስትወጪ የምምገው ሽቶሽ እራሱ ናፈቀኝ ልሞት ነው››...ፈገግ አለች"ምን አለ ሰው ሁሉ እንደአንተ የዎህ ቢሆን? አለች በውስጧ
‹‹ደሞዝ ገብቶልሀል አይደል?"
‹‹አይ እትዬ ...አዎ ገብቶልኛል...አንቺ ጋር እየሠሩ የብር ችግር የት አለ..?.ብቻ አንቺ ሀዘኑን በልክ አድርገሽ ..ቃል እንደገባሽው ወደቤትሽ ቶሎ ተመለሺ"
‹‹እሺ ..አሁን ቸው..."መኪናዎን አስነስታ ሄደች።
///
ፕሮፌሰር ቤት ስትደርስ 3 ሰዓት ሆኖ ነበር።እንደምትመጣ ስለሚታወቅ ጠረጰዛው በምግብ ተሞልቶ ነበር የጠበቃት።አቀባበላቸው ደማቅ፤ መስተንግዶቸው ልብ ሚያሞቅ ፤እንክብካቤያቸው ልክ እንደንግስት ነበር.፡፡
.ከቁርስ ቡኃላ ሁለቱም ሳይነጋገሩ ተያይዘው ቢላል ክፍል በመግባት ዕቃዎቹንና ስዕሎቹን እያዩና እዳበሱ ሲያለቅሱ እና እርስ በርስ ሲፃናኑ አረፈዱ.፡፡በመጨረሻም አንድ የተቀደሰ ሀሳብ በሁለቱም ተከሰተላቸው .በእምሮ ህመምተኞች ላይ የሚሰራ ፋውንዴሽን በስሙ ለማቋቋምና በዛ ፋውንዴሽንም ስራዎቹን ቋሚ ስፍራ እንዲያገኙ ለማድረግ አብረው ሊሰረሩና ሙሉውን ወጪ የሲፈን ካማፓኒ ሊሸፍን ተስማሙ፡፡በዚህም ሁለቱ ከብዙ የሀዘን ቀናት ቡኃላ ደስ ተሰኙ፡፡.አምስት ሰዓት ሲሆን አብረው ሲፈን ለፅንሱ ክትትል ወደምታደርበት የግል ሆስፒታል ሄዱ፤
1.2K viewsTsi B, 16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 19:59:41 ልብ ወለድ በፅዮን fiction pinned «ሊንኩን ተጭኖ ዩቲዩብ ቪዲዮዉን Like & subscribe አድርጎ ፎቶ አንስቶ(screenshot) ለላከልኝ የመጨረሻውን ክፍል በውስጥ መስመር እየላክሁ ነው። የነፍስ ስታፈቅር ወዳጆች የታላችሁ»
16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 19:59:34 Watch "ድንቅ ተከታታይ የልብ ወለድ ትረካ / ያበደው ፍቅሬ / ፀሀፊና ተራኪ ፅዮን በየነ" on YouTube

1.4K viewsTsi B, edited  16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 19:57:57 Watch "ድንቅ ተከታታይ የልብ ወለድ ትረካ / ያበደው ፍቅሬ / ፀሀፊና ተራኪ ፅዮን በየነ" on YouTube


1.3K viewsTsi B, 16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 19:52:49 ..ልጄ ፍፀም ልዩ ሰው ሆኖ ነበር የመጣው.ያው ታውቃለህ የእምሮ በሽተኛ ስለሆነ ሁኔታው ሁሉ ወሰድ መለስ ነበር የሚያደርገው...በዛን ቀን ግን እንደዛ አልነበረም….መልኩ ጥርት ያለ …አለባበሱ ጠርት ያለ…ንግግሩ ጥርት ያለ ነበር…፡፡ተደሰትኩ፤ተስፋ አደረኩ፤ጓጓው…በውስጤ ለአንድ ሺ ጊዜ ደጋግሜ ፈጣሪን አመሰገንኩ…ልጄ ሙሉ በሙሉ እየዳነልኝ ነው አልኩ….በደስታ እየተጫወተንና እየተቃለድን ቁርስ በላን..እማዬ ጸጉርሽ ተንጨብርሯል አለና ፀጉሬን ፈቶ ሲያበጥርልኝ ..መልሶ እየጎነጎነ ሲሰራልኝ …አቤት የተደሰትኩት መደሰት.ለካ እሱ እየተሰናናተኝ ነበር.ለመቸረrሻ ጊዘዜ ሰውነቴን እዳበሰኝ ነበር…የልጅ እጅ ሰውነትህ ላይ ሲያርፍ የሚሰማህን ስሜት ታውቀዋለህ…?በምንም ሊገለፅ የማይችል ልዩ ነው....እንደዚህ እንደዚህ እያልን አምስት ሰዓት ተኩል ሆነ፡፡
‹‹.ከዛ በቃ እማዬ ክፍሌ ናፍቆኛል ››አለኝ
‹‹እሺ ግባ እኔም እስከዛ ቆንጆ ምሳ በራሴ እጅ ሰራልሀለው›› አልኩና እሱን ወደክፈሉ ሸኝቼ ወደኪችን ገባው፡፡ ከዛ ሚወደውን ምግብ ሁሉ አንድ ሳላስቀር ሰርቼ ጠረጳዛውን ሞላውና ወደክፍሉ ሄጄ አንኳኳው መልስ የለም…እስኪደክመኝ አንኳኳው ‹እንቅልፍ ወስዷት ይሆን?› የሚል ጥርጣሬ ገባኝ…‹‹እንደለመደው ወጥቶ በመሄድ ጠፈቶብኝ ይሆን? ›ስልም ተጠራጠረርኩ…ቁልፍ አስመጣውና ከፍተን ስንገባ ..ልጄ በሰማያዊ ሲባጎ እራሱን አንጠልጥሎ በድኑ በአየር ላይ እየተሸከረከረ ነበር፡፡
ማንኛዋም እናት በእኔ የደረሰው ሀዘን አይድረስባት…ያው አሁን እኔም በህይወት መኖሬን እርግጠኛ አይደለውም…ውስጤ ደክሟል..ተስፋዬ መክኗል…ለህይወት ያለኝ ጉጉተት ጠፍቷል..የምበላው ምግብ ጨው ይኑረው አይኑረው እራሱ መለየት ትቼያለው…የምጠጣው ውሀ ይሁን በረኪና ግድ አይሰጠኝም…የዩኒቨርሲተ አስተማሪ ልሁን የፅዳት ሰራተኛ እርግጠኛ አይደለውም…ፕሮፌሰር ብለው ሲጠሩኝ እራሱ ማንነው? ብዬ መደንገጥ ጀምሬያለው..እኔ ይሄ ሁሉ ቀርቶብኝ እናት ብቻ ነበር መሆን የምፈልገው… የቢላል እናት መሆን…፡የቢላል እናት በሚል በፀጋ በተሞላ አስደናቂ ስም መጠራት.፡፡

ፖሊሱ ራሱ የሁሉቱ ሴቶች ሀዘን በጥልቀት ተጋባበት….ምንአይነት የተለየ ሰው ቢሆን ነው በዚህ መጠን ይወዱት የነበረ…?ሲል በውስጡ አሰበ….ከመሳቢያው ኪስ ውስጥ አንድ ወረቀት አወጣና ጠረጳዛ ላይ አሰቀመጠ….እና በሁለቱ መካከል ገፋ አደረገና አስጠጋላቸው.ሁለቱም እርስ በርስ ተያዩ
‹‹…ምንድነው ኢንስፔክተር?›ሲፈን ነች ጠያቂዋ
የቢላልን ክፍል ስንመረምር ያገኘነው ነው…ለሁለታችሁ ከመሞቱ በፊተ የተወላቸሁ መልዕክት ነው.፡
ሲፈን በፍጥነት አፈፍ አድርጋ አነሳችው….ድምፃን ከፍ አድርጋ ማንበብ ጀመረች፡፡

