Get Mystery Box with random crypto!

// 6 ሰዓት ሁለቱም በተቃጠሩት ሆቴል ፊት ለፊት ተቀምጠዎል።እሷ አሁንም ጥቁር በጥቁር እንደለበሰ | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

//
6 ሰዓት ሁለቱም በተቃጠሩት ሆቴል ፊት ለፊት ተቀምጠዎል።እሷ አሁንም ጥቁር በጥቁር እንደለበሰች ነው።ቢሆንም ከሰሞኑ ጉስቁልናዎ ቀስ በቀስ እያገገመች መሆኑን ጠቅላላ ሁኔታዎን አይቶ መገመት አይከብድም...እሳቸው ነጭ በነጭ የባህል ልብስ ለብሰው በቀኝ እጃቸው ነጭ ጭራ ይዘው በሌላ እጃቸው የተንዠረገገ ነጭ ፂማቸውን እያፍተለተሉ ላያቸው የሆነ የመላዕክትን ገፀ_ባህሪ ለመጫወት ዝግጅ የሆነ ባለግርማ ሞገስ ተዎናይ ነው የሚመስሉት።
"ናፍቀሺኝ ነበር...ማለቴ በጣም"
"እኔ ደግሞ ሳዬት ነው ናፍቀውኝ እንደነበር ያወቅኩት"
"ያንን በመስማቴ ደስ ብሎኛል"
"ደግሞም አምሮቦታል "አስባበት ሳይሆን ምላሶን አዳልጧት የተናገረችው ነው።
"ለአንቺ ያለኝን ክብር እንዲያስረዳኝ ነው እንዲህ መዘነጤ ...ለመሆኑ አንቺስ እንዴት ነሽ?*

‹‹ሰላም ለመሆን እየመኮርኩ ነው..ግን ደግሞ በጣም እየናፈቀኝ ነው።"

"አውቃለው… ንግስቴ ጥላኝ ከሄደች ብኃላ እኔሞ በጣም ትናፍቀኝ ነበር።አዎ ናፍቆቱ ስቃይ አለው...ቢሆንም እንድረሳት ስለማልፈልግ ህመሙን እችለዎለው።እንደውም ከቆይታ ብኃላ በናፍቆቱ ምክንያት ልብሽ ላይ የሚሰማሽ ስቃይ ሱስ ይሆንብሻል።..ነገሩ እኔ ካንቺ በተሻለ እድለኛ ነበርኩ››

"እንዴት ጋሼ?"
‹‹ብቻዬን ጥላኝ አልነበረም የሄደችው...ሁለት ልጇቾን ጥላልኝ ነበር የሄደችው ..እነሱም አንድ መፅናኛዎቼ ነበሩ
"ጋሼ"
"አቤት ንግስቴ"
‹‹ለአባቴም ገና ያልነገርኩትን አንድ ዜና ልንገሮት"

"ልስመዎ"

