Get Mystery Box with random crypto!

በህይወት መንገድ ላይ…… ( ታጋቾቹ) ምዕራፍ-አንድ (በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ) /// እኛ የዘላለም ተ | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

በህይወት መንገድ ላይ……
( ታጋቾቹ)
ምዕራፍ-አንድ
(በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)
///
እኛ የዘላለም ተጓዦች ነን…..ለዘላለም በሁለንተና ውስጥ ቅርፃችንን እየቀያርን ከአንዱ አፅናፍ ወደ ሌላ አፅናፍ እየተላጋን የምንኖር ተንከራታች እና ተቅበዝባዥ ፍጡሮች፡፡ይህ ታርክ ግን ስለዘላለም አይደለም የሚተርከው… ስለቅፅበት ነው፡፡ሰው ተብለን ከተፈጠርንበት ሬሳ ተብለን እስከምንሸኝበት ስላለችው ቅፅበት አንድ ነጠላ ታሪክ ነው…..ከዛ በፊትም ሆነ ከዛ ቡኃላ ስላለው ብዙም እውቀቱ ስለሌለን ብንናገርም መቀባጠር ብቻ ነው የሚሆንብን፡፡
ተወልደን ወደሞታችን እየተጎዝን ነው፡፡በእያንዳንዱ ቀን ተኝተን ስንነቃ ከበላያችን የተሰቀለውን የሞት ቅርንጫፍ ዘንጥለን ወደገደሉ ለመሽቀንጠር እየተንጠራራን…. በተንጠራራንበት ቅፅበት ሁሉ የሆነች መጠን ወደቅርንጫፉ እየቀረብን ነው፡፡ግን ይህን ለማሰብ ዳተኞች ነን፡፡ስለዚህም የዘላለማዊነትን ምኞት በጭንቅላታችን ጠቅጥቀን ትርምሱ ውስጥ ገብተን እንንቦራጨቃለን….ማግበስበስ ውስጥ እንዳክራለን…..ትንፋሽ እስኪያጥረን ብኩንና ተቀበዝባዥ እንሆናለን፡፡በዛም የተነሳ መንገዳችንን ለመመርመርና ለማጣጣም እድል አይኖረንም….ጉዞችን የእውር ድንብር እይታችንም በደመነፍስ ነው፡፡እኔም ያው ሰው ነኝና እንደዚሁ ነበር ጉዞዬ…

እድሜዬ ሰላሳ ስድስት ሆኖታል፡፡ይህን ያወቁት እንግዲህ ከልደት ሰርተፍኬታ ላይ መነሻውን በመውሰድ እስከአሁን ያለውን ዓመት ቆጥሬ ነው፡፡..የፀሀይ መውጣት እና መጥለቅ ከሰው ልጅ መወለድና መሞት ጋር ይመሳሰልብኛል፡፡የፀሀይ መውጣት ከመወለድ ጋር የፀሀይ መጥለቅ ደግሞ ከመሞት ጋር፡፡

ፀሐይ ወጣች ስንል ተፈጠረች ማለታችን ሳይሆን ለእኛ እይታ ተከሰተች ብርሀኗ እና ሙቀቷ ምድራችን ጎበኛት ማለታችን ነው እንጄ ከመውጣቷ በፊተ ባለው ለሊት የለችም ማለት አይደለም በትክክልም አለች፡፡አንድ ሰውም ተወለደ ስንል ከመወለዱ በፊት የለም ማለት አይደለም በሌላ ዓለም በሌላ ቅርጽ ወይም በማንገምተው ህልውና ነበር..(ምክንያቱም እግዚያብሄር የሰውን ልጅ አንድ ቀን አንድ ላይ ነው የፈጠረው..)ሲወለደ በዚህ ምድር ተከሰተ ማለታችን ነው እንጂ ስለመፈጠር ማውራታችን አይደለም፡፡ፀሀይ የቀን ውሎዋን አጠናቃ ስትጠልቅም ከሰመች ጠፋች ማለታችን አይደለም….ከጠለቀችም ቡኃላ ከነምሉዕነቷ መኖሯን እንደምትቀጥል እናምናለን እናውቃለንም ፡፡ ሰውም ሞተ ስንል ነፍሱ ከምድር ህልውና ተነጠለች፤ ጊዜያዊ ቆይታዋንም አጠናቀቀች ማለታችን እንጄ ጭሩሹኑ ወደአለመኖር ተሸጋገረች ከሰመች ማለታችን አይደለም፡፡

ያው እንደነገርኮችሁ እድሜዬ 36 ነው ፡፡ግን ደግሞ እድሜ እንደዛ አልነበረም መቆጠር ያለበት….በህይወታችን እርባነቢስ ሆነው ዝም ብለው የሚያልፉ ትርጉመቢስ የሆኑ ቀናቶች፤ ሳምንታቶች እና አመታቶች አሉ..አሁን እነሱ ከእድሜያችን ተደምረው እንደኖርንባቸው መቆጠር ነበረባቸው?፡፡ደግሞ አንዳንድ ጊዚያቶች አሉ አንፀባራቂና ወርቃማ የሆኑ…ማንነታችንን የሰራንባቸው፤ ለነፍሳችን መዝናኛ በአበባ ያጌጠ አፅድ ፤ በፍራፍሬ የተሞላ ጋርደን ማዘጋጀት የቻልንባቸው፤ ጥቂት ግን ደግሞ በተደራራቢ ድርጊት የተሞሉ..በመከራና አሰቃቂ ድርጊቶች የታጠሩ…ተስፋ በማስቆረጥ እና መልሰው ደግሞ ብጣቂ ተስፋ በመስጠት በህይወት ዥዋዝዌ እያላጉ እያፈረሱ መልሰው የሚሰሩን …ለዘመናት የገነባነውን መኮፈሳችንን የሚቦረቡሩ….ኩራታችንን ከአመድ ሚደባልቁ….የማናውቀውን እራሳችንን የሚያስተዋውቁን…በስቃይ እሾህ የታጠሩ ግን ደግሞ ፍሬያማ ጊዜያቶች…እና እነሱ ከእድሜያችን ጋ ሲደመሩ በሁለት ሶስት እጥፍ መባዘት አልነበረባቸውም….?
እና ለዚህ ነው እድሜዬን ሲጠይቁኝ ስንት ማለት እንዳለብኝ ግራ የሚገባኝ፡፡ለማንኛውም አሁን ስለነዛ በልኬት ጥቂት ግን ደግሞ በተደራራቢ ትንፋሽ አስቆራጭ ድርጊት የታጨቀ ኩነቶች ነው የማወራችሁ..ከዘልዛላው ህይወቴ ላይ ተቦጭቀው በጉልህ ስለሚነበቡ አይረሴ ቀናቶች ፡፡
እለቱ አርብ ነው፡፡ሰዓቱ ደግሞ 12.30 ….ስራ ላይ ነኝ…የስራ ቦታዬ በተፈጥሮ ውበት በደመቀችው የመዲናይቱ አዲስ አበባ ኮረዳ ጎረቤት በሆነችው ቢሾፍቱ ከተማ ነው፡፡
በትክክል ከቢሾፍቱ ከተማ እንብርቶ በሆነው ቢሾፍቱ ሀይቅ ጠርዝ ላይ ነው ያለውት ፡፡ይዚህን ሀይቅ ጠርዝ ታከን እዚህ አስቸጋሪ ገደልና ኮረብታማ ቦታ ላይ አስደማሚ ሪዞልት እየገነባን ነው፡፡በዚህ የሪዞልት ግንባታ ላይ ፕሮጀክት ኢንጂነር ሆኜ በመስራት ላይ እገኛለው፡፡ ስራ ከጀመርኩ አመት ከስድስት ወር ሆኖኛል፡፡ፕሮጀክቱ በሁለት ፌዝ የሚገነባ ሲሆን አሁን አንደኛውን ፌዝ ገንብተን ጨረሰን ፊኒሽንግ ላይ ስንሆን አንደኛውን ደግሞ ገና ቁፋሮ ጨረሰን ፋውንዴሽን እየሞላን ነው፡፡አንደኛውን ፌዝ ሰርተን ለማጠናቀቅ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሚባል መስዋዕትነት ከፍለናል፡፡አንድ ሰው ሞቶብናል.ከአራት በላይ ሰዎች በስራ ላይ እያሉ አደጋ ደርሶባቸው አካለጎደሎ ሆነዋል፡፡ሁለተኛውን ፌሰዝ ግን ከመጀመሪያው ያገኘነው ልምድ ቀላል የሚበል ስላልሆነ በዛ መጠን እንደማንፈተን እርግጠኞች ነኝ፡፡