I hope you are blessed
With a heart like a wildflower
Strong enough to rise again
After being trampled on
Tough enough to weather
The worst of the summer
and even able to grow and flowrish
In the most broken of places
//
ማን ነበር እነዚህን የሀዘንና የተሰፍ እንጉርጉሮ ያንጎራጎረው.?.እኔ እንጃ ተረሳኝ/እማዬ….አንቺ የአለሞ ቁጥር አንድ እናት ነሽ...በጣም ነው የምወድሸ….ጤነኛም ስሆንም እዕምሮዬም በተቃወሰ ጊዜም ጭመር አንቺን ባለመቋረጥ እወድሻለው…እናም ደግሞ ከሞትኩ ቡኃላም እንደምወድሽ እንዳትጠራጠሪ፡፡ደምፅሽ እያወራሽኝ ሁሉ ይናፍቀኝ ነበር፤.ጠረንሽ ጉያሽ ተሸጉጬ እራሱ እራበዋለው…እማዬ ጥዬሽ ስለሞትኩ በጣም አዝናለው….ግን የግድ ማድረግ ስላላብኝ ነው፡፡አዎ በፍጥነት ውሳኔ ወስኜ እራሴን ካላጠፋው የምወዳትን ልጅ አጠፋለው….እሷን ገድዬም ደግሞ ብተርፍ አንድ ነገር ነበር …..ከገደልኮት ቡኃላ ደግሞ እራሴን ማጥፋቴ የማይቀር ነው..ሁለት ኪሳራ.፡፡..እና እማዬ ይቅር በይኝ…
ሲፈን ….አንቺ በነፍሴ የማፈቅራት ልዩ ሴት ነሽ….በጣም ልዩ ሴት..፡፡በንግግርሽ በጣም ከመደንዜ የተነሳ የእውነትም አንቺን ስለማግባት እያሰብኩ ነበር…ቃል እንደገባሽልኝ ገነት መሳይ በተፈጥሮ ያሸበረቀች ልዩ የብቻችን ቦታ ወስደሺኝ .እዛ ጎጆችንን ቀልሰን ..ልጆቻችንን ወልደን….ብርቱካንና መንጎ ከጎሮ እየቀነጠስና…ጥልል ባለ የወንዝ ውሀ ገላችንን እየታጠብን …በዝሆንና ቀጪኔ ጀርባ ላይ ሰርከስ እየሰራን..ብዙ ብዙ ነገር እንዳልም አድርገሺኛል….
ግን አንዳንዴ መራር ቢሆን እውነታን መጋፈጥ የጀግኖች ባህሪ ነው.እና እኔም ጀግና መሆን ወሰንኩ…፡፡ለአንቺ ህይወት የሚበጀውን ዘላቂ ነገር ማስብ እንዳለብኝ ወሰንኩ…አንቺን አንቄ ከመግደሌ በፊት እራሴን ማንጠልጠል እንዳብኝ ወሰንኩ…፡፡.እንደዛ ያደረኩት ለአንቺ አስቤ አይደለም፡፡.ጥዬሽም ለመሄድ አንጀቴ ጨካኝ ሆኖ አይደለም…አብረን ብንሞት እና አንድ መቃብር ብንቀበር ደስ ይለኝ ነበር…ግን እንደዛ ማደርረግ አልቻልኩም .፡፡ለምን? ለልጃችን ስል፡››
.ማንበቧን አቋረጠችና አንዴ ፕሮፌሰሯን አንዴ ኢንስፔክሩን እያፈራረቀች ተመለከተች‹‹..የምን ልጁ?››
ፕሮፌሰሯ ትከሻዋን በመነቅነቅ ‹እኔ ምን አውቄ ›የሚል መልስ ሰጠች..
እንስፔክተሩ ‹‹ማንበብሽን ቀጥይ ›› አለት
ማንበብ ቀጠለች…
‹እማዬ እና ሲፈን…እድለኛ ከሆንኩ አንድ የምስራች ልንገራችሁ…ማለቴ ይሄን ደብዳቤ ከማንባችሁ በፊት በሌላ መንገድ ዜናውን ካልሰማችሁ ማለቴ ነው፤እማዬ ልጅ ትቼልሽ ነው የሞትኩት…የልጅ ልጅ ሊኖርሽ ነው..ሲፈን እርጉዝ ነች የእኔ .ል..ጅ…..አርግዛ..ለች.›
ሲፈን ከመቀመጫዋ ተነሳች..ሆዷን በእጆቾ ዳበሰች..
‹‹ምን ማለት ነው.?››ማርገዜን እንዴት ነው ያወቀው…?እንዴት እንደዛ ሊሆን ይችላል?››
‹‹ምነው? ግንኘነት አልፈፀማችሁም እንዴ…?››ኢንስፔክሩ ነው የጠየቃት
‹‹አይ.. እሱማ ፈፅመናል..አዎ በደንብ ፈፅመናል..ግን ያልገባኝ እኔ ማርገዜን ሳላውቅ እሱ እንዴት..?ደሞ እኮ ምንም አይነነት የእርግዝና ምልክት እየታየብኝ አይደለም››
‹ኢንስፔክተር ይቅርታ አድርግልን ከፈለከን በሚመችህ ሰዓት ተመልሰን መምጣት እንችላለን ..አሁን ሆስፒታል ሄደን ይህንን ተአምር ማረጋገጥ አለብን.››ከመቀመጫዋ ተነስታ ሲፈንን እየጎተተች የኢንስፔክተሩንም ይሁንታ ሳትጠብቅ ይዛት ወጣች፡፡ወደ ሆስፒታል፡
///
አለም በምንም ጉዳይ ላይ ሚዛን የምትጠብቅበት የራስዋ የሆነ ስውር ቀመር አላት…፡፡ገፍትራ ከገደል አፍፍ ላይ ብትጥለንም ስንወድቅ ግን አስከመጨረሻው ተሰባብረን እንዳንደቅ ማረፊያችንን በተደላደለ የሰንበሌጥ ሳር አልብሰሳ ትጠብቀናለች ፡፡ድንገት ሳናስበው በአስፈሪ የአዞ አፍ ተሰልቅጠን ብንዋጥም ሆዱን ሰንጥቀን አረሳችን ነፃ የምናወጣበት ጩቤ ከጎናቸን እናገኛለን፡፡
ቢላለ በምን አይነት ተአምር እንዳወቀ ለሁለቱም እንቆቅልሽ ቢሆንባቸውም በምርመራ እንዳረጋገጡት ሲፈን የሶስት ሳምንት እርጉዝ ነች፡፡አዎ ከጭለማ ቡኃላ ብርሀን ይፈነጥቃል..ከምሽት ብሃል ንጊት አይቀሬ ነው….ከስቅለት ቡኃላ ትንሳኤም የሚጠበቅ ነው…በሁለቱ ሴቶች በሀዘን የደቀቀ ልብ ውስጥ የሆነች ብጣቂ ተስፋ ለመነቃቃት ስትንፈራገጥ ትታያለች፡፡

ሊያልቅ አንድ ክፍል ብቻ ይቀረዋል

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
1.3K viewsTsi B, edited  16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