ቀኝ እጇን አነሳችና ሆዶ ላይ አስቀመጠች..አሻሸችው።አይናቸው ተበለጠጠ..‹‹.ምን እያልሺኝ ነው..?
"አዎ ለእኔም ትቶልኝ ነው የሄደው..አርግዤያለው"
‹‹እኔ አላምንም..››ከመቀመጫቸው ተነሱ .ጠረጳዛውን ዞሩና ወደእሷ በመቅረብ አገላብጠው ሳሟት…እሷ እርሷ ማርገዞን የሰማች ቀን በእሳቸው መጠን የፈነጠዘች መሆኗን አታስታውስም፡፡.ወደመቀመጫቸው ተመልሰው ተቀመጡና፡፡
‹‹..እና እግዚያብሄር በፀጋው ዳብሶሻል ማለት ነው?››
‹‹እንግዲህ መሆኑ ነዋ››
‹‹ነው እንጂ…በጣም እድለኛ ነሽ.፡፡በይ አሁን ወደቀልብሽ ተመለሺ፤ የውስጥሽንም ሀዘን ለመቆጣጠር ሞክሪ ፡፡.በማህፀንሽ ለተሸከምሽው በረከት ስትይ…በዛ ላይ የእሱም መንፈስ በቅርብ ሆኖ ያይሻል
‹‹እውነቷትን ነው››
‹‹አዎ ጨክነው ጥለውንማ አይሄዱም…..ልክ እንደከዚህ ቀደሙ ተመልሰው እስኪመጡ ድረስ መንፈሳቸው ይጎበኛናል፡፡
‹‹ለሶስተኛ ጊዜ ተመልሶ የሚመጣ ይስሎታል?፡፡››
‹‹ለሁለተኛ ጊዜ ተመልሶ መምጣቱን አምነሻል ማለት ነው?››
‹‹እኔ እንጃ አርሶ ስላሉኝ ነው…እርሶን ደግሞ አምኖታለው››
‹‹እንግዲያው አዎ አንቺና እሱ የተመቻቸ ዘመን በተመቻቸ ሁኔታ ላይ ተፈጥራችሁ በስርእት መጋባትና በፍቅር አብሮ መኖረ እስክትችሉ ድረስ በተለያየ ትውልድ ደጋግማችሁ ትፈጠራላችሁ...ይህ ነው የእኔ እምነት››
‹‹እኔም እንደዛ ማመን እፈልጋለው›አለች…እውነቷን በውስጧ የሚሰማትን ነው የተናገረችው..አንድ በጣም በነፍስ እንጥፍጣፊ ጭምር የሚያፈቅሩትን ሰው እስከወዲያኛው ለዘለለሙ ነው ያጣውት ቡሎ ማሰብ በጣም ተስፋ አስቆራጭና ጨለማ ሀሳብ ነው..በሆነ ተአምር ዳግም ስጋ ለብሶ በዚህ ምድር ይከሰታል እኔም እንደዛው አደርጋለው...እናም መልሶ በእይታው ለመደንገጥ.. በአይኑ ጥቅሻ ለመቅለጥ..ከዛም በሙቀቱ ለመቃተት እና በፍቅሩ ለመስከር እድል ይኖረኛል ብሎ ማለም ..እጅግ በውስጣችን ብርሀንን የሚረጭ ፋንታሲ ነው፡፡እና እንደዛ ለማመን መንገድ ላይ መሆኗ ተመችቷታል…ምን አልባት ከእሳቸው በላይ የዚህ እምነት ዋና አቀንቃኝ እንደምትሆን ከአሁኑ እየታወቃት ነው፡፡
‹‹ንግስቴ››
‹‹አቤት ጋሼ››
‹‹የዚህ ልጅ የጡት አባት ወይም የክርስትና አባት መሆን እፈልጋለው..ቀሪ ዘመኔን ልንከባከበው እፈልጋለው፡፡የእሷን ልጅ ተንከባክቤ እንዳሳደኩ ሁሉ የአንቺን ልጅ ድንቅ ድንቅ ተረቶች እየነገርኩ ጭንቅላቱን በፍቅር እያሻሸው ማሳደግ እፈልጋለው፡፡አውቃለው ባል ታገቢያለሽ..ባልሽ እንደልጁ ሊንከባከው ይችላል….ብዙ ሞግዚቶች ልትቀጥሪለትና እነሱ ሊንከባከቡት ይችላሉ፡፡.ግን እመኚኝ የእኔን ያህል ልምድ አይኖራቸውም.፡፡በዛ ላይ እንደዛ ማድረጌ እድሜዬን ያረዝምልኛል… አዎ ለራሴ ብዬ ነው››
‹‹ጋሼ…ወንድ ነው እንዴ? ››
‹‹ማ ?››
‹‹ልጁ..በሆዴ ያለው?››
