Get Mystery Box with random crypto!

‹‹ይቅር ስላልሺኝ በጣም አመሰግናለው..እርግጠኛ ሁኚ በቀሪው ህይወታችን እክስሻለው….ምርጥ ባል ነ | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

‹‹ይቅር ስላልሺኝ በጣም አመሰግናለው..እርግጠኛ ሁኚ በቀሪው ህይወታችን እክስሻለው….ምርጥ ባል ነው የምሆንልሽ››
‹‹ምርጥ ባል እንድትሆንልኝ አይደለም የምፈልገው ምርጥ ልጅ እንድትሆንለኝ ነው የምፈልገው.እናትህ መሆን ነው የምፈልገው.የእንጀራ እናትህ››
‹‹እያሾፍሽብኝ ነው እንዴ?›
‹‹አይ እውነቴን ነው …ታውቃለህ በጣም የማፈቅረውን ሰው በሞት ተነጥቄያለው.እሱን መመለስ አልችልም…ግን ደግሞ በህይወት ያሉት አባትህን አፈቅራቸዋለው ….እሳቸውን ማግባት ነው የምፈልገው››
‹‹እየተበቀልሺኝ ነው?››
‹‹እሱን እንደፈለክ ተርጉመው..ግን ይቅር ተባብለናል ያልነው የእውነታ ከልባችን ከሆነ ስለበቀል ማውራት ከእኛ የሚጠበቅ አይደለም››
‹‹እና አባትህን ላግባ ማለት ሌላ ምን ትርጉም ልስጠው እችላለው?ለመሆኑ እኔ እሺ ብልሽ አባዬ በዚህ እብድ ሀሳብሽ የሚስማማ ይመስልሻል.?ነው ወይስ እናቴን እንደምትመስይ ደጋግሞ ሲነግርሽ ተምታታብሽ››
‹‹አንተ እንዲስማማ ታደርገዋለህ ››
‹‹ጭራሽ እኔው..?››
‹አዎ አንተው.አባትህን ትሄድና እኔና አንተ ያለንን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ በስምምነት እንዳቋረጥን ..እና እስከአሁንም ቃል ከመገባባት በዘለለ ምንም የፈፀምነው ፃታዊ ትስስር እንደሌላ ታስረዳቸዋለህ.፡፡በተጨማሪም አኔ እሳቸውን ማግባት እንደምፈልግ ትነግራቸዋለህ…..እናም ለአንተ ሲሉ እንደያደርጉት እሺ እስኪሉህ ድረስ እግራቸው ስር ወድቀህም ቢሆን ትማፀናቸዋለህ፡
‹‹ማይሆነውን?››
ስልኳን አወጣች…ጎረጎረችና የሆነ ነገር ላከችለት
‹‹ምርጫ የለህም…የላኩልህን ነገር እየው…ይሄ እኔ ጋር ብቻ ሳይሆን ጠበቃዬ ጋርና በጣም የማምናቸው ሌሎቸ ሰዎች ጋር በተጠበቀ የሚስጥር እቃ ተቀምጧል..እኔ አንድ ነገር ብሆን ወይም አንተ በዚህ ሀሳቤ የማትስማማ ከሆነ ወዲያውኑ ፍርድ ቤት ይቀርባል….ከዛ የሚሆነውን መገመት ቀላል ነው፡፡›
ተስገብግቦ ሞባይሉን አወጣና የላከችለትን ፎልደር ከፈተው….ወዲያው ደንግጦ ዘጋው..መልሶ ከፈተው..ወደ .ጆሮው ለጥፎ አዳመጠው.ይህ ቀጥታ ለእድሜ ልክ ዘብጥያ የሚያስወረውረው መረጃ ነው፡፡
‹‹ከየት አገኘሽው?›
‹‹እሱ ምን ደያደርግልሀል…አንተም ብቻ አይደለህም እኮ እስማርት…››
‹‹አሁን መሄዴ ነው››
‹‹አንድ ሳምንት ሰጥቼሀለው››
ምንም አልመለሰላትም በተቀመጠችበት ጥሏት አንገቱን እንዳቀረቀረ በተሰበረ ቅስም….ሆቴሉን ለቆ ወጣ፡፡

ተፈፀመ


ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj