ጉብኝቴ አጠናቅቄ መጨረሻ አካባቢ አንድ ተቀፍሮ ለነገ የተዘጋጀ ብረት ብቻ የታሰረበት Footing ጋር ደረስኩ…..ስመለከተው አሰራሩ የተወታተፈና ሴንተሩን ያልጠበቀ ሆኖ ታየኝ፡፡በርቀት ላይ ስራ ሲሰሩ የነበሩትን ጋሽ አህመድንና በሪሁንን ጠራዋቸው….ቦታውን በደንብ ለማየት ጨለም ስላለኝ እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም… ‹‹ማነሽ እህት…ማን ነበር ስምሽ.እስኪ ባትሪው ይዘሺልኝ ነይ›› ‹‹የትኛውን?› ‹‹አንዱን… ደህና የሚያበራውን›› ‹‹እሺ›› ብላ ቆርቆሮ በቆርቆሮ ወደ ተሰራው እስቶር ሮጣ ሄደች...በፍጥነት በግራዋ አንድ ባትሪ በቀኞ ሌላ ባትሪ ይዛ መጣች፡ ሁለቱንም ተራ በተራ እየሞከረች ‹‹የትኛውን ልስጥህ ››አለቺኝ…..በዚህን ጊዜ በሪሁንና ጋሽ አህመድ መጥተው ስድስት ሜትር የሚረዝመው ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ነበር…አይዳ ደግሞ ከልጅቷ ጎን ልክ እንደጋርድ ተገትራ ቆማለች፡፡እኔ የጉድጎዱ ከንፈር ላይ ቆሜ አንዱን ባትሪ ከልጅቷ ተቀበልኩና እታች ላሉት ለማቀበል ሞክር ጀመር… እሷም እንደእኔው የጉድጓዱ ከንፈር ጋር ቆማ ሁላችንም እንዲታየን ወደታች ማብራት ጀመረች፡፡ አያችሁ እዛ ጋር ያለው ኦቨርላፕ ትክክል አይመስለኝም..እስቲ ቼክ አድርጉት …››ላስረዳቸው ገና ስጀምር ….የቆምንበት አፈር የመንሸራተት ስሜት አሳየ.. እርስ በርስ ተያይተን ሌላ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የማሰቢያ ጊዜ ከማግኘታን በፊት ከእኛ ውጭ ያለ ከጥልቁ ሲኦል የተላከላ የሚመስል ኃይል ጎትቶ እንደጨመረን አይነት እግራችን ከዳንና ወደጉድጎዱ ተስፈንጥረን ገባን… እንግዲህ የጉድጎዱ ጥልቀት ስድስት ሜትር ከሰላሳ ነው…. የሚቀበለን እንደአልጋ የተረበረበ ባለ 32 ዲያሜትር የአርማታ ብረት ንጣፍ እና ብረቱን ዙሪያውን አቅፎ የያዘው ወፍራም ፎርምወርክ (ጣውላ )ነው….ወይንም እድለኖች ከሆን ከታች ጉድጓድ ውስጥ ስራ ላይ በሚገኙትን ጋሽ አህመድ ና በሪሁን ጭንቅላት ላይ እናርፋለን…..እኛ ከከባድ ጉዳት እንተርፋለን…እነሱ ደግሞ ምን አልባት አንገታቸው ይቀነጠሳል፡፡ ስንት ሜትር ላይ እንደሆነ አናውቅም አዲሷን እስቶርን ኪፐር በአንድ እጄ በሌላ እጄ ደግሞ የአይዳን ቀሚስ ጨምድጄ ይዤ ነበር … ..በዛ ጭንቅ ላይ ሆኜ ‹‹አሁን እንዲሀ አንድ የተከበርኩ እና የተፈራው ፕሮጅት ኢንጂነር በሁለት ሴቶች መካከል ተጣብቄ ያየኝ ሰው ምን ይላል…?›› እያልኩ አስባለው ፡፡ …አዲሶ ልጅ . ኢየሱስ ድረስልኝ….ኢየሱስ ድረስልኘ.. እያለች ትጮኸለች ከበታቻችን‹‹ አላዋክበር …አላዋክበር….››የሚል ድምፅ ይሰማኛል…….ጋሽ አህመድ መሰለኝ .በጉጉት ወደሚሄድበት ሽርሽር ቦታ ለመድረስ እንደጎጎ ህፃን