Get Mystery Box with random crypto!

የመዝጊያ መልዕክት ከ #እረኛየ!!! ይገርማል ሁሌም ድክም ብሎኝ ስቀር ምርኩዝ ይልክልኛል፤ አንቺ | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

የመዝጊያ መልዕክት ከ #እረኛየ!!!

ይገርማል ሁሌም ድክም ብሎኝ ስቀር ምርኩዝ ይልክልኛል፤ አንቺም የበቃልዬ ምርቃት ይድረስሽ ሲል ምርኩዝ አርጎ አመጣሽ። በቃልዬ አብነትን የመረቃትን ሰምተሻል? "እውቀት እንደ ምንጭ ይፍለቅብሽ፣ እንደጅረት ወርዶ ለዓለም ሁሉ ይድረስ ብሎ ነው የመረቃት" ። ለአንቺም ከምርቃቱ ይድረስሽ። አሜን፤ ጎሽ ልጄ አዎ፤

እማማ እንመለስ? ደከመዎት?
አየ ልጄ መመለስማ የለም፤ ወደኋላ ዞሬ መመልከቴ ከመነሻየ ምን ያህል ርቀት ተጉዤ እንደመጣሁ ለማወቅ፣ ወደፊት ለመጓዝ ተስፋ እንዲሆነኝ ነው፤ መመለስማ የለም።

ብዙ መከራ አይቻለሁ፣ ብዙ መከራና ስቃይ ፈትኖኛል ልጄ፤ ያኔ ከአበባየ መርገፍ በኋላ ጉልበት ተስኖኝ እቤት ቀርቼ ነበር።

ሰው የጭረት ጠባሳውን እየገለጠ፣ የሌላውን ቁስል እየወጋ፣ በቂም መከፋፈሉን አይታ፣ መቁሰሌ ሌላውን ሰው ወደ ሞት የሚወስድ አይሁን፣ ለእርቅና ለይቅርታ ይሁን ብላ የመንደሩን ሰው በአደራ መራችው። ወደኋላ መመለስ የለም ብላ ሁሉን በአንድነት አስተሳስራ የኔ ልጅ ወደፊት መራችው። ለወደደችው፣ ላመነችበት ዋጋ ከፈለች፤ ዋጋ ከፈለች እኔ ግን እሷ የከፈለችውን ዋጋ ከንቱ ለማስቀረት እቤቴ ቁጭ አልኩ፣ እቤት ቀረሁ፤ ግን ትውልድ አይጥፋ፣ ተስፋ አይጥፋ ይሄው አንቺ መጣሽልኝ እና ምርኩዝ ሆነሽ ይዘሽኝ ወጣሽ።

ዛሬ እግሬ እንዲቀጥልና እንድበረታ ያጸናኝ ተስፋ ነው።

የኔ ልጅ በዚህ እድሜሽ የደረሰብሽን እናትሽን ማጣትሽን ሰምቻለሁ ልጄ ግን ወደኋላ መመልከቱ ምን ያህል ትተሽው እንደመጣሽ ለማወቅ እንጂ ወደኋላ ለመመለስ አይሁን፤ አይሁን ልጄ።

ከመጣንበት ይልቅ ገና የምንሄድበት ብዙ ነው።

አሁን ምንድን ነው የሚመረቀው?
ዛሬ ሸክላ በመስራት ነው የሚያስመርቁት ብለዋል።
ጎሽ ጥሩ አድርገዋል የሰው ልጅስ ከመነሻው እንዲሁ አይደል እንደሸክላ ከአፈር