‹‹እኔ እንጃ …ወንድም ሆነ ሴት ምን ለውጥ አለው…ዝም ብዬ አፌ ላይ ለምዶብኝ ነው››
‹‹ገባኝ››
‹‹እና ያልኩሽን ምን አልሺኝ..የጡት አባት ወይስ የክርስትና አባት..የትኛው?››
‹‹አይ እኔ የልጄ ብቻ ሳይሆን የሁለታችንም ጠባቂ አባት እንዲሆኑ ነው የምፈልገው…የእኔም የልጄም.››
‹አግኝቼ ነው..ሄኖክን ልተገቢው ነው እንዴ?ያው እሱን ካገበሽ ለሚወለደው ልጅ አያት ላንቺ ደግሞ አማች ስለምሆን ያው ጠባቂያችሁ ሆንኩ ማለት ነው››
ኮስተር አለች‹አይ በፍፅም እሱን አላገባም››
‹‹ታዲያ እንዴት ለሁለታችሁም ጠባቂ መሆን እችላለው?››ግራ በመጋባት ጠየቋት፡፡
‹‹ምነው እርሶ አያገቡኝም?...ማለቴ ..በፈለግሺው ጊዜ መሸሸጊያሽ እሆናላሁ ብለውኝ አልነበር ?››
‹‹አዎ ብዬሻለው ...ግን እንዴት ነው የሚሆነው?ግራ ገብቶኝ እኮ ነው››
‹‹ልክ ቅዱስ ዮሴፍ ለድንግል ማርያም እንደሆነት አይነት….ልክ እየሱስንም እናቲቱንም በፍጽም ንፅህና እና ቅንነት እንደጠበቀው አይነት…››
‹‹ተአምረኛ ልጅ ነሽ…ከቤተሰቦችሽና ከማህበረሰቡ የሚደርስብሽኝ ጫና የሚሸከም ጫንቃ ካለሽ እኔ ከዚህ በፊት እንደነገርኩሽ ሁሌም ያንቺው ነኝ፡፡›አሏት በፈግታ ተሞልተው፡፡
‹‹እንግዲያው እኔ ቤት ነው የምንኖረው…ከፈለጉ ሰርግ መደገስ እንችላለን፡፡››
‹ሁሉም አንቺ እንደፈለግሽ ይሆናል .. እኔ ካንቺ ጎን ከመኖር ውጭ ምንም ሌላ ፍላጎት የለኝም…የእኔ አንድ ጭንቀት በዚህ ጉዳይ ልጄን ማሳመን እንዴት እንደምችል ብቻ ነው….አባት የልጁን ፍቅረኛ ነጥቆ አገባ ሲባል ለሰሚው ከባድ ነው…›
‹‹ጋሼ የሄኖክነ ነገር ምንም አይጨነቁ ..የማናግረው እኔ ነኝ….››
‹‹እንደዘ ይሻላል?››
‹አዎ .ስለእሱ ምንም አይጨነቁ….እርሷን ሳይቀየም ፍቃደኛ ይሆናል፡፡››
‹‹እሺ እንዳልሽ….ግን ከዚህ ቡኃላም ጋሼ እንዳልሺኝ ነው የምትቀጥይው›
ፈገግ አለች…‹‹እስኪ በሂደት እንዴት ማስተካከል እንደምንችል እናስብበታለን፡፡››
‹‹ልቀልድ ብዬ ነው እንደፈለግሽ››
///
አሁን ልክ ከቀኑ 11 ሆኗል ፡፡እናም ሲፈን ሶስተኛው ቀጠሮዋ ላይ ተገኝታለች.፡፡ሄኖክም ከፊት ለፊቷ ተቀምጧል፡፡ይሄኛወ ቀጠሮዋ ከአጀማመሩም ውጥረት ያለበት ነው፡፡
‹‹ሲፈን እንድንገናኝ ስለፈቀድሽ በጣም ደስ ብልኛል››
‹‹የግድ ስለሆነ ነው የተገናኘነው››መለሰችለት፡፡
‹አዎ…የግድ ነው…በጣም ብዙ ጠብቄያለው…በመራራቃችን በመከከላችን ብዙ ብዙ ችግሮች ተፈጥረዋል…አሁን ግን ያን ሁሉ ከኃላችን ጥለን ቁስለታችንን በማከም ወደፊት መቀጠል ነው ያለብን፡፡››አለ ምን ትመልስልኝ ይሆን በመሚል ፍራቻ ፈራ ተባ እያለ..
‹‹ትክክል ብለሀል…አሁን በትክክል አድምጠኝ ፤እኔ ላለፈው ጥፋትህ ማለቴ በእኔ ላይ ለሰረሀው በደል ሁሉ ይቅር ብዬሀለው .አንተም ያስቀየምኩህ ነገር ካለ ይቅር እንድትለኝ እፈልጋለው፡፡››