ሪዞርቱ የሚያሰርፍበት ቦታ እጅግ ሳቢና አስደማሚ መልካአምድር ያለበት ቢሆንም ለግንባታ ግን በጣም አስፈሪና ፈታኘ ነው፡፡አሁን የቆምኩበት አለት ላይ ሆኜ ቁልቁል የግዙፍ እስትዲዬም ሜደ የመሰለውን ክቡ ሀይቅ ከነውበቱና አስፈሪነቱ ይታየኛል፡፡፡፡በዚህ ሰዓት ሰራተኛ ሁሉ ወጥተው ሄደዋል…እኔ ፤ የሳይቱ ፎርማኑ ጋሽ አህመድ ፤ዋናው ፌራዩ(የብረት ሰራተኛ) በሪሁን እና ከአመት ቆይታ ቡኃላ ሰሞኑን ከስራ ልትሰናበት በርክክብ ላይ ያለችው እስቶር ኪፐሯ አይዳ እና እሷን ተክታ ሰሞኑን የተቀጠረች አንድ ለጊዜው ስሞን የማላውቃት ልጅ ነን በሳይቱ ውስጥ ያለነው፡፡ ፡፡ሰራተኛ ከወጣ ቡኃላ ወደኃላ ቀርቶ በእለቱ የተሰራውን ስራ ማየት የዘወትር ልምዴ ነው፡፡ሳይቱ ከግርግር ነፃ ከወጠ ቡኃላ በስክነት የእለቱን ስራ ማየት..በእለቱ የተሰራውን መልካም ስራና የጠፋና የተበላሸም ካለ ግልፅ ሆኖ ስለሚተይ የሚቀጥለውን ቀን ፐሮግራም ለመከለስ ከፍተኛ እገዛ ያደርግልኝል፡፡
ነገ ኮንክሪት ለመሙላት የተዘጋጁ አስር የሚሆኑ footing ስላሉ ዛሬውኑ የብረት ስራቸው በትክክል በዲዛይኑ መሰረት መቀመጣቸውን እያረጋገጥን ነው፡፡
አና እንደተለመደው ከአንዱ ኮረነር ወደሌላወ ኮርነር እየተዘዋወርኩ በመመልከት ላይ ሳለው ከኃለዬ ድምፅ ሰማው
‹‹…አንጂነር የምትፈልገው ነገር አለ..?ልወጣ ነበር ››አለችኝ..አዲሶ እስቶር ኪፐር
‹‹ቆይ ትንሽ ጠብቂንና መኪና ስለያዝኩ እሸኝሻለው….እነበሪሁንም አሉ አንድ ላይ እንሄዳለን…. አንድ 10 ደቂቃ ጠብቂን…እሷ ግን መሄድ ትችላለች››አልኳት..አይዳን ማለቴ እንደሆነ ሁለቱም ገብቶቸዋል፡፡እሷ.እንድትቆይ የፈለኩት ምን አልባት ከስቶር የምንፍልገው እቃ ይኖራል የሚል ግምት ስለወሰድኩ ነው፡፡
‹‹እሺ …እጠበቅሀለው››አለቺኝ
‹‹እኔም እሷን እጠብቃለው…..ሆሆይ ከስራ ሰዓት ውጭ እህቴን ሶስት ወንዶች መካከል ትቻት አልሄድም…..ምን ይታወቃል››አለች አይዳ..እንግዲህ ነገር እየፈለገች መሆኑ ነው……ከስራ የለቀቀችው እሷ ፈልጋ ሳይሆን እኔ አባርሬያት ነው….ለምን የሚለውን ሌላ ጊዜ ነግራችሆነው..እሷም ታዲያ አሁን በዚህን ሰዓት እዚህ ሳይት ላይ የተገኘችው ከአስራአምስት ቀን በፊት ስለተዋወቀቻት ሴት ደህንነት ተጨንቃ ሳይሆን እኔን ምቾት ለመንሳትና ለማበሳጨት ነው…አዎ አይዳ እንዲህ ነች፡፡የተናረችውን እንዳልሰማው ሆኜ ትኩረቴን ወደስራዬ መለስኩ፡፡